• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

pp002

በአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት ልዩ የስብከተ ወንጌል የአንድነት ጉባኤ መርሐ ግብር ተጀመረ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዋና ክፍል አስተባባሪነት የተጀመረው የአድባራት እና ገዳማት የአንድነት ጉባዔ የተጀመረው የካቲት 11 ቀን 2006 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ሲሆን ጉባዔው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ የአንደኛው ዙር ጉባዔ ይካሄዳል፡፡ የአንድነት ጉባዔው በምድብ እየተመደበ የሚካሄድ ሲሆን አንድ ምድብ ከሶስት አድባራት እስከ አስር […]

0094

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን እና የድኅነትን አስከፊነት አስመልክተው ለግማሽ ቀን የቆየ የጋራ ምክክር አደረጉ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሃይማኖቶች ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የምክክሩን ጉባኤ አስመልክተው የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን  ከሩቅም ከቅርብም አሰባስቦ እርሱ የሚከብርበትን ሥራ እንድንሠራ እንደዚህ ተሰብስበን ስለ ሀገራችን ችግር እንድንወያይ ስለፈቀደልን የተመሰገነ ይሁን፡፡ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን እና የልመናን አስከፊነት ለማስወገድ የአዲስ አበባ […]

640

የአዲስ ኣበባ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ ገበታቸው ታግድው የቆዩትን ሠራተኞች ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ አደረገ

በአሁኑ ወቅት ሀገረ ስብከቱ መልካም አስተዳደር ለማስፈን እያደረገው ካለው መልካም የሥራ እንቅስቃሴ መካከል አንዱ  በእንዳንድ ገደማትና አድባራት ያለአግባብ የሚታገዱትና የሚባረሩትን ሠራተኞች ትክክለኛ የሆነ ውሳኔና መፍትሄ መስጠት ነው፡፡በአሁኑ ሰዓት ገዳማትና አድባራት ከአቅማቸው በላይ ሠራተኞች በመያዛቸው የተነሳ ለጊዜው  ቅጥር እንዲቆም የተደረገ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ግን ለሥራ መደቡ የሚያስፈልገውን መስፈርት ወጥቶለት በህጉና በሥርአቱ መሰረት ቅጥርም ሆነ እድገት […]

0908

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2006 ዓ.ም. ዐብይ ጾምን አስመልክቶ ቃለ ምዕዳን አስተላለፉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2006 ዓ.ም. ዐቢይ ጾም አስመልክቶ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ባሉበት ወቅት “ጾም ለመንፈሳዊ ሕይወት መጎልበት፣ ራስን ለመግዛት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ልዩ ግንኙነትና አንድነት ለመፍጠር እጅግ አስፈላጊ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ቅዱስነታቸው ዐብይ ጾሙን አስመልክቶ ያስተላለፉትን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡ መልእክት ዘእም ኀበ […]

0049

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ሰነድ ርክክብ ተካሄደ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን የተቋማዊ ለውጥ አመራር ሲያጠና የቆየው የባለሞያ ቡድን የካቲት  6 ቀን 2006 ዓ.ም የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ሰነዱን ለሀገረ ስብከቱ በይፋ አስረክቧል፡፡የካቲት 6 ቀን 2006 ዓ.ም ረፋድ ላይ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በተካህደው የርክክብ እና ምስጋና መርሐ ግብር፣ 13 አባላት ያሉት የባለሞያ ቡድኑ ከ800 በላይ አጠቃላይ ገጾች ያሏቸውን 12 ሰነዶች በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ […]

g008

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በጅማ ሀገረ ስብከት ሐዋርያዊ አገልግሎት አካሄዱ

ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ከሌሊቱ በአስር ሰዓት ከመንበረ ፓትርያርክ ጉዞአቸውን የጀመሩት ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ሌሎች የቤተ ክርስቲያናችን ልዩ ልዩ የሥራ መሪዎች ዕሁድ ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም ከጧቱ አንድ ሰአት […]

0836

የአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት በታላቅ ድምቀት ተከበረ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የምትገኘው የአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት በዐል ሰኞ ጥር 19 ቀን 2006 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ […]

0822

ቃና ዘገሊላ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ ያደረገውን የበረከት ተአምር በየዓመቱ ጥር 12 ቀን በደማቅ ሁኔታ እንደምታከብር ይታወቃል፡፡  በዚሁ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ ከሚከበሩት የቃና ዘገሊላ በዓላት መካከል በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተከበረውን የቃና ዘገሊላ በዓል አስመልክቶ የበዓሉን ገጽታና ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ […]

6

የ2006ዓ.ም የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከበረ

እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥመቀት በሰላም በጤና በሕይወት አደረሳችሁ፡፡ በየዓመቱ ጥር 10 እና 11 የሚከበረው የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥመቀት በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን መሪነት ከ13 ታቦታት በላይ በሚያድሩበት በጃን ሜዳ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ  ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁአን […]

diocese

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መዋቅራዊ ለውጥ ረቂቅ ተፈጻሚ እንዲሆን ተጠየቀ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መዋቅራዊ ለውጥ ረቂቅ ደንብ ተፈጻሚ እንዲሆን ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት የተውጣጡ አስተዳዳሪዎች፣ ካህናት፣ ጸሐፊዎች ፣የሰበካ ጉባኤ ተወካዮች፣ የሰንበት ት/ቤቶት ተወካዮችና ምእመናን ጥር 2 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት በመገኘት ድጋፋቸውን ገለጹ፡፡ ድጋፋቸውን የገለጹት የቤተ ክርስቲያኒቷ ተወካዮች፤ ረቂቁ ተግባራዊ ሆኖ ቤተ ክርስቲያን […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን