• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ተወካዮች ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሕንጻ ግንባታ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት እንደሚችሉ አስታወቁ! !

ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሁለገብ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ተገኝተው እየተገነባ የሚገኘውን የኮሌጁን ሕንጻ አስመልክተው በሰጡት ሐሳብ ይህ እየተገነባ የሚገኘው ሕንጻ የኮሌጁን የማስተማር አቅም ወደ ተሻለ የዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለማሳደግ ታስቦ ሲሆን ኮሌጁ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት ቅድሚያ በመስጠት እያስተማረ ይገኛል፡፡ ይሁን […]

x 004

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጾመ ፍልሰታን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት መልእክት

x 004

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ፣ የእግዚአብሔርና የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች ምእመናንና ምእመናት፣ እንኳን ለሁለት ሺሕ ሰባት ዓመተ ምሕረት የቅድስት ድንግል ማርያም መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችሁ፡፡
‹‹ታዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር፣
ነፍሴ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች›› (ሉቃ. 1፡47)
ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት አካላዊ ቃለ እግዚአብሔርን ከፀነሰች በኋላ ወደ ቅድስት ኤልሳቤጥ ቤት ገብታ ሰላምታ ባቀረበች ጊዜ በኤልሳቤጥ ማኅፀን ያለው ፅንስ በድንግል ማርያም ማኅፀን ላለው ፅንስ ከመስገዱም በተጨማሪ  ቅድስት ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብፅዕና በሰፊው መናገሯ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፎአል (ሉቃ 1፡45) ፡፡እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር በቅዱስ ገብርኤልና በቅድስት ኤልሳቤጥ በኩል ያስነገረላትን ታላቅ ክብርና ሞገስ በማድነቅ እግዚአብሔርን በከፍተኛ ደረጃ አመሰግናለች፤ ደስታዋንም ገልጻለች፡፡
ከዚህ ከቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና የምንማረው ዓቢይ ትምህርት እግዚአብሔር በየጊዜው ያደረገልንን መልካም ነገር ሁሉ በማሰብ ለእርሱ አምልኮና ምስጋና ማቅረብ ያለብን መሆኑን ነው፤
ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔርን ባመሰገነችበት በዚህ ክፍል በእርስዋና በክርስቲያኖች መካከል ያለው የዘላለም ግንኙነትና ትስስር ምን ዓይነት ገጽታ እንደሚኖረው በትንቢት ተናግራለች፤ እርሱም ‹‹ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል››  የሚል ነው (ሉቃ. 1፡48)፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት፤
በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቅ የቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚ ተግባር ቃለ እግዚአብሔርን መጠበቅና ማስጠበቅ እንደሆነ ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፤
እግዚአብሔር ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከተናገራቸው ኃይለ ቃላት መካከል ‹‹ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፣ ባለሟልነትን አግኝተሻል፤ ጸጋን የተመላሽ ነሽ፤ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው›› የሚሉት በቀዳሚነት ተጠቃሽ ናቸው፤ (ሉቃ፡ 1፡ 28-30) በተለይም ‹‹ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል›› የሚለው ቃል በቅድስት ድንግል ማርያም አንደበት የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ይህ የእግዚአብሔር ቃል ቅድስት ድንግል ማርያምንና ምእመናንን እስከ ወዲያኛው ያስተሳሰረ የቃል ኪዳን ሐብል ነው፤ በየዓመቱ ከነሐሴ አንድ ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ ዐሥራ አምስት ቀን በጾም፣ በጸሎት፣ በአምልኮ፣ በምሥጋና፣ በንሥሐና በቁርባን ለእግዚአብሔር መገዛታችንና ቅድስት ድንግል ማርያምን መማፀናችን ባለሟልነትን አግኝተሻል የሚለውን ቃል መሠረት በማድረግ ነው፡፡
ባለሟል ማለት በባለሥልጣን ዘንድ ተሰሚነት፣ ተደማጭነት፣ ተቀባይነት ያለው ቀራቢ ልዩ ወዳጅ ማለት እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡
በዚህ መሠረት ቀደምት ቅዱሳን አበውና ነቢያት በባለሟልነታቸው በሕይወት እያሉም ሆነ ከሞቱ በኋላ በአፀደ ነፍስ ሆነው እግዚአብሔርን እየተማፀኑ እየማለዱና እየለመኑ ሰውን ያስምሩ እንደነበር ተጽፎአል፤ (ዘፀ. 32፡ 11-14፤ ኢዮ. 42፡ 7-9፤ ነገ.ቀዳ. 11፡ 10-13) ፡፡
እንደዚሁም ሁሉ ቅድስት ድንግል ማርያም በባለሟልነቷ ብቻ ሳይሆን እርሱን ፀንሳ የወለደችና ያሳደገች የጌታችን እናትና ልዩ ባለሟል በመሆኗ በጸሎትዋ፣ በልመናዋና በአማላጅነቷ አምነን ስንማፀናት እኛን ታስምራለች ብለን እናምናለን፤
የቅድስት ድንግል ማርያም ልመና ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ በቃና ዘገሊላ የሠርግ ቤት ያቀረበችው ምልጃና ልመና በሁኔታውም የተገኘው ውጤት ለኛ በቂ ማስረጃችን ነው፤ (ዮሐ. 2፡ 1-9)
ከዚህም ጋር ራሱ ጌታችን በመስቀል ላይ ሆኖ እርስዋን የኛ እናት አድርጎ፣ እኛንም የእርስዋ ልጆች አድርጎ መስጠቱ ልጅ የሚፈልገውን ነገር ከእናቱ እንደሚሻ ሁሉ እኛም የምንሻውን

4001

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስተር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስ/ት/ቤት ወጣቶችን አነጋገሩ

                       በቀሲስ አሉላ ለማ የሀ/ስ/የሰ/ት/ቤት/ማ/ዋ/ክ/ኃላፈ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች ጋር በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ዓርብ በ23/11/07 ከ8፡30 ሰዓት ጀምሮ አነጋገሩ፡፡ በስብሰባው የተነሱት የመወያያ አጀንዳዎች በሰላም፣ በአክራሪነት እና በቤተክርስቲያን አጠቃላይ ጉዳዮች ሲሆን፣ በርካታ ሐሳቦችና መወያዎች ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ አግኝተዋል፡፡በስብሰባው የተሳተፉ የሰ/ት/ቤት ወጣቶችም ቤተክርስያናችን ለዘመናት ሰላምን ስትሰብክና የሌሎችንም […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች እግዚአብሔር ዝናመ ምሕረቱን እንዲያወርድ እና ወርሐ ክረምቱ የተባረከ እንዲሆንልን የአንድ ሳምንት ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ አሳሰቡ

ዓመታዊ የቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግሥ በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከብሯል፡፡በዓመት ሁለት ጊዜ በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ በዓለ ንግሥት ሐምሌ 19 ቀነ 2007 ዓ.ም. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምያ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ አህጉረ ስብከቶችና አድባራትና […]

03380

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሙያ ማሻሸያ ስልጠና በመከታተል ላይ ላሉ የሒሳብ ባለሙያዎች በስልጠና ማዕከሉ በአካል በመገኘት የሥራ መመሪያና ቃለ ቡራኬ ሰጡ

ቅዱስ ፓትርያርኩ በሀገረ ስብከቱ ተገኝተው ለሠልጣኞቹ አባታዊ ምክር ሲሰጡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዐን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት የተወጣጡ የሂሳብ ባለሙያዎች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና የሚወስዱበትን የስልጠና ማዕከል ለመጎብኘትና የሥራ መመሪያ ለመስጠት በተገኙበት ወቅት የሀገረ ስብከቱን ዋና […]

00336

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለአድባራትና ገዳማት የሒሳብ ሠራተኞች ሲሰጥ የቀየውን አንደኛ ዙር የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በኮምፒውተር በተደገፈ የተግባር ሥልጠና መስጠት ቀጥሏል!!

የሀ/ስ/ሒ/በ/ዋ/ክ/ኃ/ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ሥልጠናውን ሲሰጡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሥሩ ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት የሒሳብ ሠራተኞች ሲሰጥ የቆየውን አንደኛ ዙር የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና በኮምፒውተር በተደገፈ መልኩ የተግባር ሥልጠና መስጠት የቀጠለ ሲሆን ሥልጠናውን በበላይነት በማስተባበርና በመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የትግበራ ሥልጠናውን አስመልክተው ለሠልጣኞቹ […]

0297

ለጋራዥ አገልግሎት እንዲውል ተደርጎ የነበረው የቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ወደ ቀደሞ የመማር ማስተማር ታሪኩ ተመለሰ!

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ትምህርት ቤትን አስመልክቶ የካቴድራሉ የሰበካ ጉባኤ ም/ሊቀ መንበር ኮ/ል ክፍሉ ሀብተወልድ የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ት/ቤቱ በወቅቱ በነበረበት የሥራ አፈጻጸም ጉድለት የተነሳ ከትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው መመሪያ መሠረት የመማር ማስተማር ተግባሩን እንዲያቆም መደረጉን ምክንያት በማድረግ በወቅቱ የነበረው የሰበካ ጉባኤ ውሳኔ ት/ቤቱ ወደ ጋራዥነት ተለውጦ በብር 17,000.00 ለግለሰቦች እንዲከራይ […]

1601

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ ባርከው ከፈቱ!

ገዳሙ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ ቅዱስ ባርከው ሲከፍቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ሐሙስ ሐምሌ 16 ቀን 2007 ዓ.ም 22 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተገኝተው የደብረ ሊባኖስ አንድት ገዳም ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ ባርከው ከፍተዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ሕንጻውን በባረኩበት ወቅት ሕንጻው ለገዳሙ የሚሰጠው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑንና ሌሎቹም እንዲህ አይነቱን […]

1599

ዜና እረፍት

የመንበረ ፖትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም የበላይ ኃላፊ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለዩ፡፡ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀጳጳስ ከአባታቸው ከመምህር ሀብተ ማርያም ደስታ ተክሌና ከእናታቸው ከወ/ሮ በስሙ ቸርነት ታኅሣሥ 19 ቀን 1925 ዓ.ም በድሮው አጠራር ሸቸ ጠቅላይ ግዛት ሰላሌ አውራጃ እንሳሮ ወረዳ እየተባለ ይጠራ በነበረው በአሁኑ አጠራር በውጨሌ ወረዳ ልዩ ስሙ […]

0572

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሊባኖስ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው ተመለሱ!!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ኪልቅያ ካቶሊኮስ የአርመን ሰማዕታትን አንድ መቶኛ ዓመት አከባበር ምክንያት በማድረግና በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማጠናከር ይቻል ዘንድ ባደረጉላቸው ይፋዊ ጥሪ መሠረት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን አስከትለው ከሐምሌ 9-14 ቀን 2007 ዓ/ም በቤይሩት ሊባኖስ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን