• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

2527

የአቃቂ ቃሊቲ እና የልደታ ክፍላተ ከተሞች አድባራት እና ገዳማት ተወካዮች በመዋቅራዊ ረቂቅ ሰነድ ዙሪያ ላይ ውይይት አካሄዱ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአቃቂ እና ልደታ ክፍላተ ከተሞች ሥር የሚገኙ የአድባራት እና የገዳማት ተወካዮች በመዋቅራዊ ረቂቅ ሰነድ ዙሪያ ለመወያየት ዛሬ አርብ ታህሳስ 11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በስብከተ ወንጌል አዳራሽ የተገኙ ሲሆን ከሁለቱም ክፍላተ ከተሞች ከሚገኙ ከ30 ያላነሱ አድባራት እና ገዳማት ብዛታቸው 480 የሚደርስ  ተሰብሳቢዎች ተገኝተዋል፡፡ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ […]

pp002

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር ጽ/ቤት በካቴድራሉ ግቢ ውጥ በአ/አ ሀ/ስብከት መዋቅራዊ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት ላይ በመቃውሞ ድብቅ ስብሰባ ተካሂዷል ተብሉ የተዘገበውን በፅኑ ተቃወመ

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል  አስደናቂ ከሚባሉ ታሪካዊ ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ ካቴድራሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ዓለም ዓቀፋዊ ይዘት ያለውና አንጋፋ ካቴድራል ሲሆን ከታሪካዊነቱም በተጨማሪ፡-•    ዓለም አቀፋዊ የኃይማኖት ስብሰባዎች የሚካሄድበት፣•    የፓትርያሪኮችና የብፁአን ለቃነ ጳጳሳት በዓለ ሲመት የሚከናወንበት፣•    ብሔራዊ የመታሰቢያ በዓላትና ሥርዓተ ፀሎት የሚካሄድበት ነው፡፡ከ6ቱ ቅዱሳን ፓትርያሪኮች መካከል 4ቱ የካቴድረሉ አገልጋዮችና የሥራ ኃላፊዎች የነበሩ […]

2400

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል በዓታ ለማርያም በዓል አደረሳችሁ

እመቤታችን 3 ዓመት ሲሆናት  ቅድስት ሐና ለባሏ ጌታዬ ልጃችን አድጋለች በተሳልነው መሰረት ለቤተ እግዚያብሔር እንስጣት አለችው፤ ይዘዋት ወደ ቤተመቅደስ ሲሄዱ ካህኑ ዘካርያስ ጉባዬ ዘርግቶ ህዝቡን ሰብስቦ እያስተማራቸው ነበር፤ እመቤታችንን ቢያያት ከጸሐይ አብርት ከመብረቅ አስፈርታ ታየችው፤ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን ልንመግባት ነው ብለው ተጨነቁ፤ በዚህ ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ህብስት ሰማያዊ ጽዋ ሰማያዊ ይዞ ተገለጸ አንድ ክንፉን […]

2346

በየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር ለሚገኙ አድባራት እና ገዳማት ተወካዮች ለሁለት ቀናትየቆየ የመዋቅር ረቂቅ ሰናድ ውይይት ተካሄደ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር የሚገኙ አድባራት እና ገዳማት ተወካዮች ከህዳር 29 – 30 ቀን 2006 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የመዋቅር ረቂቅ ሰነድ ስልጠና እየተሰጣቸው የሚገኝ ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎች ከሰላሳ አድባራት እና ገዳማት የተውጣጡ ናቸው፡፡ አጠቀላይ የሰልጣኞቹ ብዛትም ከ480 የማያንሱ መሆናቸውን ተረጋግጧል፡፡ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት […]

000xc

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ፣ ለአድባራትና ገዳማት ተወካዮች መዋቅርዊ የአሠራር ለውጥ እና አደረጃጀት ላይ ውይይት በመካሄድላይ ነው

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአራዳና ጉለሌ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር ለሚገኙ የ20 አድባራት እና ገዳማት ተወካዮች በመዋቅራዊ አደረጃጀት ረቂቅ ሰነድ ዙሪያ ከህዳር 27 – 28 ቀን 2006 ዓ.ም የሚቆይ ስልጠና እየተሰጣቸው የሚገኙ ሲሆን የሰልጣኞች ብዛት 320 ይደርሳል፡፡ በሀገረ  ስብከቱ የጥሪ ደብዳቤ መሠረት ከእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የሚወከሉት ተሳታፊዎች ጠቅላላ ብዛት 16 ሲሆኑ የውክልናቸው […]

00004

ሰበር ዜና የመስቀል በዓል በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ

የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ)በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ  ባኩ ከተማ ነው፡፡ስለቅርሱ የመረመረው ኮሚቴ ባቀረበው ውሳኔ ሐሳብ ላይ […]

m00001

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም አመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ !! ታቦተ ጽዮን ፤ ኅዳር ጽዮን እና አክሱም ጽዮን

m00001

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት አንዱ “ኅዳር ጽዮን” ሲሆን የሚከበረውም ኅዳር 21 ቀን ነው፡፡ የበዓሉን አከባበር ፤ ጥንተ ታሪኩን፤ ንግስት ሳባ ፤ቀዳማዊ ምኒልክና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮችን  እንመለከታለን፡፡
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  “ታቦተ ጽዮን” የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ተአምራት ለምእመናን እያስተማረች በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ በደብረ ሲና አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመና ከጸለየ በኋላ ዐሥርቱ ቃላተ የተጻፈበትን ጽላት /ታቦተ ጽዮን/ ከእግዚአብሔር እጅ ተቀበለ፡፡  “ታቦተ ጽዮን” የሚለውንም ስያሜ ያገኘችው ጽዮን ተብላ በምትጠራው የእስራኤል ከተማ ስም ነው፡፡ ጽዮን ማለት ተፀወነ፡- ተጠጋ፣ ተማጠነ ማለት ነው፡፡ ክቡረ ዳዊትም ጽዮንን አምባ፣ መጠጊያ አድርጎ ብዙ ጠላቶቹን ተዋግቶ አሸንፎ ድልን ተጎናጽፏል፡፡

ጽዮን የተባለችው የታላቁ የዳዊት ከተማ የተገፉና የተበደሉ ሕዝቦች ሁሉ እውነተኛ ፍርድ ለማግኘት፣ ተሰብስበው የሚሰነብቱባት ከተማ ስለነበረች፣ ጽላተ ሙሴም በዚያ ስለነበረች በርሷ ተማጽነውም ችግራቸው ሰለሚቃለል ታቦቷ “ታቦተ ጽዮን” ተብላለች፡፡
ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ በራእዩ “በሰማይ ያለችው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ

2213

ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ዋና አማካሪ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ፡፡በዛሬው ዕለት ማለትም ህዳር 19/2006 ዓ.ም የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው የተሾሙት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ÷ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ […]

2223

የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት ሊቀህሩያን ሰርፀ አበበ ከአድባራት እና ገዳማት ተወካዮች ጋር የትውውቅ መርሐ ግብር አደረጉ

                                                                                                                                                                                      

2223

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት ሊቀህሩያን ሰርፀ አበበ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አድባራት እና ገዳማት ተወካዮች ጋር የትውውቅ መርሐ ግብር ያደረጉ ሲሆን በዚሁ ዕለት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡ መሆናቸው ይፋ ተደርጓል፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ሀሳብ እንዲሰጡ በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት እና የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተጋበዙ ሲሆን ሥራ አስኪያጅ ንግግር ካደረጉ በኋላ ብፁዕነታቸው የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የዛሬው መርሐ ግብር አዲሱን የሀገረ ስብከታችንን ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ በመኮንንን፣ የምንቀበልበት፣ ሊቀ ህሩያን ሠርፀ አበበን የምናስተዋውቅበት ሲሆን ላዕከ ወንጌል በዕደ ማርያም ይትባረክ ከስራ አስኪያጅነት ወደ ስብከተ ወንጌል የሸኘንበት ነው፡፡

ብፁዕነታቸው አክለው ለተሰብሳቢው አካል የክፍለ ከተማውንም ሆነ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅም ምን እንስራ ልትሉአቸው ይገባል ገንዘባችንን በአግባብ ከተቆጣጠርን ገቢው ተመልሰው ወደ እኛው ነው የሚመጣው ለምዕመናን አገልግሎት እየሰጠን፣ እየፀለይን የምንኖር ከሆነ አንድ አገልጋይ የአንድ ምኒስቴር ደመወዝ ያህል ሊያገኝ ይችላል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ጥሩ ጠንካረን ተግባብተን እና ተከባብረን ከሠራን ነው፡፡ እንዱ ከልክ  ያለፈ ከበሬታ ሲሰጠው አንዱ ሊናቅ አይገባም፡፡ ጉድለታችንን ልትነግሩን እንጂ ልታሙን አይገባም፤ ጉድለት የሌለው ማንም ሰው የለም፤ እግዚአብሔር ከነጉድለታችን ነው የተሸከመን አንዱ ለሌላው መስታወት መሆን አለበት፡፡ አንዱ ከአንዱ ጋር መጻጻፍ ጉዳት እንጂ

2204

የአዲስ አባ ሀገረ ስብከት በአዲሱ አስተዳደራዊ የመዋቅር ሰነድ ዙሪያ ያደረገውን የ2 ቀናት ውይይት በጥሩ ውጤት አጠናቀቀ

                                 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ህዳር 17 ቀን 2006 ዓ/ም የተጀመረው የአዲሱ መዋቅር ሰነድ በ8 ዓበይት ርዕሶች የተከፈለ ሲሆን የሰነዶቹም ዝርዝር ረቂቅ የአደረጃጀት ሰነድ፣ የፋይናንስ መመሪያ ሰነድ፣ የግዥመመሪያ ሰነድ፣የልማትመመሪያ ሰነድ፣ የዕቅድመመሪያ ሰነድ፣ የቁጥጥርመመሪያ ሰነድ፣የስልጠናመመሪያ ሰነድ፣የአብያተ ክርስቲያናትመመሪያ ሰነድ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን