• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

2021

የ2007 ዓ.ም.የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ

ሚያዝያ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በጸሎት የተጀመረው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሲካሔድ ቆይቶ ዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ተጠናቅቆ የሚከተለውን መግለጫ ሰጥቷል፡፡በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜንከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫበፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ላይ በተደነገገው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን […]

346

የ2007 ዓ.ም.የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጀመረ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱ-ስ አሐዱ አምላክ አሜን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትምሕረትና ይቅርታ፣ ትዕግሥትና ቸርነት የባህርዩ የሆነ እግዚአብሔር አምላክ፣ ሰፊውን የወርኃ ጾም አገልግሎት በሰላም አስፈጽሞ ብርሃነ ትንሣኤውን በሰላም ስለአሳየን፣ እንደዚሁም ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና ዓመታዊ ከሆነ ከዚህ የረክበ ካህናት ጉባኤ በሰላም ስላደረሰን ክብርና ምስጋና ለእርሱ እናቀርባለን፡፡ ‹‹ኀበ ሀለዉ ክልኤቱ ወሠለስቱ ጉቡአን በስምየ አነ እሄሉ ማእከሌሆሙ […]

00011

በሊቢያ ለተሰዉት ሰማዕታት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት ተካሔደ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የግብጽ አምባሰደር፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ የሰማዕታቱ ቤተሰቦችና ምእመናን በተገኙበት ጸሎተ ፍትሐቱ ተከናውኗል፡፡ቅዱስ ፓትርያርኩ ያስተላለፉትን መልእክት ቀጥሎ እናቀርባለን፡፡በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን!ዘሰ አምነኒ በቅድመ ሰብእ አነኒ አአምኖ በቅድመ አቡነ ዘበሰማያትበሰው […]

346

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2007 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

346

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በእንተ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡
– በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
– ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
– የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
– በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
– እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤
በሞትና በመቃብር ላይ ሥልጣን ያለው ኃያሉና አሸናፊው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ ፡፡
‹‹ወበከመ በእንተ አዳም ኵልነ ንመውት ከማሁ በክርስቶስ ኵልነ ነሐዩ፤ ሁላችን በአዳም እንደምንሞት እንደዚሁም ሁላችን በክርስቶስ ሕያዋን እንሆናለን›› (1ቆሮ. 15÷22)፡፡
እዚህ ላይ በተገለፀው ቃለ እግዚአብሔር መሠረት የሰዎች መጻኢና የመጨረሻ ዕድል ከሁለት አዳማዊ ውርስ ጋር የተያያዘ ሆኖ ይገኛል ፡፡
በቅዱስ መጽሐፍ በግልጽ እንደተጻፈው ሰው ሁሉ ከቀዳማዊ አዳም በሥጋ ተወልዶአል፤ የእርሱ የሆነውንም ሁሉ ወርሶአል፤ይህም ማለት በሥጋው በኩል የግብረ ኃጢአት ዝንባሌን፣ ሞተ ሥጋን፣ ወሪደ መቃብርን፣ በመቃብር ውስጥ መበስበስንና መፍረስን ሲወርስ በነፍሱ በኩል ደግሞ ከእግዚአብሔር መለየትን፣ በኃጢአት ተሸንፎ የዲያብሎስ ሎሌ መሆንን፣ በኃጢአቱ ምክንያት ለኵነኔ ሲኦል ተጋላጭ መሆንን እና የመሳሰሉትን ሁሉ ወርሶአል ማለት ነው፡፡
ጠቅለል አድርገን ስናየው ቀዳማዊ አዳም በሥጋና በነፍስ ከባድ ውድቀትን ለልጆቹ አውርሶአል ማለት ነው ፡፡
ከቀዳማዊ አዳም የውድቀት ዘመን ጀምሮ

00030

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የ2007 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

ሊ/ማ/ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአ/ አ/ ሀ/ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡እንኳን ለ2007 ዓ.ም የጌታችን፤የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው መታሰቢያ በዓል ሁላችንንም ጠብቆ አደረሰን አደረሳችሁ በማለት በራሴና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስም መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡ የጌታችን ትንሣኤ የሰው ልጆች ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገሩበት በመሆኑ የሁሉም የሰው […]

233

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከግብፁ ፕሬዚዳንት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ

የሕዳሴ ግድብን መሠረት በማድረግ የስምምነት ፊርማ ሱዳን ላይ አድርገው ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ሀገራችን የመጡትና ከሀገራችን ከፍተኛ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ስለ አጠቃላይ የጋራ እሴቶችና የጋር ጥቅሞች አብሮ ተባብሮ ማሳደግ ስለሚቻልበት ሁኔታ እጅግ መልካም በሆነ ሁኔታ ሲነጋገሩና ስምምነት ላይ የደረሱትን የግብፁ ፕሬዚዳንት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ […]

ጾምን ለዩ ምህላውንም በዚህ ቀን ይሁን ብላችሁ አዋጅ ንገሩ ፣አለቆችንም ሰብስቧቸው፤ ከፈጣሪችን ከእግዚአብሔር ማደሪያ የሚኖረውንም ሰ ብ ስ ቡ ት ፣ ሁላችሁም አንድነት ሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ለምኑ፡፡ ኢዩ 2÷15

ሙሉ የኆኀተ ጥበብ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሔትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ (‹‹የመጋቢት 2007 ዓ.ም ኆኀተ ጥበብ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሔት››)

00030

የአ/አ/ሀ/ስ/ ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈ ስቅዱስ ከሀገረ ስብከቱና ከክፍለ ከተማ ሠራተኞች ጋር በጋራ ሥራ ለመሥራት በሚያስችል ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄዱ

በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል በሚችል ሁኔታ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱና እንዲሁም በገዳማትና አድባራት ልብሰ  ተክህኖ በለበሱ ካህናትና ልዩ ልዩ ሠራተኞች እጅግ በጣም ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈ ስቅዱስ ከ2 ቀናት በኋላ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ከ7ቱም ክፍላተ ከተማ መላው ሠራተኞች ጋር መጋቢት 18/2007 ዓ.ም በሀገረ […]

0010

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ካህናት አዲስ ለተመደቡት ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቀባበል አደረጉ!!!

በመናገሻ  ገነተ ጽጌ  ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ  በዋና ጸሐፊነት ሲያገለግሉ የነበሩት ሊቀ ማእምራን የማነ ብርሃን ዘመንፈሰ ቅዱስ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ  የሊቃውንት ጉባኤ አባል በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት መጋቤ ብሉይ  አእመረ አሸብር  ምክትል ሥራ አስኪያጅ በመሆን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተመድበዋል፡፡  አዲስ የተመደቡት ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጁ  ዛሬ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም  ከጠዋቱ […]

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ገዳማትና አድባራት አዲስ ለሚቀጠሩ የአብነት መምህራን ውድድር ተካሄደ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሥሩ ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት የአብነት መምህራንን አወዳድሮ ለመቅጠር ባወጣው መርሐ ግብር መሰረት ፈተናውን ያለፉ መምህራን 32 መሆናቸው ተገጸ፡፡በሀገረ ስብከቱ የትምህርት ክፍል ዋና ክፍል ኃላፊ ሊቀ ማዕምራን ብርሃነ መስቀል ገበየሁን ጠይቀን እንደተረዳነው እነዚህ መምህራን በድጓ፣ በቅዳሴ ፣ በአቋቋም፣ በቅኔ፣ በዝማሬ መዋሥዕት፣ በብሉያት እና በሐዲሳት ተወዳድረው የተሻለ ውጤት በማምጣታቸው ነው ያለፉት በማለት ተናግረዋል፡፡አያይዘውም […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት