• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ዓመታዊ የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓልና የቤተ መቅደሱ መታደስ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከበረ

ዓመታዊው የአጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓልና የቤተ መቅደሱ መታደስ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከበረ። የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በትናትናው ዕለት የቤተ መቅደሱን መታደስ በዓል የተከበረ ሲሆን በዛሬ ዕለትም የቅድሥት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የካቴድራሉ ሊቃውንት ማኅሌታውያን “ዮም መላእክት ይየብቡ ወሊቃነ መላእክት […]

የጻድቁ የአቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ በዓለ ዕረፍት በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ተከበረ

የጻድቁ የአቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ በዓለ ዕረፍት በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ተከበረ። በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደኖሩ የሚነገርላቸው ጻድቁ አቡነ ሊባኖስ ትውልዳቸው ሮም ሲሆን በግብጽ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ እየተዘዋወሩ በብርቱ ቅዱስን ወንጌል በሕይወት እግዚአብሔርን በእውነት አግልግለዋል። ጻድቁ አቡነ ሊባኖስ ምንኩስናን ከአባ ጳኩሚስ የተቀበሉ ሲሆን በኢትዮጵያና በኤርትራ የተለያዩ ገዳማትን […]

“የወለዱትን ማሳደግ ከባድ በሆነበት በዚህ ዘመን ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሕጻናትን ሰብስቦ ማሳደግ ሀገራዊና መንፈሳዊ ኃላፊነትን መወጣት ነው”። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

“የወለዱትን ማሳደግ ከባድ በሆነበት በዚህ ዘመን ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሕጻናትን ሰብስቦ ማሳደግ ሀገራዊና መንፈሳዊ ኃላፊነትን መወጣት በማለት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ገለጹ። ቅዱስነታቸው ይህንን ያሉት በዛሬ ዕለት የሰበታ ጌቴሴማኒ ቤተ ደናግል ወጠባባት የእናቶች ገዳምንና በዚያ የሚያድጉ ሕጻናትን በመጎብኘት ቡራኬ በሰጡበት መርሐ ግብር […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ። ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው እንደገለጹት የሰላም ትርጉሙ ተረጋግቶ መኖር፣ ወደ ዓላማ ፍጻሜ መድረስ፣ መርቆ ማለፍ ነው። ካሉ በኋላ ወልዶ ለመሳም፣ አሳድጎ ለመዳር፣ ዐርፍተ ዘመን የገታቸውን በክብር ለመሸኘት ሰላም አስፈላጊ ነው ።ብለዋል። አያይዘውም እስካሁን […]

የ፳፻፲፯ ዓ/ም በዓለ ልደት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ እንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ተከናወነ

በየዓመቱ የሚከናወነው ይህ የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ለቤተ ክርስቲያናችን ርእሰ መንበር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ለሆኑት አባት የሚደረግ ሥርዐት ነው። መርሐ ግብሩ ከበዓለ ልደት በተጨማሪ በበዓለ ትንሣኤ እንዲሁም በዘመን መለወጫ የሚካሔድ ነው። በዚህ በ፳፻፲፯ ዓ/ም በዓለ ልደት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የእንኳን አደረሰዎ መርሐ […]

“ይእዜ አስተርአየ እግዚአብሔር ዮም እምቅድስት ድንግል፤ ዛሬ እግዚአብሔር ከቅድስት ድንግል በሥጋ ተወልዶ ታየ” ሃይ.አበው ዘቴዎዶጦስ

ተወዳጅ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ እንኳን ለ፳፻፲፯ ዓ.ም የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ! አባቶቻችን ሊቃውንት እንዳስተማሩን በዛሬው ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተዋረደውን የእኛን ሥጋ በመዋሐድ ከወድቀት ወደ ከፍታ፤ ከመዋረድ ወደ ክብር ከፍ አድርጎናል። ሁሉን ቻይ የሆነው አምላካችን ከአዳም ባሕርይ ከተገኘች እመቤታችን እንበለ ዘርዕ ነፍስንና ሥጋን ተዋሕዶ አከበረን። ለአንዲት ሰከንድ ቆም ብለን […]

“የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ ነገረ ፍቅርን፣ ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል”

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክየልደት በዓልን አስመልክተው ካስተላለፉት ቃለ በረከት የተወሰደ መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፤ በምሉእ […]

የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ከፍተኛ የአብነት ትምህርት ቤትና የዕጓለ ማውታና አረጋውያን መጦሪያ ምትክ ቦታ የወሰን ችካል ተከላ ተከናወነ

የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ከፍተኛ የአብነት ትምህርት ቤትና የዕጓለ ማውታና አረጋውያን መጦሪያ ምትክ ቦታ የወሰን ችካል ተከላ ተከናወነ። በሊቀ ሊቂውንት አባ ገብረ አብ በኋላ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ አስተባባሪነት በ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ላለፉት ፺፪ ዓመታት ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን በርካታ ሊቃነ ጳጳሳትንና እንዲሁም ሊቃውንትን እያበረከተ የሚገኝ ታላቅ የትምህርት ማእከል ነው። […]

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽን ለሰበታ ጌቴሴማኒ ቤተደናግል ጠባባት ገዳም የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽን ታኅሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በሰበታ ለሚገኘው እናቶች ገዳም በገዳሙ ውስጥ እየተማሩ ለሚያድጉ ወላጅ አልባ ህፃናት እና ገዳማዊያን የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ የማዕድ ቤት ቁሳቁስ ፤የምግብና መጠጥ ማቅረቢያ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ድጋፍ አድርጓል ። ድጋፉን ለገዳማዊያን እናቶች ያስረከቡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ለማክበር ድሬዳዋ ገቡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ የሥራ ኀላፊዎች ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤል በዓል ለማክበር ድሬዳዋ ገብተዋል። ቅዱስነታቸው ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ክቡር አቶ ከድር ጁሐር የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን