• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ። በመርሐ ግብሩ ላይ የመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እንዲሁም የአዲስ አበባና የሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ እና የመስቀል በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ በተገኙበት ከአዲስ […]

ተቀጸል ጽጌ በዓል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጬጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት ተከብሯል

መስከረም ፲/፳፻፲፰ ዓ/ም በየዓመቱ መስከረም ፲ ቀን በጥንት ጊዜ ወርኃ ክረምቱ አለፈ የጽጌ ዘመን መጣ ይህን ያደረገ እግዚአብሕር ይመስገን ሲሉ ተቀጸል ጽጌን መስከረም ፳፭ ቀን በታላቅ የምስጋና ማዕድ በቤተ ክርስቲያንንና ነገሥታቱ አብያተ መንግሥት ይከበር ነበር። በኋላ አጼ ዳዊት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ግማደ መስቀል ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ መስከረም ፲ ቀን በመግባቱ ምክንያት መስቀል ከሁሉም ነገር […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያለፉት 100 ቀናትና ሥራዎቹ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚገኙ ጥንታውያት አህጉረ ስብከት መካከል አንዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ነው። ሀገረ ስብከቱ በሥሩ 8 ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት፣ ከ260 በላይ አብያተ ክርስቲያናት፣ ከ30,000 በላይ አገልጋዮችና ሠራተኞች፣ በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰንበት ተማሪዎች፣ እጅግ ብዙ ደጋግ ኦርቶዶክሳውያን የሚገኙበት ታላቅ ሀገረ ስብከት ነው። ሀገረ ስብከቱን በርካታ ብፁዓን […]

“ከምክርቤት እስከ መምሪያ” የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መዋቅር

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የምስካየ ኅዙናን ገዳም የበላይ ኀላፊ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፣ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ እና የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ የበላይ ኀላፊ ክቡር ንቡ እድ ኤልያስ አብርሃ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክህነት ጽ/ቤት […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ከ፪፻ አገልጋዮች በላይ ክህነት ሲሰጡ የአንድ ቤተሰብ አባላት #አባታቸው የቅስና ሁለት ልጆቹ የዲቁና ማዕረግ ተቀበሉ

መስከረም ፬/፳፻፲፰ ዓ/ም ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና የሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለተ ሰንበት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ከ፪፻ በላይ ለሚሆኑ አገልጋዮች ማዕረገ ክህነት ሰጡ። ከተቀበሉት አገልጋዮች መካከልም የአንድ ቤተሰብ አባላት #አባታቸው_ቅስና_ሁለት_ልጆቹ_ዲቁና_ማዕረግ_ተሰጥቷቸዋል። በቦሌ መከብፁዕነታቸው ጋር በመሆን ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ማዕረገ ክህነት የሰጡ ሲሆን መጋቤ ስብሐት ዐቢይ […]

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የዐዲስ ዓመት የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ያስተላላፉት የእንኳን አደረሰዎ መልእክት

< ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው፡፡ መዝ. 102,24> ❖ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ❖ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ እና የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ የበላይ ሓላፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ❖ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት […]

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ለ፳፻፲፰ ዓ/ም ዐዲስ ዓመት የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ተካሔደ

የ፳፻፲፰ ዓ/ም ዐዲስ ዓመት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ተካሔደ። በመርሐ ግብሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ተሃይማኖት፣ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የመንበረ […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት የበላይ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የተመራ የሥራ አመራር ቦርድና አስተዳደር ልኡክ ለብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞቱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት የበላይ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የተመራ የሥራ አመራር ቦርድና አስተዳደር ልኡክ ለብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞቱን ገለጸ። ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የምሥራቅ ና የሰሜን አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የመገናኛ ብዙኃኑ የበላይ ሐላፊ የተመራ ልኡኩ […]

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ቃለ በረከት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የ2018 ዓ,ም የዘመን መለወጫ በዓልን መግባት አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል ፣ የቅዱስነታቸው ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው። ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምርቃትን አስመልክቶ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ። የቅዱስነታቸው መልእክት የሚከተለው ነው

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ‹‹ወስሙ ለካልእ ፈለገ ግዮን ወውእቱ ዘየዐውድ ኵሎ ምድረ ኢትዮጵያ፦ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል ” (ዘፍ 2+13) ኢትዮጵያ የሚለው ስም ጽርዓዊ፣ ደኃራዊ ስም ሲሆን ቀደም ሲል የኖኅ የልጅ ልጅ በሆነው በኵሽ ምክንያት የኵሽ ምድር እንዲሁም ምድረ አዜብ፣ ምድረ ሳባ፣ ምድር ኣግዐዚት በመባል […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት