• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

በለቡ መብራት ኃይል አደባባይ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በለቡ መብራይት ኃይል አደባባይ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በባሕረ ጥምቀቱ እጅግ በርካታ ምእመናን ከዋዜማው ጀምሮ በስፍራው የተገኙ ሲሆን በዓሉ ሌሊት በማኅሌት ደምቆ አድሮ ንጋት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴውን ተከናውኖ በመልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ይርጋ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥተዋል። የምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት […]

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጥምቀት በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል!

በተለምዶ መሿኪያ ተብሎ በሚጠራው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት አከባቢ በሚገኘው የታቦት ማደሪያ ስፍራ ከአስራ ሰባት አድባራትና ገዳማት የወጡ ታቦታት አድረዋል። እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ምእመናን ከዋዜማው ጀምሮ በስፍራው ተገኝተው ሌሊት ማኅሌቱን፣ ንጋት ላይ ደግሞ ሥርዓተ ቅዳሴውንና ትምህርተ ወንጌል ተከታትለዋል። ከቅዳሴው መርሐግብር በኋላ በመ/ሃ ተስፋዬ ሞሲሳ በዓሉን የተመለከተ ሰፊ ትምህርት ተሰጥቷል። በዓሉ ትህትና የተፈጸመበት፣ ምሥጢረ […]

ዛሬ የነጻነታችን ቀን ነው……..ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

ዛሬ በጃን ሜዳ በድምቀት እየተከበረ ባለው የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በዓል ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የበዓሉ መሰረቱ የእዳ ደብዳቤ እንደሆነ ገልጸው ይሄንን የተመለከተ ሰፊ ትምህርት ስጥተዋል። ይህ እዳ ደብዳቤ ተቀዶ ነጻነታችን የታወጀበት የነጻነታችን ቀን ነው ሲሉ በተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ በሚል ቃለ ወንጌል መነሻ አስደግፈው በዓሉን […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይሜኖት ወልዱ የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማሕበር ጎበኙ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይሜኖት ወልዱ በሽሮ ሜዳ ቁስቋም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚገኘው የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማሕበር ጎብኝተዋል። ክቡር ዋና ሥራ አስኪያጁ ተቋሙን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢጎድል ምን ይጠቅመዋል?” ማቴ 16፥26 የሚል የእግዚአብሔር ቃል መነሻ አድርገው አስተምረዋል። የሰው ልጅ […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ!

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጥምቀት አስመልክተው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ። በዓሉን ስናከብር “የበዓሉን መንፈሳዊ ጭብጥ መልእክት” ከልብ በመረዳትና በመገንዘብ መሆን እንዳለበት ብፁዕነታቸው አሳስበዋል። ሐዋርያው የተናገረውን ” …ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን፤ ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን […]

በዓለ አስተርእዮ

አስተርእዮ፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ አስተርእዮ ማለትም መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው፡፡ በግሪክ ቋንቋ ኤጲፋንያ ይባላል ኤጲፋንያ ማለት መገለጥ፤ መታየት ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ዘመን ዘመነ አስተርእዮ ይባላል የመገለጥ፣ የመታየት ዘመን ማለት ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ሰው ሆኖ የተገለጠበት ዘመን ስለሆነ እና እንዲሁም በጥምቀቱ አንድነቱን ሦስትነቱን […]

የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ተጠናቆ ለበዓል አከባበር ሥርዓቱ ዝግጁ ሆነ

ከአንድ ወር በፊት የ2014 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን በማስመልከት በዘመናት አገልግሎት ምክንያት በእጅጉ ተጎሳቁሎ የነበረውን የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀትን ለማደስ በተደረገው እንቅስቃሴ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔና በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አሳሳቢነት የግንባታ ሥራው የተጀመረው የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ መጠናቀቁና ለጥምቀት በዓል ዝግጁ መሆኑ ታውቋል። በምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል የባህረ ጥምቀቱን ገንዳ በአዲስና […]

የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፥ ሊቃውንተ ቤተ ክስርስቲያንና በርካታ ምእመናን በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል  በድምቀት ተከብሮ ውሏል። በዓውደ ምሕረት መርሐ ግብሩ “ዮም መላእክት ይዬብቡ ወሊቃነ መላእክት ይዜምሩ፤ እስመ መድኅን መጽአ ውስተ ዓለም ለቢሶ ሥጋነ”የሚል ያሬዳዊ ወረብ በሊቃውንት ሲቀርብ፤ በካቴድራሉ ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ወይቤላ አብ ለማርያም አምጣንየ አምጣነኪ አዝማንየ አዝማነኪ […]

የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 15,000,000 ብር የሚገመት የአልባሳት፣ የአስቤዛ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ!

የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት አብያተክርስቲያናትን በማስተባበር 15,000,000 ብር የሚገመት የአልባሳት፣ የአስቤዛ እና የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍን በማሰባሰብ በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች ዕርዳታ አደረገ። የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ብ ሩፋኤል የማነብርሃን የዕርዳታውን ዓላማ እና አሰባሰብ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የዕርዳታው ዋና ዓላማ በሀገራችን በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ከሞቀ ቤታቸውና ከቀያቸው ለተፈናቀሉ እና ለተጎዱ ወገኖች የሚውል […]

የኢትዮጵያና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤያት የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ !!!

በምሥራቅ አፍሪካ የቀጠናውን የሰላምና የመከባበር ዕሴት ለመገንባት እንዲሁም ጽንፈኝነትን ለመከላከል የሚያስችል የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ። ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና የኬንያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ናቸው። ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላትና የኬንያ የተቋሙ ዳይሬክተርና ዋና ጸሐፊ ተፈራርመዋል። በስምምነቱ ወቅት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ጉባኤው በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ከሚገኙ የሃይማኖት ተቋማትና […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን