• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

በፉሪ ጽርሐ ንግሥት ቅድስት ሐና ቤተ ክርስቲያን ለሚያገለግሉ ማኅበረ ካህናት ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል!!

በጽርሐ ንግሥት ቅድስት ሐና ቤተክርስቲያን ለሚያገለግሉ ማኅበረ ካህናት ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ዘማርያም ሙጬ ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት ሥልጠና የራሱ የሆነ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል። አያይዘውም የዚህ ሥልጠና ዋና ዓላማ የደብሩ ካህናትን በሥልጠና ብቁ በማድረግ የወንጌል አገልግሎትን በሰፊው ለምእመናን በማድረስ ለመንግሥቱ ማዘጋጀት እንደሆነ ገልጸዋል። የን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ በኩረ ትጉኃን ደመላሽ […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ለ32 የአብነት ተማሪዎች  የዲቁና እና የቅስና ማዕርገ ክህነት ሰጡ!!

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሲኤምሲ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተገኝተው ለ31 የአብነት ተማሪዎች የዲቁና፣ ለአንድ ዲያቆን የክህነት ማዕርገ ሥልጣን ሰጥተዋል። መጋቢት 09 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ መልካም ፈቃድ በመ/ምሕረት በቃሉ ወርቅነህ የሀገረ ስብከቱ የትምህርትና የሥልጠና ዋና ክፍል ኃላፊ አስተባባሪነትና ፈታኝነት ከደብረ […]

እጅግ ባማረ መልኩ ሁለንተናዊ ዕድሳት የተካሄደለት የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ!!

በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ ባማረ መልኩ ሁለንተናዊ ዕድሳት የተካሄደለት የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ። ከአንድ ዓመት በፊት ማለትም መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታዊ መልካም ፈቃድ  ፅላቱን ጊዜያዊ መቃኞ በማስገባት ዕድሳቱ እንዲጀምር መደረጉ የሚታወስ ነው። በ2013 ዓ.ም ወርኃ ሚያዚያ የተጀመረው ሁለንተናዊ […]

  ” መጻጒዕ “

አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት “መጻጒዕ”ይባላል። ትርጉሙም በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዘ በሽተኛ ማለት ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ከቅዱስ ያሬድ ቢሆንም የዕለቱ ሙሉ ታሪክ የሚገኘው ግን በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩-፳፭ ባለው ክፍል ላይ ነው። በዚህ ዕለት የእግዚአብሔር አምላካችን ፈዋሽነትና አዳኝነት እንዲሁም ታዳጊነትና የወደቁትን የማይረሳ  እውነተኛ መድኃኒት መሆኑ የሚዘከርበትና ምሥጋና የሚቀርብበት ነው። ዘማሪው ቅዱስ ዳዊትም “እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ […]

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ተፈጸመ !!!!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዐሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና  ብፁዓን አበው  ክብርት ፕረዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት ብዙ የአሃት አብያተክርስቲያናት ሊቃ ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መምህራን እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ስለቅዱስነታቸው የረጅም ጊዜ […]

“ምኩራብ”

“እስመ ቅንዓተ ቤትከ በልዓኒ፤ የቤትህ ቅንዓት በላኝ።” (መዝ. 68፥9፤ ዮሐ. 2፥17) የዐቢይ ፆም ሦስተኛው ሰንበት (እሑድ) ምኩራብ ይባላል፦ ስያሜውን ያገኘው ጌታችን በአይሁድ ቤተ-መቅደስ ተገኝቶ ቤተ-መቅደስ ንጹህ የእግዚአብሔር ቤት፣ የጸሎት ቤት፣ ሃይማኖትና ጽድቅ  የሚነገርበት የተቀደሰ/የተለየ ቦታ መሆኑን ያረጋገጠበት ስለሆነ ነው። ሊቁም “ቦአ ኢየሱስ ምኩራቦሙ ለአይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት” በማለት ጌታችን  ወደ ቤተመቅደሱ የገባ ክህደትና ዓለማዊነትን አስወግዶ […]

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት በመስቀል አደባባይ ተካሄደ።

የቅዱስነታቸው አስከሬን ከሃሌ ሉያ ሆስፒታል በክብር ታጅቦ መስቀል አደባባይ ከደረሰ በኋላ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መርሐ ግብሩን በጸሎት አስጀምረዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ 9 ዓመት በጵጵስና፤ 34 ዓመት ደግሞ በፓትርያርክነት እንዳገለገሉ ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በመርሐ […]

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ስብከተ ወንጌልን በተመለከተ ሥልጠና  እየተሰጠ ይገኛል!!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የክፍለ ከተማው አስተዳዳሪዎች፣ ሰባክያነ ወንጌልና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች ስብከተ ወንጌልን አስመልክቶ እየተሰጠ ያለውን ሥልጠና እየተከታተሉ ይገኛሉ። ሰልጣኞቹ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ ክቡር ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የደብረ እንቁ ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የልማት ሥራዎችን ጎበኙ!!!

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን እየተሰራ ያለውን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እና 64 ሜትር የሚረዝመውን የመስቀል ፕሮጀክት ግንባታን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት ለብፁዕነታቸው ከሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ እና ከአካባቢው  ምዕመናን ስለገጠማቸው አጠቃላይ ተግዳሮት አስረድተዋል። ብፁዕነታቸው በበኩላቸው ወቅቱ ዓብይ ጾም በመሆኑ ምዕመናን ጾሙን በተረጋጋ መንፈስ መጾም እንዳለባቸው […]

ቅድስት ( የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት )

ትርጉም የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ቅድስት ይባላል፤ ትርጓሜውም የተቀደሰች የተለየች ማለት ነው። ስያሜውም የተገኘው ከቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ በዚህ ሳምንት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ቅድስና በሰፊው ትምህርት ይሰጣል፡፡ ሥርዓተ ቅዳሴው በሚካሄድበት ጊዜም የሚሰበከው ምስባክ፣ የሚነበቡ መልዕክታት፣ የሐዋርያት ሥራና ወንጌል ስለ ቅድስና የሚያስተምሩና የሚሰብኩ ናቸው፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ በዚህ ሳምንት፦ ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ ቅድስና፣ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን