ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ አሰራርን አስመልክተው ከምኒልክ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቀለ መጠይቅ
ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ አሰራርን አስመልክተው ከምኒልክ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቀለ መጠይቅ ይመልከቱ ሌሎችም እንዲያዩት በፌስ ቡክ፣ በቴሌግራም፣ በዩቲዩብ….. ሼር ያድርጉ!!!
ማስታወቂያ
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቅያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል







“ልጃችን መምህር_ዘለዓለም ወንደሙ ያለዋጋ የተቀበለውን የእግዚአብሔር ቃል ለምእመናን በማስተማር አደራውን በሚገባ ተወጥቷል”
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ” በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሐዱ አምላክ አሜን !! ‹‹ወነአምር ከመ ለእመሂ ተነሥተ ቤተ ማኅደርነ ዘበምድር ዘውእቱ ሥጋ ብነ ሕንጻ በኀበ እግዚአብሔር በሰማያት ዘኢገብሮ እደሰብእ፡- በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን፡፡›› (2ቆሮ. 5፡1) በልዩ ልዩ ጊዜያት ዐረፍተ ዘመን የገታቸውን ወገኖች ልንሸኝ እንችላለን፤ የአንዳንድ […]
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀዲያና ስልጤ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የመምህር ዘለዓለም ወንድሙ የሥጋ ዕረፍት አስመልክተው ጥልቅ ኀዘናቸውን ገለጹ
ወአርአይከኒ ፍኖተ ሕይወት የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ መዝ 16÷11 – አንተ መንገዴ ሆነህ ወደ ሕይወት እንዳቀና አደረግኸኝ – በመንገድነትህ የደረስኩበት ሕይወት አንተ ነህ። መምህር ዘለዓለም ወንድሙ ለወንጌል የተሰጡ የሕይወት መንገዳቸውን በወንጌል ተልዕኮ ላይ ትኩረት በማድረግ የመሩ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን ለምናደርግላቸው የአገልግሎት ጥሪ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በታዣነት በትጋት ያገለገሉ ልጃችን ነበሩ:: መምህር ዘለዓለም ወንድሙ […]
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በዝውውርና በአዲስ ምድብ የተመደቡት የየክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጆች የተሰጣቸው ሐላፊነት ሹመት ሳይሆን የአገልገሎት ጥሪ መሆኑን ሳይዘነጉ እንዲያገለግሉ አሳሰቡ
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በዝውውርና በአዲስ ምድብ የተመደቡት የየክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጆች የተሰጣቸው ሐላፊነት ሹመት ሳይሆን የአገልገሎት ጥሪ መሆኑን ሳይዘነጉ እንዲያገለግሉ አሳሰቡ። ብፁዕነታቸው ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ተዘዋውረውና በአዲስ ምደባ እንዲያገለግሉ ለተመደቡት ሥራ አስኪያጆች የእንኳን ደህና መጣችሁና የትውውቅ እንዲሁም የሥራ መመሪያ መስጫ መርሐ ግብር […]
በሩሲያ ውስጥ ካሉ ግዙፍ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የ”ጋዝፕሮም” ሚዲያ ልዑካን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅትን ጎበኙ
የ”ጋዝፕሮም” ሚዲያ ልዑካን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ዘመናዊ የቴሌቭዥን ስቱዲዮን ጨምሮ በድርጅቱ ቅጽረ ግቢ ውስጥ የሚከናወነውን የፕሮዳክሽን የሥራ ሂደትና የአስተዳደር ቢሮችዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ የ”ጋዝፕሮም” ሚዲያ ልዑካን በጉብኝታቸው ሩሲያ ከአፍሪካ በተለይም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር ያላትን ግንኙንት ይበልጥ ማጠናከር እንደምትፈልግ የገለጹ ሲሆን ልዑካኑ የቤተክርስቲያኗን ሚዲያ መጎብኘቱም ለዚህ መሻት አንዱ ማሳያ […]
‹‹ተዘከሩ መዋዕለ ዘቀዲሙ የቀደመውን ዘመን አስቡ›› (ዕብ. 10÷32)
ኢትዮጵያ ሀገራችን የብሉይ ኪዳን ሥርዐትን መቀበሏ፥ ከነገደ እስራኤል ለመመሳሰል ብላ ወይም የልማድ ተጽዕኖ ደርሶባት ሳይሆን፤ ከጥንት ጀምሮ በሕገ ልቡና ከነ መልከጼዴቅ፥ ከነዮቶር የተማረችው እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ቶራህ የሚባለውን የአይሁድ እምነት መጽሐፍ ቅድመ ክርስትና ትጠቀምበት ነበር፤ እንዲሁም ከክርስቶስ ልደት በፊት በሦስተኛው ክፍለ ዘመን በሰሜን አፍሪካ ብሉይ ኪዳን ወደ ጽርእ ቋንቋ ተተርጒሞ የመላው ዓለም ሀብት ሁኖ […]
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በቅዱስ ፓትርያርኩ 13ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
“ ወምክሆሙ ለውሉድ አበዊሆሙ – የልጆችም ክብር አባቶቻቸው ናቸው።” (መጽሐፈ ምሳሌ 17፥6) ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ እንኳን ለ13ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላም አደረስዎ፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን በተናገረው በዚህ ታላቅ የጥበብ ቃል ውስጥ “አባቶች” የሚለው ቃል ሥልጣንን፣ ጥበቃን፣ ማንነትን እና የሥነ ምግባር መሠረትን ይወክላል። የእውነተኛ ልጅ ክብር ሀብት፣ ሥልጣን ወይም ሌላ ደረጃ አይደለም፡፡ የልጆች ክብር አባቶች ናቸው፡፡ አባቶች […]
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !! ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ ኣህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዲስ ዋና ጸሓፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ እና የሓዲያ ስልጤ ኣህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፣የቅዱስ ሲኖዶስ […]
የቅዱስ ፓትርያርኩን “ሐዋርያዊ አገልግሎት ፤ አባታዊ ትምህርት ፤ ወቅታዊ መረጃዎችና ታሪካዊ ሰነዶችን” የሚያቀርብ ድረ-ገጽ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ይፋ ተደረገ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ፤ የቅዱስነታቸውን የዕለት ከዕለት ሐዋርያዊ ተግባራት አባታዊ መመሪያዎች፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን እና የቤተክርስቲያኒቱን ዘመናዊና ታሪካዊ ክንውኖች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተደራሽ የሚያደርግ አዲስ ድረ-ገጽ በይፋ ሥራ ማስጀመሩን አስታወቀ። የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት eotcp.org በሚል አድራሻ ይፋ ያደረገው ይህ ዲጂታል መድረክ፤ ከመደበኛ የዜና ማሰራጫነት ባለፈ […]
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ የቤተክርስቲያናችንን ንዋያተ ቅድሳት ያለአግባብ በሚጠቀሙና ክብር ዝቅ በሚያደርጉ አካላት ላይ በሕግ ሊያስጠይቅ የሚያስችል ሥራዎችን መሥራት እንዳለበት አሳሰቡ
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ የቤተ ክርስቲያናችንን ንዋያተ ቅድሳት ያለአግባብ በሚጠቀሙና ክብር ዝቅ በሚያደርጉ አካላት ላይ በሕግ ሊያስጠይቅ የሚያስችል ሥራዎችን መሥራት እንዳለበት አሳሰቡ። ብፁዕነታቸው ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት የቤተክርስቲያንኗን የአእምሮ ሀብትና ቅርሶች ለማስከበር የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ በቀጣይ በሚሠሩ ሥራዎች ዙርያ ባካሔደው የውይይት መርሐ ግብር ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊና ታሪካዊ […]
በብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለደብሩ ማኅበረ ካህናት የሚሰጠውን የሦስት ወራት ሥልጠናን አስመልክቶ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናወነ
በብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለደብሩ ማኅበረ ካህናት የሚሰጠውን የሦስት ወራት ሥልጠናን አስመልክቶ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናወነ። በመርሐ ግብሩ ላይ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ሊቀ ሊቃውንት አባ ጥዑመ ልሳን አዳነ የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ፣ ሊቀ ብርሃናት አድማስ […]