ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ አሰራርን አስመልክተው ከምኒልክ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቀለ መጠይቅ
ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ አሰራርን አስመልክተው ከምኒልክ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቀለ መጠይቅ ይመልከቱ ሌሎችም እንዲያዩት በፌስ ቡክ፣ በቴሌግራም፣ በዩቲዩብ….. ሼር ያድርጉ!!!
ማስታወቂያ
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቅያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ የ2017 ዓ/ም የአእላፋት ዝማሬ የጥናት መርሐ ግብርን አስጀመሩ
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ2017 ዓ/ም የአእላፋት ዝማሬ የጥናት መርሐ ግብርን አስጀመሩ። የጌታችንን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያው ጀንደረባው ትውልድ የሚዘጋጀው የእላፋት ዝማሬ በ2016 ዓ/ም የተጀመረ ሲሆን በርካታ ኦርቶዶክሳውያን በምስጋናው ተባብረዋል። የዝማሬ መርሐ ግብሩ በዚህ ዓመት የሚቀጥል ሲሆን ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ […]
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ በሀገረ ስብከቱ በሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተቋማዊ የሆነ የበይነ መረብ ሚዲያ እንዲቋቋም መመሪያ አስተላለፉ።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ በሀገረ ስብከቱ በሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተቋማዊ የሆነ የበይነ መረብ ሚዲያ እንዲቋቋም መመሪያ አስተላለፉ። ብፁዕነታቸው ይሄን ያሉት “መገናኛ ብዙኃን ለቤተ ክርስቲያን ተሌእኮ ” ቀሚሙም መሪ ቃል ሀገረ ስብከቱ ከTakeoff Digital ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሦስት ቀናት ሥልጠና መርሐ ግብር ተዘጋጀው ላይ ነው። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት […]
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት “መገናኛ ብዙኃን ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የሦስት ቀናት ሥልጠና ተጠናቀቀ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት “መገናኛ ብዙኃን ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የሦስት ቀናት ሥልጠና ተጠናቀቀ። ሀገረ ስብከቱ Takeoff Digital ከተባለና መቀመጫውን ዱባይ ያደረገ በcyber Security and Artifical Intelligence ከሚሠራ ድርጅት ጋር በመተባበር በማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች አጠቃቀም ዙሪያ በተመለከተ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከሁሉም ገዳማትና አድባራት ለተውጣጡ በርካታ ቁጥር ላላቸው ሠልጣኞት ሥልጠናው ተሰጥቷል። ሥልጠና በብፁዕነታቸው […]
የመካነ መቃብራት አያያዝና አጠቃቀም ትኩረት እንደሚሹ ተገለጸ።
የሰው ልጆች ምድራዊ ቆይታችንን አጠናቀን ከዚህ ዓለም በሞት በምንለይበት ወቅት ቤተ ክርስቲያን አስከሬናችንን ተቀብላ በክብር በቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ውስጥ ታሳርፈዋለች። በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚገኙ መካነ መቃብራት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አስከሬኖችን ይዘው የሚገኙ ቢሆንም በተደጋጋሚ ጊዜ ከምእመናን ከሚነሱ ቅሬታዎች መካከል ለቦታው ልዩ ትኩረት ካለመስጠት የተነሳ የፅዳት ችግር እና የተለያዩ አላስፈላጊ ድርጊት እየተፈፀመባቸው መሆኑ ይገኛል። ስማቸውን […]
የሰባክያነ ወንጌል ኅብረት ጥሪ
ለታላቅ የምሥራች ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ “በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” ፩ኛ ቆሮንቶስ ፱፥፳፫ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ትልቁ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአ/አ ሀገረ ስብከት የሰባክያነ ወንጌል ኅብረትን በማስመልከት የምስጋናና የዕውቅና መርሐግብር ላይ መላው ኦርቶዶክሳውያን ተገኝታችሁ የደስታ ቀናችንን በጋራ እናክብር በማለት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ በዕለቱም፡- […]
“ሰላም ከአንገት በላይና ዝም ላለማለት ያህል የምንናገረው ሳይሆን ዋጋ ከፍለን የምናመጣው ነው”
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ጥቅምት ፳፭/፳፻፲፯ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ መልእክት አስተላልፈዋል። በመልእክታቸውም “ሰላም ከአንገት በላይና ዝም ላለማለት ያህል የምንናገረው ሳይሆን ዋጋ ከፍለን […]
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ […]
ለ፲ ቀናት በዝግ ሲካሔድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በሚሰጠው መግለጫ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ።
ለ፲ ቀናት በዝግ ሲካሔድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በሚሰጠው መግለጫ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ በጥቅምት 12 እና በግንቦት ርክበ ካህናት (የትንሣኤ 25ኛ ቀን) ይካሔዳል። በዚህ ዓመት የጥቀምት ቅዱስ ሲኖዶስ መልዐተ ጉባኤ ከጥቅምት 12/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ሲካሔድ የቆየ […]
የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ባሕረ ጥምቀት ቦታ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ሥራዎች መጀመራቸው ተገለጸ።
የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ባሕረ ጥምቀት ቦታ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ሥራዎች መጀመራቸው ተገለጸ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቦሌና ለሚኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል የባሕረ ጥምቀት ከተማ አስተዳዳሩ ከሚከተለው የኮሪደር ልማት ጋር በተገናዘበ መልኩ አገሎግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ፕሮጆክቶች እንደሚሠሩበት የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት […]
ለቅዱስ ያሬድ የዜማ ኮሌጅ የወሰን ችካል ለመቸከል በትናትናው ዕለት ተይዞ የነበረው መርሐ ግብር መስተጓጎሉ ተገለጸ።
ለቅዱስ ያሬድ የዜማ ኮሌጅ የወሰን ችካል ለመቸከል በትናንትናው ዕለት ተይዞ የነበረው መርሐ ግብር መስተጓጎሉ ተገለጸ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ የዜማ ኮሌጅ ቦታ አቅርቦት እንዲዘጋጅላቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ሚያዚያ 5/2013 ዓ/ም ከተወሰነላቸው የቦታ ጥያቄዎች መካከል አንዱ እንደነበር ሰነዱ ያስረዳል። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ከተማ አስተዳደሩ የቦታ አቅርቦቱ እንዲዘጋጅ በንፋስ ስልክ ላፍቶና በለሚ […]