• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የአትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ለመንበረ ፓትርያርክ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች መጻሕፍትን አበረከተ

የአትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ለመንበረ ፓትርያርክ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች መጻሕፍትን አበረከተ ። በመርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የመምሪያው የበላይ ሊቀ ጳጳስ ሊቀ ኅሩያን ይልማ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሐፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የመምሪያው ሐላፊ እንዲሁም የየተቋማቱ የሥራ ሐላፊዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር […]

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያንን የሕንጻ እድሳት ጎበኙ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውን የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያንን የሕንጻ እድሳት ሥራ ጎብኝተናል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ከዓድዋ ታሪክ ጋር በእጅጉ የተሣሠረ ታሪክ አለው፡፡ በዚህም የተነሣ በሁለተኛው የፋሽስት ወረራ ጊዜ እንደ ጦር ወንጀለኛ ተቆጥሮ ዋጋ ከፍሏል፡፡ በእሳት እስከ መቃጠልና ጥቁር ቀለም እስከ መቀባትም ደርሷል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ደረጃውን በጠበቀና ልዩ ልዩ ባለሞያዎችን ባሳተፈ መልኩ […]

“ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን ዕድገት” በሚል መሪ ቃል ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎች ሥልጠና ተሰጠ

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በ፳፻፲፷ ዓ.ም ትኩረት በመስጠት እሠራባቸዋለሁ ካላቸው ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋነኛው የቴክኖሎጂ ልማት […]

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት “አገልግሎቴን አከብራለሁ” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ የምስጋና የእውቅና መርሐግብር አካሄደ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት “አገልግሎቴን አከብራለሁ” ( ሮሜ 11፥13-14) በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ ኅዳር ፳፬ /፳፻፲፰ ዓ/ም በቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የምስጋና የእውቅና መርሐግብር አካሄደ። በመርሐግብሩ ላይ ክቡር መልአከ ገነት ልሳነወርቅ ተስፋ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ […]

ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ “ቆሞሱን ጳጳስ” በማለት በዐውደ ምሕረት የተናገሩት ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰና መጋቤ ሐዲስ ቃለ ጽድቅ ግርማ ይቅርታ ጠየቁ

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ሀብታተ ቤተ ክርስቲያን ከሚባሉት መካከል በዘር የማይሰጥ በብሔር የማይታደል፣ ሥጋዊ ደማዊ በሆነ ድምጽ ብልጫ የማያገኙት፣ ልሁን ስላሉ የማይሆኑት አልፈልግም ስላሉም የማይቀር በመንፈስ ቅዱስ መራጭነት እንደቸርነቱ ለተገባቸው አካላት ብቻ የሚሰጠው “ሀብተ ክህነት” ዋነኛው ነው። ይህን ሀብተ ክህነት ደግሞ ሐዋርያዊት የሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ክብረ ክህነትን በቀኖና ጠብቃ፣ ከትውልድ ትውልድ አልፋ […]

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጠቃላይ የሥራ ሂደት ላይ ያላትን ተቋማዊ ሀሳብ እያቀረበች ትገኛለች

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስከአሁን የሠራቸውን ሥራዎች እና ወደፊት ለመሥራት በዕቅድ በያዛቸው ሥራዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማትና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኀላፊዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል። ኮሚሽኑ ዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ለስብሰባው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተወከሉት […]

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሯል

በበዓሉ ላይ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ መጋቤ ሠናያት የቻለው ለማ የአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ አሚን ለይኩን አበጀ የደብሩ አስተዳዳሪ ፣የሀገረ ስብከቱና የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ተወካዮች፣ የሰበካ ጉባኤና የሕንጻ ኮሚቴ አባላት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የደብሩ ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት […]

“ከእግዚአብሔር ጋር ያልታረቀ የሕይወት ሰልፍ ውጤቱ ሽንፈት ነው” ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፳፩ ቀንን በዋናነት የጽዮን ቅድስት ማርያም ዓመታዊ በዓል መሆኑን በማሰብ በተለያዩ መንፈሳዊ ድንቅ ሥርዓታት ታከብረዋለች። በዓሉ ከብሉይ እስከ ሐዲስ፣ ከታቦተ ጽዮን እስከ ድንግል ማርያም ፣ ከደብረ ሲና እስከ ሴሎ ፣ ከምርኮ እስከ ድል፣ ከደብተ ኦሪት እስከ ቤተ መቅደስ፣ ከዳዊት እስከ ቀዳማዊ ምኒልክ ፣ ከምሳሌነት እስከ አማናዊነት ፣ ከእስራኤል እስከ […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ በየካ አባዶ አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በየካ አባዶ አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ። በጉብኝቱ ከብፁዕነታቸውን ጋር መጋቤ አእላፍ ማሙየ ሸዋፈራው የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ፣ መጋቤ ስብሐት ዐቢይ ዘለቀ የብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ፕሮቶኮልና ልዩ ጸሐፊ፣ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ እግዚአብሔር ታደለ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት […]

የሊጋባው በየነ ልጅ ባሠሩት በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በተገኙበት የተለያዩ የራስ አገዝ ልማት ሥራዎች ተመረቁ

የሊጋባው በየነ ልጅ ባሠሩት በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በተገኙበት የተለያዩ የራስ አገዝ ልማት ሥራዎች ተመረቁ። በመርሐ ግብሩ ላይ ክቡር ዋና ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ መጋቤ አእላፍ ማሙየ ሸዋየ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ፣ መጋቤ ስብሐት ዐቢይ ዘለቀ የብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ልዩ ጸሐፊ፣ መልአከ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት