• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የእንኳን አደረሰዎ መርሐግብር አካሄደ።

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት በየዓመቱ በበዓለ ልደት፣ በበዓለ ፋሲካና በዘመን መለወጫ በዓል ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የእንኳን አደረሰዎ መርሐግብር እንደሚያከናውን የሚታወቅ ነው። በዚሁ መሠረት የ2018ዓ.ም. የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል አስመልክቶ በዛሬው እለት የእንኳን አደረሰዎ መርሐግብር የተካሄደ ሲሆን በመርሐግብሩ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ […]

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመት ምሕረት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሐዱ ኣምላክ አሜን! + በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ + ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣ + የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣ + በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣ + እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣ እኛ በሕይወት እንኖር ዘንድ አንድ ልጁን ወደ ዓለም የላከ እግዚአብሔር […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በጎርጎርዮሳውያን /Gregorians/ የዘመን አቆጣጠር በነገው ዕለት የሚጀመረውን የ2026 አዲስ ዓመት በማስመልከት ለመላው የዓለም ማኅበረሰብእ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ

ቅዱስነታቸው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት የአማርኛ ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል፦ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ለመላው የዓለም ሕዝብ የተላለፈ አባታዊ መልእክት በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! “እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት፡- እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ ጌታ ክርስቶስ ነው።” (ሉቃ. 2፡11) የጌታችን ልደት የሰው […]

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጫ

ከሰሞኑ በአገልጋይ ሄኖክ (በጂፕኤስ) ቴሌቬዠን የተላለፈው መልዕክት የተከበረውን የሰላሌን ማህበረሰብ የማይመጥን እና አጠቃላይ የማህበረሰባችንን መልካም ባህሎችና እሴቶቻችንን የማይወክል መልዕክት በመሆኑ ጉባኤያችን ይህንን ተግባር በፅኑ ያወግዛል። እንዲህ አይነት ተግባራት መጠኑና ይዘቱ ይለያይ እንጂ በሁሉም የእምነት ተቋማት አከባቢ የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው። እንደዚህ አይነት በሃይማኖት ተቋማት ስር ተጠልለው የጥላቻ ንግግሮችንና፣ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ግለሰቦች የጥላቻ ንግግሮችን በሶሻል ሚዲያ ማስተላለፍ […]

የታኅሣሥ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በኮተቤ ደብረ ልዑል ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በድምቀት ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት፣ በየዓመቱ ታኅሣሥ ፲፱ የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል በዓል ቅዱስ ገብርኤል አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ከእቶን እሳት የታደጋቸውን ዕለት የሚዘክር መሆኑ የሚታወቅ ነው። በበዓሉ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ፣ መልአከ ምሕረት ዘካርያስ አዲስ የየካ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ መጋቤ […]

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሚያከናውናቸውን የአገልግሎት አሰጣጥና የልማትና ሥራዎችን ጎበኙ። በጉብኝቱ ወቅት የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ዓይናለም እንደገለጹት የክፍለ ከተማው ፖሊስ የአባላቶቹን ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዙ […]

የ፳፻፲፰ ዓ/ም የጥምቀት በዓልን ሥርዓቱን ጠብቆ በሰላም ማክብር እንደሚገባ ተገለጸ

የ፳፻፲፰ ዓ/ም የጥምቀት በዓል አከባበርን አስመልክቶ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ መሪነት ታኅሣሥ ፲፬ ቀን ፳፻፲፰ ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ የምክክር ጉባኤ ተካሂዷል። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በየዓመቱ ከጥር ፲-፲፪ ቀን በመላው ኢትዮጵያና ከሀገር ውጭም በመላው ዓለም በደመቀ ሁኔታ እንደሚከበር የሚታወቅ ነው። በተለይ በአዲስ አበባ በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት ብፁዕ […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ለ፺፭(95) ደቀ መዛሙርት የዲቁና ማዕረገ ክህነት ሰጡ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና የሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ለ፺፭ ደቀ መዛሙርት የዲቁና ማዕረገ ክህነት ሰጡ። ከብፁዕነታቸው ጋር መልአከ ስብሐት ዐቢይ ዘለቀ የብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ልዩ ፀሐፊ፣ ሊቀ ሊቃውንት አባ ጥዑመ ልሳን አዳነ የቂርቆስ ልደታና አዲስ ከተማ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፣ […]

መምሪያው በ25 አህጉረ ስብከት ላይ የቅዱስ ወንጌል ስምሪት ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ገለጸ

የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በ25 አህጉረ ስብከት ላይ የቅዱስ ወንጌል ስምሪት ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ገለጸ። በዛሬው ዕለት ታኅሣሥ ፲/፳፻፲፰ ዓ/ም የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ከአዲስ አበባና ከሸገር አህጉረ ስብከት የተውጣጡ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሥራ ሐላፊዎች ጋር ወይይት አድርገዋል። በምክክሩ ላይ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መመሪያ ሐላፊ መጋቤ ሐዲስ […]

በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ የተመራ ልኡክ የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ የታሪክ አሻራ ባለበት በወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረገ

በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሣዊሮስ ሊቀ ጳጳስ የተመራ ልኡክ የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ የታሪክ አሻራ ባለበት በወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረገ። በ14ኛው መቶ ክፍ ዘመን እንደተመሠረተ የሚነገርለት የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም የታሪካዊ ቅርሶችና የአያሌ ንዋያተ-ቅዱሳት ባለቤት ነው። ከነዚህም መካከል አፄ ዘርዓያዕቆብ ለቤተ ክርስቲያኑ ያበረከቱት ገድለ-ቂርቆስ፣ አፄ ፋሲለደስ ያበረከቱት የብረት መረዋ/ደወል/፣ ዜና ፋሲል […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት