• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

004

ዕለታተ ሰሙነ ሕማማት

ሰሙነ ሕማማት ምንድን ነው? ከዕለተ ሆሣዕና ሰርክ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ ወይም ቀናት የሚያመለክት ነው፡፡ ሐመ ማለት ታመመ ማለት ሲሆን ይህም የሰውን ዘር ሁሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነፃ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች የሚያሳስብ ነው፡፡ ዕለታቱ የዓመተ ኩነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት፣ የሚያለቅሱበት፣ የሚሰግዱበት […]

የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ቱፊታዊ ክንዋኔዎች

በዐቢይ ጾም ከሰርክ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከነዚህ ክንዋኖዎች ውስጥ አለመሳሳም፣ አክፍሎት፣ ቄጤማ ማሰር፣ ጥብጠባ፣ ጉልባን እና ሕፅበተ እግር ይገኙበታል፡፡ ስለእነዚህ ክንዋኔዎች በቅድስት ቤተ ክስቲያን ስላለው ትውፊታዊ አፈፃፀም መዛግብት አገላብጠን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

{flike}{plusone}

002

በዓለ ሆሳዕና እና ታሪኩ

            እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ!! የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩስአሌም ሲገባ የሚቀድሙት እና የሚከተሉት ህዝብ በተለይም አእሩግ እና ህጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም ሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና በአርያም “ በማለት ጌታችንን መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው። ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ […]

በሃይማኖት ሽፋን ቅ/ኤልያስ መጥቷል ብለው በኤልያስ ስም ሲነግዱ የነበሩ ግለሰቦች ንፁሀን ዜጎችን ሲያስደበድቡና ሁከት ሲፈጥሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ታሰሩ

ቀደም ሲል በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በተለያዩ የቤተክርስቲያኒቷ አገልጋዮች የተፃፉትን ጽሑፎች በአህጉረ ስብከታችን ዌብ ሳይት ስናስነብብ መቆየታችን አይዘነጋም፡፡ ምንም እንኳን ጉዳዩ ዘግይቶ በተለያዩ ሚዲያዎች መሰራጨት የጀመረ ቢሆንም ቀደም ሲል ከሁለት ዓመታት በፊት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጀርባ በተለምዶ ቆሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው መንደር ቤተክርስቲያኑንና ህብረተሰቡን ሲረብሹ የቆዩ ሲሆን የካቴድራሉ ጽ/ቤት ጉዳዩን እየባሰ ሲሄድ በመስከረም […]

4

የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ እንቅስቃሴዎቹን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ መልዕክት ክቡር መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሀገረ ስብከቱን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የስብከተ ወንጌልን እንቅስቃሴ አስመል ክተው ለኆኅተ ጥበብ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሙሉ ማብራሪያውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ “ማዕረሩሰ ብዙኀ ወገባሩ ኀዳጥ […]

ሙስናና ብልሹ አሠራር እንዲቆም ብፁእ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አሳሰቡ

ብ ፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሚያዝያ 5 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ደቡብ ሀገረ ስብከት በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው የቅዱስ ያሬድ 1500 የልደት በዓል ባከበሩበት ወቅት ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት፡፡ ‹‹ለዛሬው በዓል ያደ ረሰን አምላካችን እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን›› የታላቁን ሊቅ የቅዱስ […]

በሃይማኖት ሽፋን “ተረፈ አይሁዳዊነት በኤልያሳዊነት ስም ሲበቅል”

ሰሞኑን በከተማችን አዲስ አበባ ““የኢትዮጵያ ትንሳኤ ሊያረጋግጥ ኃያል ባለስልጣን ቅዱስ ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቷል፤ የአለም ፍጻሜ ቀርቧል” የሚሉ አካላት ተነስተዋል፡፡ እነሱ እንደሚሉት ነብዩ ኤልያስ መጥቶ አዲስ አበባ ይገኛል፡፡ ቤተመንግሥቱንና ቤተክህነቱን ለማጥራት ተዘጋጅቷል ፡፡ ከሚያጠራቸው የቤተክህነት ጉዳዮችም ሦስቱ ትኩረት አግኝተዋል ይላሉ፡፡ “የመጀመሪያው ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ስህተት ነው ፤ ስማችን ተዋህዶ ነው ፤ መለበስ ያለበት ልብስ ነጭ […]

‹‹ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል›› 1ጴ 4፣8

‹‹ኃጢአት አንዳች የእግዚአብሔር ፀጋ፣ ሰማያዊ በረከት፣ በነፃ የተቸረን የለጋስ አምላክ ሥጦታ የማጣት ትርጉም ያለው ክፉ የመንፈስ ደዌ ነው፡፡ የዘላለሙን አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ዓላማ ለጊዜውም ቢሆን ያደናቀፈ፣ ልዑላዊ ክብር ተችሮት በአምላክ አምሳያ የተፈጠረውን ሰው ያዋረደ፣ የአዳምን ውበት ያጠፋ፣ የሔዋንን ደም ግባት ያረገፈ፣ የልጆቻቸውን ዕድሜ በበርካታ መቶ ዓመታት የቀነሰ ይኸው የሰው ልጆች የዕድሜ ልክ ቀበኛ ‹‹ኃጢአት›› […]

0020

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መሠረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ሥልጠና ተጀመረ

የካቴድራሉ ሠራተኞች ሥልጠናውን ሲከታተሉ በሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በካቴድራሉ አስተዳደር አማካኝነት መሠረታዊ የኮምፒውተር ትምህርት /ሥልጠና በካቴድራሉ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለካቴድራሉ ጽ/ቤት ሠራተኞች እና ለተወሰኑ ማህበረ ካህናት ከመጋቢት 20/07/2005 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጠናው በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የሥልጠናው ዋና አስተባባሪ መ/ር ዘሩ ብርሃኔ እንደተናገሩት፤ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ማስተማር […]

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ዐቢይ ጾምን አስመልክቶ መልእክት አስተላለፉ

                            በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ በየጠረፉ የቆማችኹ፤ በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችኹ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ኾናችኁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤ እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የ2005 ዓ.ም መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችኹ፡፡ ‹‹እብለክሙ በመንፈስ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን