• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

4

የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ እንቅስቃሴዎቹን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ መልዕክት ክቡር መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሀገረ ስብከቱን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የስብከተ ወንጌልን እንቅስቃሴ አስመል ክተው ለኆኅተ ጥበብ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሙሉ ማብራሪያውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ “ማዕረሩሰ ብዙኀ ወገባሩ ኀዳጥ […]

ሙስናና ብልሹ አሠራር እንዲቆም ብፁእ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አሳሰቡ

ብ ፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሚያዝያ 5 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ደቡብ ሀገረ ስብከት በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው የቅዱስ ያሬድ 1500 የልደት በዓል ባከበሩበት ወቅት ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት፡፡ ‹‹ለዛሬው በዓል ያደ ረሰን አምላካችን እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን›› የታላቁን ሊቅ የቅዱስ […]

በሃይማኖት ሽፋን “ተረፈ አይሁዳዊነት በኤልያሳዊነት ስም ሲበቅል”

ሰሞኑን በከተማችን አዲስ አበባ ““የኢትዮጵያ ትንሳኤ ሊያረጋግጥ ኃያል ባለስልጣን ቅዱስ ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቷል፤ የአለም ፍጻሜ ቀርቧል” የሚሉ አካላት ተነስተዋል፡፡ እነሱ እንደሚሉት ነብዩ ኤልያስ መጥቶ አዲስ አበባ ይገኛል፡፡ ቤተመንግሥቱንና ቤተክህነቱን ለማጥራት ተዘጋጅቷል ፡፡ ከሚያጠራቸው የቤተክህነት ጉዳዮችም ሦስቱ ትኩረት አግኝተዋል ይላሉ፡፡ “የመጀመሪያው ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ስህተት ነው ፤ ስማችን ተዋህዶ ነው ፤ መለበስ ያለበት ልብስ ነጭ […]

‹‹ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል›› 1ጴ 4፣8

‹‹ኃጢአት አንዳች የእግዚአብሔር ፀጋ፣ ሰማያዊ በረከት፣ በነፃ የተቸረን የለጋስ አምላክ ሥጦታ የማጣት ትርጉም ያለው ክፉ የመንፈስ ደዌ ነው፡፡ የዘላለሙን አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ዓላማ ለጊዜውም ቢሆን ያደናቀፈ፣ ልዑላዊ ክብር ተችሮት በአምላክ አምሳያ የተፈጠረውን ሰው ያዋረደ፣ የአዳምን ውበት ያጠፋ፣ የሔዋንን ደም ግባት ያረገፈ፣ የልጆቻቸውን ዕድሜ በበርካታ መቶ ዓመታት የቀነሰ ይኸው የሰው ልጆች የዕድሜ ልክ ቀበኛ ‹‹ኃጢአት›› […]

0020

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መሠረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ሥልጠና ተጀመረ

የካቴድራሉ ሠራተኞች ሥልጠናውን ሲከታተሉ በሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በካቴድራሉ አስተዳደር አማካኝነት መሠረታዊ የኮምፒውተር ትምህርት /ሥልጠና በካቴድራሉ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለካቴድራሉ ጽ/ቤት ሠራተኞች እና ለተወሰኑ ማህበረ ካህናት ከመጋቢት 20/07/2005 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጠናው በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የሥልጠናው ዋና አስተባባሪ መ/ር ዘሩ ብርሃኔ እንደተናገሩት፤ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ማስተማር […]

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ዐቢይ ጾምን አስመልክቶ መልእክት አስተላለፉ

                            በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ በየጠረፉ የቆማችኹ፤ በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችኹ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ኾናችኁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤ እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የ2005 ዓ.ም መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችኹ፡፡ ‹‹እብለክሙ በመንፈስ […]

በሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ የአንድነት ጉባኤ መርሃ ግብር ተጀመረ

                                        በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ መጋቢት 8/005 ዓ.ም በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 3.00 ሰዓት ጀምሮ በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሃ ግብር ላይ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የሰሜን እና የምስራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ክቡር መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ […]

m

የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሠራተኞችና በሥራቸው የሚገኙት የገዳማትና አድባራት ሠራተኞች ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ጋር የትውውቅ መርሃ ግብር ተካሄደ

                               በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ የካቲት 29 ቀን 2005 ዓ.ም በጠቅላይ በተ ክህነት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ የትውውቅ መርሃ ግብር ላይ ብፁአን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት፤የ4ቱም አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሥራ አስከያጆችና ሠራተኞች፤የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፤የሰበካ ጉባኤ ም/ሊቃነ መናብርት፤ፀሐፊዎች፤ቁጥጥሮች፤ሒሳብ ሹሞች፤ሰባኪያነ ወንጌሎችና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በትውውቅ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል፡፡ ስብሰባው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርዕሰ […]

d

የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ.የ6ኛው ፓትርያርክ በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ

                                      በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ኃይሉ ብፁእ አቡነ ማትያስ በእስራኤል የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ስድስተኛው የኢትዮጵዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፓትሪያሪክ በመሆን የካቲት 21/2005 ዓ.ም እንደተመረጡ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በዚሁ በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ 806 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ አቡነ ማትያስ 500 ድምፅ በማግኘት ነበር ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት፡፡ በዚሁም መሠረት […]

b

ሰበር ዜና

ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢትየጽያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ስድስተኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ፡፡ ከ806 ድምጽ 500 ውን በማግኘት ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በዚሁም መሠረት:- ብፁዕ አቡነ ማትያስ 500ድምፅ በማግኘት 1ኛ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 98 ድምፅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 98 ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በ70 ድምፅ ድምፅ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ 39 በዚህም መሠረት ብፁዕ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት