በአ/አ/ ሀገረ ስብከት በመዋቅርና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ ሰነድ ላይ ለ2 ቀናት ሲካሄድ የቆየውን የመጀመሪያ ዙር የውይይት መርሃ ግብር ተጠናቀቀNovember 28, 2013 በሀገረ ስብከቱ አይቲና ዶክሜንቴሽን ክፍል ህዳር 17 እና 18/2006 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፤የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎች፤የሀገረ ሰብከቱ የዋና ክፍል እና ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት ለ2 ሙሉ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መልካም የሥራ ጅምር የሆነውን የሀገረ ስብከቱ መዋቅራዊና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ ሰነድ ላይ ለአዘጋጆችና አቅራቢ ባለሞያዎች […] Read more https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/0006.jpg 480 640 tc https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png tc2013-11-28 04:27:342023-11-09 10:25:59በአ/አ/ ሀገረ ስብከት በመዋቅርና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ ሰነድ ላይ ለ2 ቀናት ሲካሄድ የቆየውን የመጀመሪያ ዙር የውይይት መርሃ ግብር ተጠናቀቀ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የነበርውን የመልካም አስተዳደር እና የፋይናንስ ችግር ሙሉ በሙሉ ይፈታል በተባለው መዋቅርዊ የአሠራር ለውጥ እና አደረጃጀት ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ነውNovember 26, 2013ቀደም ብለን በድህረ ገፃችን ስናሰራጭ እንደቆየነው ሀገረ ስብከቱ ከሚያዘያ 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአሠራር ለውጥ ውስጥ የቆየ ሲሆን በዚህም መነሻነት ሀገረ ስብከቱ በቃለ ዓዋዲው መሠረት በ7 ወረዳ/ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ተዋቅሮ ለ3 ወራት የሚያገለግል ጊዚያዊ ውስጠ ደንብ ከመዘጋጀቱም በላይ ከሀገረ ስብከቱ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረስ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን አዲሱ […] Read more https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/0014.jpg 480 640 tc https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png tc2013-11-26 15:14:342023-11-09 10:25:59በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የነበርውን የመልካም አስተዳደር እና የፋይናንስ ችግር ሙሉ በሙሉ ይፈታል በተባለው መዋቅርዊ የአሠራር ለውጥ እና አደረጃጀት ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው
በአ/ሀ/ስ/የአራዳ ጉለሌ ክ/ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት በወረዳው ስለ ተሠሩ ሥራዎች ሪፖርት አቀረበNovember 24, 2013 ሪፖርት – ብፁዕ አባታችን አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት እና የጅማ ሀገረ ስብከተ ሊቀ ጳጳስ – ክቡር ንቡረ ዕድ አባ ዮሐንስ ገ/ሕይወት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ – ክቡራን የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች – ክቡራን የአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እና የልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች ቸሩ አምላካችን እና አባታችን ሕይወታችንን በቸርነቱ ጠብቆ፣ ሥራችንን ባርኮ እና ቀድሶ ለዚህች ሰዓት ስለአደረሰን ክብርና ምስጋና ለስመ አጠራሩ ይሁንልን አሜን:: ማዕረሩ ብዙህ በገባሩኒ ህዳጥ ሰአልዎ እንከ ለበዐለ ከመይወስክ ገባዕተ ለማዕረሩ (ማቴ. 9፡37) መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመንግሥተ እግዚአብሔርን ወንጌል በሚአስፋፋበት ወቅት በየምኩራቡ በመሄድ የእግዚአብሔርን መንግሥት መልካም ዜና እያበሠረ ሕዝቡን ከበሽታ እና ከደዌ እየፈወሰ ህዝቡ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀው እና ተቅበዝብዘው፣ ረዳት አጥተው ባያቸው ጊዜ ራራላቸው እና ከአጠገቡ ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን መከሩ ብዙ ነው የመከሩ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው የመከሩ ባለቤት ተጨማሪ ሠራተኞችን እንዲልክ ለምኑት በማለት ጥበብ የተሞላበትን መልእክት አስተላልፏል፡፡ የሥራ ጀማሪ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይናገራል “አባቴ እስከ አሁን እየሠራ ነው እኔም ደግሞ እሠራለሁ” (ዮሐ. 5፡17) ዛሬም ቢሆን እግዚአብሔር ሥራውን አላቋረጠም፡፡ እኛም ደግሞ ከእርሱ ልንማር ይገባናል፡፡ (ማቴ. 11፡28) አምላካችን እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ለሥራ እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወስዶ እንዲአለማት እና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት በኤደን የአትክልት ቦታ አስቀመጠው (ዘፍ. 2፡15) ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በበኩሉ ስለ ሥራ አስፈላጊነት ሲናገር ሊሠራ የማይወድ አይብላ በማለት ተናግሯል፡፡ (2ተሰ 3፡8) በዚህ ሕገ እግዚአብሔር መሠረት የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዕቅድ አውጥቶ ተገቢውን ሁለገብ የሥራ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ የክፍለ ከተማ ቤተክህታችን የተመሠረተው ከሐምሌ 24 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን Read more https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/b003.jpg 480 640 tc https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png tc2013-11-24 13:27:542023-11-09 10:25:59በአ/ሀ/ስ/የአራዳ ጉለሌ ክ/ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት በወረዳው ስለ ተሠሩ ሥራዎች ሪፖርት አቀረበ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአዲሱ መዋቅርዊ የአሠራር ለውጥ እና አደረጃጀት ላይ ውይይት ሊካሄድ ነውNovember 24, 2013አዲሱ የሀገረ ስብከቱ መዋቅራዊ የአሠራር ለውጥና አደረጃጀት እጅግ ከፍትኛ ልምድ ባላቸው የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2006 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ቀርቦ ከታዬ በኋላ ለሀገረ ስብከቱ ያለው ጠቃሚነት እጅግ የላቀ መሆኑን ስለታመነበት የሚመለከታቸው አካላት ውውይት አድርገውበት በቋሚ ሲኖዶስ እንዲፀድቅ በተወሰነው መሠረት የመጀመሪያው ዙር ውውይት ህዳር 17 እና 18/2006 ለሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎች፤ የክፍል […] Read more https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/640.jpg 480 640 tc https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png tc2013-11-24 12:47:222023-11-09 10:25:59በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአዲሱ መዋቅርዊ የአሠራር ለውጥ እና አደረጃጀት ላይ ውይይት ሊካሄድ ነው
እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓለ በሰላም አደረሰን አደሳችሁ!November 22, 2013 በዚህች ቀን የሰማይ ሰራዊት ሁሉ አለቃቸው መልአከ ምክሩ የምክሩ አበጋዝ ይለዋል የቅድስት ሥላሴ መንጦላእትን የሚከፍትና የሚዘጋ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ቀን ነው። በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡(ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡) የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ አለ “በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱም ዘንዶውን ተዋጉት፥ ዘንዶውም አልቻላቸውም፥ ከዚያም በኋላ በሰማይ ቦታ አልተገኘለትም። ራእ 12፤7 ነብዩ ዳንኤልም እንዲህ አለ “በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” ዳን ፲፪፥፩። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን“ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡ እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው”መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡ በመጽሐፈ ዳንኤል ”እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ” (ዳን 10፤13) የሚለውን ቃል ስናነብ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ቀና መንገድ ላይ የሚጓዙትን፤ በእምነት የጸኑትን ሊረዳ እንደሚፋጠን እንገነዘባለን። በመጽሐፈ ዘካሪያስም እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን ”የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ። ” (ዘካ 1፤12) መልአኩ ይህንን ልመና በእግዚአብሔር ፊት ያቀረበው እስራኤላውያን በበደላቸው ምክንያት ለግዞት ተላልፈው በተሰጡበት ዘመን መሆኑ ልመናውን ልዩ ያደርገዋል። በበደላቸው ጊዜ፤ በደከሙና በግዞት በወደቁ ጊዜ መልአኩ ስለእነርሱ በእግዚአብሔር ፊት እንደቆመ ማስተዋል የመላእክትን ተራድኦ ያመላክታል። እግዚአብሔር አምላክም ይህንን በሐዘን የቀረበ የመልአኩን ልመና ተቀብሎ ለእስራኤላውያን የምሕረት ፊቱን እንደመለሰላቸው እናነባለን ”ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፤ ቤቴ ይሠራባታል፤ . . . ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።” (ዘካ 1፤17) Read more https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/0337.jpg 599 461 tc https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png tc2013-11-22 09:28:232023-11-09 10:25:59እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓለ በሰላም አደረሰን አደሳችሁ!
የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ በአሜሪካ ሐዋርያዊ ጉዞ አደረጉNovember 22, 2013ቅደስነታቸው በአሜሪካ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ከበርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያት ጋር ውይይት አካሒደዋል ፡፡ ብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ ቀዲማዊ ፓትርያርክ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት በዓለም ላይ የፖለቲካና የሃይማኖት ልዩነት ተፈጥሮአዊ በመሆኑ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሁሉም በጋራ እንዲሠሩ ጠይቀዋል ፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩና ተከታዮቻቸው በአሜሪካ በተለያዩ ክፍላተ ሀገር በመዘዋወር ስለ አንድነት፣ ሰላምና ትብብር ከኢትዮጵያውያኑ ጋር ውይይት አድርገዋል ፡፡ በአንድ […] Read more https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/0336.jpg 266 400 tc https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png tc2013-11-22 05:23:402023-11-09 10:25:59የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ በአሜሪካ ሐዋርያዊ ጉዞ አደረጉ
የ2006 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀNovember 1, 2013ጉባኤው ከጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 10 ቀናት ተወያይቶ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አስመልክቶ ጥቅምት21/2006 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን […] Read more https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/2021.jpg 425 640 tc https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png tc2013-11-01 11:50:152023-11-09 10:25:59የ2006 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ
32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ተጠናቀቀNovember 1, 2013ለተጨማሪ ንባብ እዚህ ላይ ይጫኑ (ሙሉ የአቋም መግለጫና ቃለ ገባኤ) {flike}{plusone} Read more https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png 0 0 tc https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png tc2013-11-01 11:38:162023-11-09 10:25:5932ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ተጠናቀቀ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት በሥሩ ካሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በልማት ዙሪያ ውይይት አካሄደOctober 17, 2013መስከረም 29/1/06 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ሥር ከሚገኙ አስተዳዳሪዎች፤ ፀሐፊዎች፤ቁጥጥሮች፤ሒሳብ ሹሞችና ሰባክያነ ወንጌል ጋራ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በዚሁ ስብሰባ ላይ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እና የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል፡፡ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ ስለ ክፍለ ከተማው አስመልክተው ሰፊ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በልማትና በመልካም አስተዳደር እንዲሁም […] Read more https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/0004.jpg 480 640 tc https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png tc2013-10-17 16:31:582023-11-09 10:25:59በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት በሥሩ ካሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በልማት ዙሪያ ውይይት አካሄደ
32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው፡፡October 16, 201332ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተጀምሯል፡፡ በመደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ የየሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ ሰንበት […] Read more https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/h002.jpg 324 600 tc https://eotc-aa.org/a/wp-content/uploads/logo_am-2.png tc2013-10-16 15:23:032023-11-09 10:25:5932ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በአ/አ/ ሀገረ ስብከት በመዋቅርና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ ሰነድ ላይ ለ2 ቀናት ሲካሄድ የቆየውን የመጀመሪያ ዙር የውይይት መርሃ ግብር ተጠናቀቀ
በሀገረ ስብከቱ አይቲና ዶክሜንቴሽን ክፍል ህዳር 17 እና 18/2006 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፤የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎች፤የሀገረ ሰብከቱ የዋና ክፍል እና ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት ለ2 ሙሉ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መልካም የሥራ ጅምር የሆነውን የሀገረ ስብከቱ መዋቅራዊና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ ሰነድ ላይ ለአዘጋጆችና አቅራቢ ባለሞያዎች […]
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የነበርውን የመልካም አስተዳደር እና የፋይናንስ ችግር ሙሉ በሙሉ ይፈታል በተባለው መዋቅርዊ የአሠራር ለውጥ እና አደረጃጀት ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው
ቀደም ብለን በድህረ ገፃችን ስናሰራጭ እንደቆየነው ሀገረ ስብከቱ ከሚያዘያ 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአሠራር ለውጥ ውስጥ የቆየ ሲሆን በዚህም መነሻነት ሀገረ ስብከቱ በቃለ ዓዋዲው መሠረት በ7 ወረዳ/ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ተዋቅሮ ለ3 ወራት የሚያገለግል ጊዚያዊ ውስጠ ደንብ ከመዘጋጀቱም በላይ ከሀገረ ስብከቱ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረስ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን አዲሱ […]
በአ/ሀ/ስ/የአራዳ ጉለሌ ክ/ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት በወረዳው ስለ ተሠሩ ሥራዎች ሪፖርት አቀረበ
ሪፖርት
– ብፁዕ አባታችን አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት እና የጅማ ሀገረ ስብከተ ሊቀ ጳጳስ
– ክቡር ንቡረ ዕድ አባ ዮሐንስ ገ/ሕይወት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ – ክቡራን የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች
– ክቡራን የአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እና የልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች
ቸሩ አምላካችን እና አባታችን ሕይወታችንን በቸርነቱ ጠብቆ፣ ሥራችንን ባርኮ እና ቀድሶ ለዚህች ሰዓት ስለአደረሰን ክብርና ምስጋና ለስመ አጠራሩ ይሁንልን አሜን::
ማዕረሩ ብዙህ በገባሩኒ ህዳጥ ሰአልዎ እንከ ለበዐለ ከመይወስክ ገባዕተ ለማዕረሩ (ማቴ. 9፡37) መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመንግሥተ እግዚአብሔርን ወንጌል በሚአስፋፋበት ወቅት በየምኩራቡ በመሄድ የእግዚአብሔርን መንግሥት መልካም ዜና እያበሠረ ሕዝቡን ከበሽታ እና ከደዌ እየፈወሰ ህዝቡ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀው እና ተቅበዝብዘው፣ ረዳት አጥተው ባያቸው ጊዜ ራራላቸው እና ከአጠገቡ ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን መከሩ ብዙ ነው የመከሩ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው የመከሩ ባለቤት ተጨማሪ ሠራተኞችን እንዲልክ ለምኑት በማለት ጥበብ የተሞላበትን መልእክት አስተላልፏል፡፡
የሥራ ጀማሪ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይናገራል “አባቴ እስከ አሁን እየሠራ ነው እኔም ደግሞ እሠራለሁ” (ዮሐ. 5፡17) ዛሬም ቢሆን እግዚአብሔር ሥራውን አላቋረጠም፡፡ እኛም ደግሞ ከእርሱ ልንማር ይገባናል፡፡ (ማቴ. 11፡28) አምላካችን እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ለሥራ እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወስዶ እንዲአለማት እና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት በኤደን የአትክልት ቦታ አስቀመጠው (ዘፍ. 2፡15) ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በበኩሉ ስለ ሥራ አስፈላጊነት ሲናገር ሊሠራ የማይወድ አይብላ በማለት ተናግሯል፡፡ (2ተሰ 3፡8) በዚህ ሕገ እግዚአብሔር መሠረት የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዕቅድ አውጥቶ ተገቢውን ሁለገብ የሥራ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
የክፍለ ከተማ ቤተክህታችን የተመሠረተው ከሐምሌ 24 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአዲሱ መዋቅርዊ የአሠራር ለውጥ እና አደረጃጀት ላይ ውይይት ሊካሄድ ነው
አዲሱ የሀገረ ስብከቱ መዋቅራዊ የአሠራር ለውጥና አደረጃጀት እጅግ ከፍትኛ ልምድ ባላቸው የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2006 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ቀርቦ ከታዬ በኋላ ለሀገረ ስብከቱ ያለው ጠቃሚነት እጅግ የላቀ መሆኑን ስለታመነበት የሚመለከታቸው አካላት ውውይት አድርገውበት በቋሚ ሲኖዶስ እንዲፀድቅ በተወሰነው መሠረት የመጀመሪያው ዙር ውውይት ህዳር 17 እና 18/2006 ለሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎች፤ የክፍል […]
እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓለ በሰላም አደረሰን አደሳችሁ!
በዚህች ቀን የሰማይ ሰራዊት ሁሉ አለቃቸው መልአከ ምክሩ የምክሩ አበጋዝ ይለዋል የቅድስት ሥላሴ መንጦላእትን የሚከፍትና የሚዘጋ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ቀን ነው። በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡(ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡)
የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ አለ “በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱም ዘንዶውን ተዋጉት፥ ዘንዶውም አልቻላቸውም፥ ከዚያም በኋላ በሰማይ ቦታ አልተገኘለትም። ራእ 12፤7 ነብዩ ዳንኤልም እንዲህ አለ “በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” ዳን ፲፪፥፩።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን“ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡ እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው”መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡
በመጽሐፈ ዳንኤል ”እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ” (ዳን 10፤13) የሚለውን ቃል ስናነብ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ቀና መንገድ ላይ የሚጓዙትን፤ በእምነት የጸኑትን ሊረዳ እንደሚፋጠን እንገነዘባለን።
በመጽሐፈ ዘካሪያስም እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን ”የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ። ” (ዘካ 1፤12) መልአኩ ይህንን ልመና በእግዚአብሔር ፊት ያቀረበው እስራኤላውያን በበደላቸው ምክንያት ለግዞት ተላልፈው በተሰጡበት ዘመን መሆኑ ልመናውን ልዩ ያደርገዋል። በበደላቸው ጊዜ፤ በደከሙና በግዞት በወደቁ ጊዜ መልአኩ ስለእነርሱ በእግዚአብሔር ፊት እንደቆመ ማስተዋል የመላእክትን ተራድኦ ያመላክታል። እግዚአብሔር አምላክም ይህንን በሐዘን የቀረበ የመልአኩን ልመና ተቀብሎ ለእስራኤላውያን የምሕረት ፊቱን እንደመለሰላቸው እናነባለን ”ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፤ ቤቴ ይሠራባታል፤ . . . ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።” (ዘካ 1፤17)
የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ በአሜሪካ ሐዋርያዊ ጉዞ አደረጉ
ቅደስነታቸው በአሜሪካ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ከበርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያት ጋር ውይይት አካሒደዋል ፡፡ ብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ ቀዲማዊ ፓትርያርክ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት በዓለም ላይ የፖለቲካና የሃይማኖት ልዩነት ተፈጥሮአዊ በመሆኑ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሁሉም በጋራ እንዲሠሩ ጠይቀዋል ፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩና ተከታዮቻቸው በአሜሪካ በተለያዩ ክፍላተ ሀገር በመዘዋወር ስለ አንድነት፣ ሰላምና ትብብር ከኢትዮጵያውያኑ ጋር ውይይት አድርገዋል ፡፡ በአንድ […]
የ2006 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ
ጉባኤው ከጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 10 ቀናት ተወያይቶ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አስመልክቶ ጥቅምት21/2006 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን […]
32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ተጠናቀቀ
ለተጨማሪ ንባብ እዚህ ላይ ይጫኑ (ሙሉ የአቋም መግለጫና ቃለ ገባኤ) {flike}{plusone}
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት በሥሩ ካሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በልማት ዙሪያ ውይይት አካሄደ
መስከረም 29/1/06 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ሥር ከሚገኙ አስተዳዳሪዎች፤ ፀሐፊዎች፤ቁጥጥሮች፤ሒሳብ ሹሞችና ሰባክያነ ወንጌል ጋራ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በዚሁ ስብሰባ ላይ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እና የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል፡፡ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ ስለ ክፍለ ከተማው አስመልክተው ሰፊ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በልማትና በመልካም አስተዳደር እንዲሁም […]
32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተጀምሯል፡፡ በመደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ የየሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ ሰንበት […]