• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

0020

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መሠረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ሥልጠና ተጀመረ

የካቴድራሉ ሠራተኞች ሥልጠናውን ሲከታተሉ በሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በካቴድራሉ አስተዳደር አማካኝነት መሠረታዊ የኮምፒውተር ትምህርት /ሥልጠና በካቴድራሉ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለካቴድራሉ ጽ/ቤት ሠራተኞች እና ለተወሰኑ ማህበረ ካህናት ከመጋቢት 20/07/2005 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጠናው በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የሥልጠናው ዋና አስተባባሪ መ/ር ዘሩ ብርሃኔ እንደተናገሩት፤ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ማስተማር […]

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ዐቢይ ጾምን አስመልክቶ መልእክት አስተላለፉ

                            በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ በየጠረፉ የቆማችኹ፤ በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችኹ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ኾናችኁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤ እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የ2005 ዓ.ም መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችኹ፡፡ ‹‹እብለክሙ በመንፈስ […]

በሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ የአንድነት ጉባኤ መርሃ ግብር ተጀመረ

                                        በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ መጋቢት 8/005 ዓ.ም በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 3.00 ሰዓት ጀምሮ በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሃ ግብር ላይ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የሰሜን እና የምስራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ክቡር መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ […]

m

የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሠራተኞችና በሥራቸው የሚገኙት የገዳማትና አድባራት ሠራተኞች ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ጋር የትውውቅ መርሃ ግብር ተካሄደ

                               በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ የካቲት 29 ቀን 2005 ዓ.ም በጠቅላይ በተ ክህነት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ የትውውቅ መርሃ ግብር ላይ ብፁአን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት፤የ4ቱም አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሥራ አስከያጆችና ሠራተኞች፤የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፤የሰበካ ጉባኤ ም/ሊቃነ መናብርት፤ፀሐፊዎች፤ቁጥጥሮች፤ሒሳብ ሹሞች፤ሰባኪያነ ወንጌሎችና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በትውውቅ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል፡፡ ስብሰባው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርዕሰ […]

d

የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ.የ6ኛው ፓትርያርክ በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ

                                      በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ ብፁእ አቡነ ማትያስ በእስራኤል የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ስድስተኛው የኢትዮጵዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፓትሪያሪክ በመሆን የካቲት 21/2005 ዓ.ም እንደተመረጡ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በዚሁ በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ 806 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ አቡነ ማትያስ 500 ድምፅ በማግኘት ነበር ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት፡፡ በዚሁም መሠረት […]

b

ሰበር ዜና

ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢትየጽያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ስድስተኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ፡፡ ከ806 ድምጽ 500 ውን በማግኘት ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በዚሁም መሠረት:- ብፁዕ አቡነ ማትያስ 500ድምፅ በማግኘት 1ኛ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 98 ድምፅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 98 ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በ70 ድምፅ ድምፅ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ 39 በዚህም መሠረት ብፁዕ […]

z

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

                                              በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ በስመ አብ ወወልድ መንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን   ከስድስተኛው የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ስድስተኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ ከተቋቋመበት እና ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እየሰራ ያለውን ስራዎች ለሚዲያ ተቋማት መግለጫ ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህም ምርጫው በካህናት እና በምዕመናን ዘንድ ግልፅ እንዲሆን ጥረት ተደርጓል፡፡ የካቲት […]

ራሱን ቅዱስ ሲኖዶስ ብሎ የሚጠራው አካል ያወጣውን የሐሰት መግለጫ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

‹‹ኢያስሕቱክሙ አኃዊነ ፍቅራን፤ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ›› ያዕ. 1፡16

ስሕተት በባህርዩ ጎጂና በማናቸውም ጊዜ የማይደገፍ ቢሆንም ከሰው ጋር አብሮ የሚኖር በመሆኑ ሰው ከስሕተት ጸድቶ አያውቅም፤ ስሕተትም ከሰው ጠፍቶ አያውቅም፡፡

ቅዱስ መጽሐፍ ለሰው የሚያስተላልፈው ቋሚ ምክር ሰው ስሕተትን እንዳይፈጽም ነው፣ አውቆም ሆነ ሳያውቅ ስሕተት ከፈጸመ ደግሞ በንሥሐ እንዲመለስ ነው፣ ቅዱስ መጽሐፍ ስሕተት እንዳይፈጸም አጥብቆ ከማስተማሩም በተጨማሪ ስሕተትን በንሥሐ ማሰረዝ የሚያስችል ጸጋ አለው፣ ሰዎች በዚህ ጸጋ እየተጠቀሙ ራሳቸውን ያስተካክላሉ እግዚአብሔርንም ያስደስታሉ፡፡

ሰው በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ፍጹም ተወቃሽ የሚሆነው ስሕተትን በመፈጸሙ ብቻ ሳይሆን ስሕተቱን አምኖ በመቀበል በንሥሐ ለመታረም ዝግጁ ባለመሆኑ ነው፡፡

በክርስቶስ ደም የተመሠረተችና በመንፈስ ቅዱስ ጥበቃ የምትጠበቅ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በሃይማኖቷ በትምህርቷና በሥርዓቷ እንከን የለሽ ቤተ ክርስቲያን ለመሆኗ ዓለም የሚመሰክረው ሐቅ ነው፣ ይሁንና በውስጧ የሚገኙ አገልጋዮች ሰው እንደመሆናቸው መጠን አልፎ አልፎ ስሕተት አይፈጽሙም ማለት አይቻልም፡፡

ከዚህ አንጻር ከዛሬ ሃያ ዓመታት በፊት በቤተክርስቲያናችን ከፍተኛ ባለሥልጣን የተፈጸመውን ቀኖናዊ ስሕተት የዚህ ማሳያ አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡

ለቤተክርስቲያን አገልግሎት በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን የፈጸሙ አባት፣ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5፡198 ላይ ‹‹ወአይደልዎ ለኤጲስ ቆጶስ ከመ ያውድቅ ርእሶ እም ሐራተ ንጉሥ ወይሠየም በምንትኒ እምግብራተ ንጉሥ ወለእመ እጥብዐ ውስተ ዝንቱ ይትፈለጥ እመዓርጊሁ እስመ እግዚእነ ይቤ ኢይክል አሐዱ ገብር ከመ ይትቀነይ ለክልኤ አጋእዝት ወእመ አኮሰ ያምዕዖ ለአሐዱ ወያሠምሮ ለካልኡ›» ፓትርያርክ ራሱን ከክርስቶስ አገልጋይነት ሌላ ለንጉሥ ከሚሠሩ ሥራዎች በማናቸውም ስፍራ መሾም አይገባውም፤ በዚህ ቢገኝ ከሹመቱ ይሻር፣ ጌታችን ‹‹አንድ አገልጋይ ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻለውም፣ አለዚያ ግን አንዱን ያሳዝናል፣ ሌላውንም ደስ ያሰኛል ብሎአልና»፡፡ (ማቴ 6፡24) ተብሎ በቅዱስ ወንጌልና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተከለከለውን የዚህን ዓለም ሹመት ከመንፈሳዊው ሹመት ጋር በማዳበል እየሠሩ የጣሱት ቀኖና ሳያንስ ‹‹ወለእመ ተራድኦ በመኳንንተ ዝንቱ ዓለም ወተሠይመ ለቤተ ክርስቲያን እመኀቤሆሙ ይትመተር ወይሰደድ ውእቱኒ ወኩሎሙ እለ ተሳተፍዎ፣ ማለትም የቤተ ክርስቲያን መሪ በዚህ ዓለም ገዥዎች ጉልበት ለቤተክርስቲያን ቢሾም ይሻር እርሱና ግብረ አበሮቹ ሁሉ ይለዩ›› ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5፡175 የሚለውን ሌላ ቀኖና በድጋሚ በመጣስ የገዥዎችን ኃይል ተጠቅመው ሲኖዶሱን ተጭነውና መንፈስ ቅዱስን ተጋፍተው የፓትርያርክነቱን ሥልጣን ጨበጡ፡፡

በይቀጥላልም ለእግዚአብሔርና ለእውነት ከመታዘዝ ይልቅ ላስመረጣቸውና ለቆሙለት ምድራዊ ባለሥልጣን በማድላት፣ የተዛባ አሠራርን በመከተል፣ እውነትነት የሌለው መልእክትን በማስተላለፍ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለነቀፋ ዳረጉ፣ ሕዝቡንም ቅር አሰኙ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጸሙ እነኚህ ስሕተቶች በቀኖናው ላይ በግልጽ እንደተደነገገው ከሥልጣን የሚያሽሩ ናቸው፡፡ በዚህ ሁሉ

7

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 6ኛውን የፓትሪያርክ ምርጫ የካቲት 21/2005 ዓ.ም እንደምታካሂድ አስታወቀች፡፡

                                              በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ ስድስተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ለማስመረጥ የተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ ከምርጫው ሂደት ጋርና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ በተመለከተ ዛሬ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለጋዜጠኞች ወቅታዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዚሁም መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 6ኛ የፓትሪያሪክ ምርጫ ለማካሄድ ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሠረት ከሊቃነ ዻዻሳት ፣ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰራተኞች ከአድባራትና ገዳማት […]

በምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአጉስታ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰ

                            በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ ማክሰኞ ጥር 14/05/05 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 7.30 ሰዓት ሲሆን መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ቤተ ክርስቲያኑ ሙሉ በሙሉ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ሊደርስ እንደቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡በዚሁ የእሳት ቃጠሎ እጅግ በጣም የሚያስደንቅ እና የሚያስገርም ተአምር ታይቷል፤4ቱም ፅላቶች ከነመጎናፀፊያቸው አንድም የእሳት አደጋ ሳይነካቸው ሊትርፉ እንደቻሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የፅላቶቹም ስም ፡- 1. […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን