ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ አሰራርን አስመልክተው ከምኒልክ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቀለ መጠይቅ
ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ አሰራርን አስመልክተው ከምኒልክ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቀለ መጠይቅ ይመልከቱ ሌሎችም እንዲያዩት በፌስ ቡክ፣ በቴሌግራም፣ በዩቲዩብ….. ሼር ያድርጉ!!!
ማስታወቂያ
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቅያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል







በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ባለፈው የአገልግሎት ዓመት የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ላሳዩ ገዳማትና አድባራት የምስጋና መርሐ ግብር አከናወነ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የ ፳፻፲፯ ዓ.ም የበጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የምስጋናና መርሐ ግብር አከናወነ። መርሐ ግብሩ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሲሆን ፳፻፲፯ በጀት ዓመት የሥራ ሪፖርት በመጋቤ ሠናይት የቻለው የአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሪፖርት ቀርቧል። በሪፖርቱ በክፍለ […]
“ውስጣዊ ችግሮቻችን በመፍታት ምእመናን ላይ መሥራት ይኖርብናል” “ተቃራኒዎችን ያበዛናቸውን እኛው መሪዎቹ ነን ምእመናኑ ላይ ምን ችግር የለም! ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ፪ኛ ዓመት አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት አጠናቋል። ኅዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም የጀመረው የሸገር ስቲ ሀገረ ስብከት አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬ ዕለትም የቀጠለ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደን ፣ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትምህርተ ወንጌልና […]
“ቤተ_ክርስቲያን_በዚህ_መልክ አስተምራ ያስመረቀቻችሁ በሌላኛው የሕይወት ገጽ የተማራችሁትን የዓለማዊ ትምህርትና እውቀት እንድትተው ሳይሆን ከመንፈሳዊ ትምህርቱ ጋር አጣጥማችሁና አቀናጅታትሁ ቤተ ክርስቲያን እንድታተርፍባችሁ ነው። ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በሥርዓተ ትምህርት መሠረት ያስተማራቸው 11,885 ተማሪዎች ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ለ5ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት አስመርቋል። መርሐ ግብሩ ሕያውን የእግዚአብሔር ቃልና ግሩም ግብሩን እንዲሁም ወርኃ ጽጌን የሚገልጹ ዝማሬዎች ፣ ኪነ ጥበብ፣ ሥነ ጽሑፍ እና ስብከት እንዲሁም በብፁዓን አባቶች ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቶበታል። በዛሬው ዕለት የተመረቁ ተማሪዎች ከ164 ገዳማት እና […]
በሰሜን አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ምእመናን ቦታ ገዝተው፣ ቤተክርስቲያን አሳድሰው አስረከቡ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካ በዩታ ግዛት ለኢትዮጵያውያን ምእመናን ቦታ ገዝተው፣ ቤተክርስቲያን አሳድሰው ያስረከቡትን የኋላኛው ቀን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ ቅዱስነታቸው ልዑካኑን “ወደ ኢትዮጵያ፣ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንኳን ደህና መጣችሁ” በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ የቤተክርስቲያኑ መሪ ቫስባንድ እንደተናገሩት […]
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ “የአብነት ትምህርት ለዘመናዊ የኢትዮጵያ ሥነ ትምህርት” በሚል መሪ መልእክት ዐውደ ጥናት አካሔደ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ “የአብነት ትምህርት ለዘመናዊ የኢትዮጵያ ሥነ ትምህርት” በሚል መሪ መልእክት ዐውደ ጥናት አካሂዷል። በዐውደ ጥናቱ የግዕዝ ቋንቋ ጥናት ለኢትዮጵያ የዕውቀት እና የምርምር ዘርፍ ስላበረከተው አስተዋጽኦ በዘርፉ ታዋቂ ምሁራን የጥናት ሥራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ ሙሉቀን አንዱዓለም (ዶ.ር) ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ የግዕዝ ቋንቋን በማስተማር ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ […]
ለሰባት ቀናት ሲካሔድ የቆየው ፻፴፫ኛው የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ምልዐተ ጉባኤ ምልዐተ ጉባኤው ተጠናቀቀ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤው መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚመራው፣ የሐዋርያት መንበር ወራሽ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ “ወይኩን ጉባኤ ሊቃነ ኤጴስ ቆጶሳት ወኤጲስ ቆጶሳት ክልዔተ ጊዜ በበዓመት ወይትናገሩ በእንተ ግብረ አብያተ […]
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ስድስተኛውን የእምነትና ሥርዓት ዓለም አቀፍ ምክክር መርሐ ግብር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ፓትርያርክ በተገኙበት በግብጽ አባ ቢሾይ ገዳም ማካሔድ ጀመረ
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ስድስተኛውን የእምነትና ሥርዓት ዓለም አቀፍ ምክክር መርሐ ግብር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ፓትርያርክ በተገኙበት በግብጽ አባ ቢሾይ ገዳም ማካሔድ ጀመረ። የስደስተኛው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት የእምነትና ሥርዓት ዓለም ዓቀፍ ምክክር ጉባኤ ዋና ርእሰ ጉዳይ “የሚታየው አንድነት አሁን የት ነው?” በሚል ሲሆን ክርስቲያናዊ ኅብረትን ለማጠናከር የታሰበ ነውም ተብሏል። በዚህ ከፍተኛ ትኩረት በሚሰጠው […]
“በቤተ ክርስቲያናችን ህልውና ላይ በዓላማ የተነሡ አካላት የላኳቸው እንዳሉ በሚመስል መልኩ በስመ ተሐድሶ የሚደረገው እንቅስቃሴ የኛው መለያ የሆነውን ንዋየ ቅድሳትና ልብሰ ተክህኖ፣ መዝሙርና ሥርዓተ አምልኮ በመጠቀም ቤተ ክርስቲያናችንን በአደባባይ እየተዳፈረ ይገኛል”፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ • ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ በአጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ ቅዱስ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፤ የጎደለብንን እየሞላ አገልግሎታችንን እያቃና ከዚህ ላደረሰን፣ ይህንን ዓመታዊና ሐዋርያዊ […]
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እጅግ ከፍተኛ ልዩ ተሸላሚ በመሆን ስጦቷ ተበረከተለት
በተያያዘም ከየምድቡ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ለወጡ አህጉረ ስብከት #የሞተር ሳይክል ሽልማት ተበርክቷላቸዋል። ጥቅምት፰/፳፻፲፰ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ከጥቅምት ፬ እስከ፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ሲካሔድ የሰነበተው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በትላንትናው ዕለት መጠናቀቁን ተከትሎ ተመሳሳይ አቅም ያላቸው አህጉረ ስብከት በአሥራ አንድ ምድብ ተከፋፍለው እንዲወዳደሩ የተደረጉት አህጉረ ስብከት ውድድር በሸልማት ኮሚቴው የመወዳደሪያ መስፈርት መሰረት […]
“አንዲት ቤተ ክርስቲያን፥ አንድ ሲኖዶስ፥ አንድ ፓትርያርክ፥ አንድ መንጋ በማለት የቤተ ክርስቲያንን እንድነት ለማስከበር ፈሪሃ እግዚአብሔርና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲጠበቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን የዓለማዊ ሐሳብ ማራመጃ እንዳትሆን የሚከፈለውን መስዋእነት ሁሉ በመክፈል አንድነቷን፣ ሕልውናዋን፣ ሉዓላዊነቷንና ነጻነቷን ለማስከበር ቃል እንገባለን፤ “
የ፵፬ኛ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አቋም መግለጫ በዓመት አንድ ጊዜ የሚደረገው ዓለም አቀፉ የሰበካ መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ ከጥቅምት ፬-፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤ/ክህነት በሚገኘው አዲሱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄዷል፡፡ መሠረቷ የማይናወጽ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘአበው ሐዋርያዊት የሆነች፣ አንድነቷ የማይከፈል ቅድስት፣ ጥንታዊትና ታሪካዊት፣ በርኀበ ዓለም ሰፋኒት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ […]