• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ሰባክያነ ወንጌል በወንጌል አገልግሎቱ ዙሪያ በቀጣይ ሳምንት ሰኞና ረቡዕ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰባክያነ ወንጌል በወንጌል አገልግሎቱ ዙሪያ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን እና ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ/ም በየክፍላተ ከተሞቻቸው ውይይት እንደሚያደርጉ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ ዋና ክፍል የተጣለበትን አደራ ለመወጣት እና በወንጌል አገልግሎቱ ዙሪያ ለውጥ ለማምጣት የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል። በተለይም ደግሞ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ባሉ ገዳማትና […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባሳለፍነው ዓመት ከ631 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በማስገባቱ ከፍተኛ ተሸላሚ ሆነ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፵፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለጥቅምት ፬/፳፻፲፯ ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። በማጠናቀቂያ መርሐ ግብሩ በየዘርፉ አህጉረ ስብከትን በማወዳዳር የእውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር ተከናውናል። ከማወዳዳሪያ ዘርፎቹ መካከል አንዱ ከፍተኛ አጽተዋጽኦ በማስገባት ዘርፍ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 631 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት […]

የአቋም መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ የአቋም መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል። “ትውልደ ትውልድ ይንእዱ ምግባሪከ ወይዜንዉ ኃይለከ – የልጅ ልጅ ሥራህን ይናገራሉ፤ ያመሰግናሉ፣ ከሃሊነትህን ይናገራሉ ያስተምራሉ” መዝ 144 ቁ 4 ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ዓለምአቀፋዊት የሆነቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያዊ ተልዕኮዋ ረጅም ዘመናትን ሰማያዊውን ጥበብንና ምድራዊውን ዕውቀትን […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባደረገው ድጋፍ በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የተዘጉ 9 አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፍቱ ማድረጉ ተገልጸ።

ሦስተኛውን ቀን የያዘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 43ኛ መንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የየአህጉረ ስብከቱ ዓመታዊ የአገልግሎት አፈጻጸም ሪፖርቶች እየቀረቡ ይገኛሉ። ከነዚህ በአዲስ የተቋቋመው የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባደረገው ድጋፍ በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የተዘጉ 9 አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፍቱ አድሮጓል በለዋል። የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ድጋፍ […]

የ፵፫ ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

የ፵፫ ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል። ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት እየተመራ ይገኛል። ቅዱስነታቸው የመክፈቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክሆነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የባሕር ዳርና […]

የአዲስ አበባ ከተማ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ። በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት አባቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሙዚና ከድር፣ ከፍተኛ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ሐላፊዎች፣ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትን ለመመርመር በጠቅላይ ቤተ ክህነት የተቋቋመውን አጥኚ ኮሚቴ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ።

መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር 782/354/2017 ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ለአጣሪ ኮሚቴ በአድራሻ ሲጻፍ በተመዘገበልን ግልባጭ ለመገንዘብ እንደቻልነው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የሚስተዋሉ የአመራር ግድፈቶችንና በአሠራር ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን አጥንቶ የሚያቀርብ ኮሚቴ መቋቋሙን ተረድተናል፡፡ ለኮሚቴው መቋቋም ምክንያቱ “በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የሚስተዋሉ የአሰራር ግድፈቶች ላይ የተፈጠሩ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ የመስቀል ደመራ በዓል ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መከበሩን አስመልክቶ የምስጋና መልእክት አስተላለፈ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ የቅዱስ መስቀል ደመራ በዓል ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በመከበሩ የምስጋና መልእክት አስተላለፈ። የ፳፻፲፯ ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል ዐደባባይ ቅዱስ ፓትርያርካችን፣ ክብርት የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት፤ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሚኒስትሮች፣ የአሜሪካን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት አምባሳደሮች በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት […]

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የቅዱስ መስቀል ደመራ በዓል በከፍተኛ ድምቀትና ሰላም መከበሩን አስመልክቶ የምስጋና መልዕክት አስተላለፈች።

የ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓትና ድምቀት ተከብሮ በመዋሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተሰማትን ደስታ ትገልጻለች። በዓሉ በተዋበና በደመቀ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑ ዝናብና ቁር ሳይበግረው በጽናትና ፍጹም በሆነ መንፈሳዊነት በዓሉን ማክበሩ እጆግ የሚያስደንቅ ሲሆን መርሐ ግብሩ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንዲችል ተረኛው ደብር፣ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ልጆቻችንና በበዓሉ […]

“#የመስቀሉ ቃል ማለት እግዚአብሔርን ፍሩ፣ ለእርሱም ታዘዙና ተገዙ ማለት ነው” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! “እስመ ነገረ መስቀሉሰ ዕበድ ውእቱ በኀበ ኅጉላን ወበኀቤነሰ ለእለ ድኅነ ኃይለ እግዚአብሔር ውእቱ፤ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ነው፤ ለኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው”(1ቆሮ. 1÷08)፤ በመስቀሉ ኃይል ከፍዳ ኃጢአት ያዳነን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት በዓለ ቅዱስ መስቀል በሰላም አደረሰን […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን