• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

00101

ሰበር ዜና

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሽልማት የተበረከተለትን ጄነሬተር ለአዲግራት ሀገረ ስብከት በስጦታ አስተላለፈ፡፡የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባስመዘገበው ከፍተኛ የሥራ ውጤት በ34ኛ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሽልማት የተበረከተለትን የመብራት ጄነሬተር በርካታ ገዳማት ለሚገኙበት ለአዲግራት ሀገረ ስብከት በስጦታ አስተላልፏል፡፡ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ለጉባኤው ታዳሚዎች ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ […]

00401

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባስመዘገበው ከፍተኛ የሥራ ውጤት ልዩ ተሸላሚ ሆነ!!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስተያን በተካሄደው 34ኛ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከ2006 ዓ.ም  በ2007 የበጀት ዓመት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ድርሻ ከሆነው 65% ብር  16,445,189.90  ብልጫ በማሳየቱ አጠቃላይ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በተጠናቀቀበት ወቅት ልዩ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ይህ ከፍተኛ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው ከሚያዝያ ወር 2007 እስከ ሐምሌ ወር 2007 ዓ.ም የበጀት […]

0156

የ34ኛው አጠቃላይ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጸሎተ ቡራኬ ተጀመረ!!!

በየዓመቱ በጥቅምት ወር የሚካሄደው አጠቃላይ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዘንድሮው ዓመት ከጥቅምት 8/2008 ዓ.ም- ጥቅምት 11/2008 ዓ.ም ድረስ ለ4 ተከታታ ቀናት እንደሚካሄድ ከሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምርያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የጉባኤው መርሃ ግብር በተጀመረበት ወቅት “ስምአነ አምላክነ ወመድኃኒነ ተስፋሆሙ ለኩሎሙ አፅናፈ ምድር ወለእለሂ ውስተ ባህር ርሁቅ” የሚለው የዳዊት መዝሙር በዜማ ቅርቧል፡፡በመቀጠልም በማቴዎስ ወንጌል ም.18 ቁ.18 ላይ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ለ2ኛ ቦንድ መግዛቱ ተገለፃ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለህዳሴው ግድብ ቀደም ሲል የገዛው ቦንድ ብር2,026,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ሃያ ስድስት ሺህ ብር / ሲሆን በ2008 ዓ.ም የበጀት ዓመት ብር3,000,000.00 /ሦስት ሚሊዮን ብር/ በመጨመር ወደ ብር5,026,000.00 /አምስት ሚሊዮን ሃያ ስድስት ሺህ ብር / ከፍ እንዲል ያደርገ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ {flike}{plusone}

3247

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የ2008ዓ.ም የደመራ በዓል በድምቀት ተከበረ

                                                                                     በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ(MA) በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ  በመስቀል አደባባይ  የቤተክርስትያኒቱ ርዕሰ መንበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ የአሌክሳንድሪያ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ማርቆስ መንበረ ፓትርያርክ ፤ብጹአን  አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ፣ የአዲስ አባባ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማን […]

000921

የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ናቸው

                                                                                        በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ(MA) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ የአሌክሳንድሪያ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ማርቆስ መንበረ ፓትርያርክ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በመስቀል ደመራ በዓል ላይ እንዲገኙ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተደረገላቸው ግብዣ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።በዚሁም መሠረት ቅዱስነታቸው መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም. […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከቀረጥ ክፍያ ነጻ የገዛቸውን 4 ዘመናውያን አዳዲስ ሞዴል መኪኖች የርክክብ ሥርዓት አከናወነ!!

አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቀደም ሲል ከቀረጥ ክፍያ ነጻ የገዛቸውን 4 መኪኖችን አስመልክቶ የሕጋዊነታቸውን የማረጋገጫ ሰነድ አሟልቶ ካጠናቀቀ በኋላ መስከረም 13 ቀን 2008 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ቁጥራቸው 1,000 በሚደርስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመመሪያ ኃላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አድባራት እና ገዳማት ተወካዮች በተገኙበት 4ቱንም መኪኖች በይፋ በማሳየት በብፁዕ ወቅዱስ […]

0043

የተቀፀል ፅጌ በዓል በድምቀት ተከበረ!!

በየዓመቱ መስከረም 10 ቀን ሲከበር የቆየው የተቀፀል ፅጌ በዓል በዘንድሮውም በ2008 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጰሳት ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የአድባራትና ገዳማት ተወካዮች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ […]

0373

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2008 ዓ.ም የዘመን መለወጫ መልእክት አስተላለፉ

0373

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በእንተ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
-በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
-ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
-የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
-በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
-እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤
የዘመናት ፈጣሪ የሆነው አምላካችን እግዚአብሔር ያለፈውን ዓመት በሰላም አስፈጽሞ እንኳን ለአዲሱ የሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አደረሰችሁ!!
‹‹ወኀሊ ዓመተ ለትውልደ ትውልድ፤ የብዙ ትውልድን ዓመታት አስብ›› (ዘዳ. 32፡7) ፡፡ የሁሉም አስገኝና ፈጣሪ የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን ከፈጠራቸው ፍጥረታት መካከል አንድ ስንኳ ጥቅም የለሽ የሆነ ፍጥረት አይገኝም፡፡ፍጥረታት ሁሉ በእርሱ ዘንድ ውብና የየራሳቸው ዓላማና ተግባር ያላቸው ናቸው (ዘፍ.1፡25)እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት በፍጡር ዓቅም ሙሉ በሙሉ ተቆጥረው የሚዘለቁ አይደሉም፤

0018

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ ለ፳፻፰ ዓ.ም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!እንኳን ከ ፳፻፯ ዓ.ም ወደ ፳፻፰ ዓ.ም ሁላችንንም በሰላምና በጤና ጠብቆ አደረሰን!!ያለፈውን ዓመት በእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ በጤናና በሰላም አሳልፈነዋል ፤ ያለፈው ዓመት በሀገረ ስብከታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰጡት የመጨረሻ አመራር መሠረት በርካታ የለውጥ ሥራዎችን የጀመርንበት ዓመት […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት