• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የውስጥ ቢሮዎች ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ ተመረቀ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የውስጥ ቢሮዎች ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዲዮስቆሮስ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ ተመረቀ ። የሀገረ ስብከቱ ዋና መሥሪያ ቤት ቀደም ሲል ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ሊቀ ጳጳስ በሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ለመሥራት አቅደው ባይሳካም በኋላ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በአዲስ አበባ ሀገረ […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ በአቃቂ ደብረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው በደብሩ የተሠሩት የልማት ሥራዎች አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ ባረኩ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአቃቂ ደብረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው በደብሩ የተሠሩት የልማት ሥራዎች አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ ባረኩ። ከብፁዕነቻው ጋር የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤና የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች አብረው ተገኝተዋል። ብፁዕነታቸው የመጀመሪያውን ጉብኝት በአቃቂ ደብረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ […]

“150 ተፈናቃይ አገልጋዮችን” በተመለከተ ሀገረ ስብከቱ ወደ ሥራ መድቦ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑ ተገለጸ

በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነላቸውን “150 ተፈናቃይ አገልጋዮችን” በተመለከተ ሀገረ ስብከቱ ወደ ሥራ መድቦ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑ ተገለጸ። ዛሬ ከሰዓት በኋላ በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መሪነት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ፣ የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ የሀገረ ስብከቱና […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ በመገንባት ላይ ያለውን የፍል ውሃ መድኃኔዓለም ሕንፃ ቤተክርስቲያን ጎበኙ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ፣ የሐድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነትና የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰባኪያን ኅብረት ሰብሰቢና ሥራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት በልዩ ሁኔታ በመገንባት ላይ ያለውን የአያት የፍል ውሃ መድኃኔዓለም (አያት ጸበል) ሕንፃ ቤተክርስቲያን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት ብፁዕነታቸው ሕንፃ ቤተክርያኑን ከታች እስከላይ ድረስ የጎበኙ […]

የደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ለነበራቸው አባታዊ ፍቅርና የእረኝነት አገልግሎት ምስጋናውን ገለጸ

የደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ለሰጡት አባታዊ አገልግሎት ምስጋናውን ገለጸ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ለብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀዲያና ስልጤ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ መንበረ ጵጵስና መድኃኔዓለም ካቴድራል ደማቅ አሸኛኘት መርሐ ግብር ተደረገላቸው። በመርሐ ግብሩ ላይም ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ከሀገረ ስብከቱና ከክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሐላፊዎችና ሠራተኞች ጋር ትውውቅና ውይይት አካሄዱ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ከሀገረ ስብከቱና ከክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሐላፊዎችና ሠራተኞች ጋር ትውውቅና ውይይት አካሔዱ ። ግንቦት 15/2017 ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው መመደባቸው የሚታወስ ነው። በመሆኑም ብፁዕነታቸው በዛሬው ከሀገረ ስብከቱና ከክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሐላፊዎችና ሠራተኞች ጋር ትውውቅና ውይይት ያደረጉ […]

“የቤተ ክርስቲያንን እድገት በተግባር አረጋግጠን የቤተክርስቲያንን ልዕልና ለማስጠበቅ በጋራ መሥራት ይኖርብናል” ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ

የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት የመጀመሪያውን ቀን ጉባኤና የትውውቅ መርሐ ግብር አካሔደ። አስተዳደር ጉባኤው ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሔደው ጉባኤና የትውውቅ መድረክ ላይ በቀጣዮቹ የሥራ ጊዜያት የቤተክርስቲያንን ልዕልናና ዕድገት ሊያረጋግጥ የሚችል ሥራ በመሥራት ቤተ ክርስቲያንን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ በሚደረገው ጥረት ውስጥ አስተዳደር ጉባኤው ፍፁም የሆነ ተቋማዊ አሠራርን […]

“ቤተ ክርስቲያን የጣለችብንን መንፈሳዊ ሐላፊነትና አደራ ሁላችንም እጅ ለእጅ በመያያዝ በጋራ እንደምንወጣ ተስፋ አደርጋለሁ” ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ

“ቤተ ክርስቲያን የጣለችብንን መንፈሳዊ ሐላፊነትና አደራ ሁላችንም እጅ ለእጅ በመያያዝ በጋራ እንደምንወጣ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተናገሩ። በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገረ ስብከቱ መግባታቸውን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጡ መርሐ ግብር ተከናውኗል። በመርሐ ግብሩ ላይ […]

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ በደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ትናንት ጥር ፲፯/፳፻፲፯ ዓ/ም ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ። በሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ደብሩ ለሰንበት ትምህርት ቤት መገልገያ እንዲሆን የሚገነባው ባለሁለት ወለል (G+2) ሕንጻ መሠረት ድንጋይ ባርከው አስቀምጠዋል። ከዚሁ ጋር ደብሩ ለጸበል አገልግሎት እንዲሰጡ ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን 12 ክፍሎች መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። ብፁዕነታቸው በደብሩ […]

የከተራ እና የጥምቀት እንዲሁም የቃና ዘገሊላ በዓላት በሰላም መከበራቸውን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

“ይትባረክ እግዚአብሔር፣ አቡሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ዘባረከነ በኩሉ በረከተ መንፈስ ቅዱስ ዘበሰማያት በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን ፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ” (ኤፌ.1፥3/ ብርሃነ ዓለም እየተባለ የሚጠራው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ የተባረክንበት በረከት ምንያህል ትልቅ መሆኑንና ባረኪው እግዚአብሔር በልጁ እንደቀሰን ሲናገር “በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን