• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

0018

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ ለ፳፻፰ ዓ.ም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!እንኳን ከ ፳፻፯ ዓ.ም ወደ ፳፻፰ ዓ.ም ሁላችንንም በሰላምና በጤና ጠብቆ አደረሰን!!ያለፈውን ዓመት በእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ በጤናና በሰላም አሳልፈነዋል ፤ ያለፈው ዓመት በሀገረ ስብከታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰጡት የመጨረሻ አመራር መሠረት በርካታ የለውጥ ሥራዎችን የጀመርንበት ዓመት […]

00104

በፌደራል ጉዳዮች ሚንስቴርና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጋራ ትብብር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሁከትን የማስወገድና ሰላምን የማስፈን ጉባኤ ተጠናቀቀ!!

00104

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጋራ ትብብር ከነሐሴ 29 ቀን እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ያህል፡-
1.የሃይማኖት አክራሪነት፣ፅንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው፣
2.በሀገራችን የሃይማኖት ተቋማትና ተከታዮች በሰላም አብሮ የመኖር ወርቃማ ተሞክሮን የማስቀጠል ፋይዳው፣
3.በሃይማኖት ተቋማት የጤናማ ግንኙነት ጉዳዮችና የመፍትሔ አቅጣጫ በተሰኙ ሦስት ዐበይት መወያያ አጀንዳዎች በፌደራል ጉዳዮች ምንስትር በዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያምና በሚኒስትር ዴታው በአቶ ሙሉጌታ አቅራቢነት ቁጥራቸው አንድ ሺህ ለሚደርስ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ተወካዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሲሰጥ ቆይቶአል፡፡
የስብሰባው ተሳታፊዎችም በአስር ቡድን በመደራጀት በተሰጡት የመወያያ አርእስቶች ላይ የተመሠረተ የቡድን ውይይት አካሄደዋል፤ በቡድን ውይይቱም ከተነሱት በርካታ ነጥቦች መካከል የሃይማኖት ተቋማትና መንግሥት በጋራ አጀንዳዎች አብረውና ተባብረው መሥራታቸው ተገቢ ነው ፣ በታሪክ እንደተረዳነው በፅንፈኞችና በአክራሪዎች የብዙ ዜጎች ሕይወት ተቀጥፏል ፣ አክራሪዎችና ፅንፈኝነት ወደ ሀገራችንም እየገባ ነው ፣ የፅንፈኝነትና የአክራሪነት እንቅስቃሴ ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ ነው፣ የፅንፈኝነትና የአክራሪነት አስተሳሰብ ወጣቶች በተሳሳተ መንገድ እንዲሄዱ ማድረግ ነው፤ ይህ አደገኛ አስተሳሰብ ሥር ሳይሰድ መነቀል አለበት፣ ፅንፈኝነትና አክራሪነት በቤተ ክርስቲያናችን እየታየ በመሆኑ ለወደፊቱ ይህንን እኩይ ተግባር መዋጋት አለብን፣ የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች ለዚህ እኩይ ተግባር ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጠንክረን ማስተማር አለብን፣ የፅፍኞችና የአክራሪዎች የቅስቀሳ ስልት በቤተ ክርስቲያን የመልካም አስተዳደርና የሙስና ችግር አለ በሚል ሽፋን ነው፤ ፅንፈኞቹ ለቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ ደዌ ሲሆኑ ለመንግሥት ደግሞ የጎን ውጋቶች ናቸው ፣ ፅንፈኞቹና አክራሪዎቹ የወደዱትን ሰው ኦርቶዶክሳዊ ነው ይላሉ ፤ የጠሉትን ሰው መናፍቅ እና ተሐድሶ ነው ይሉታል፡፡

የጽንፈኞቹና የአክራሪዎቹ መገለጫ ባህርያት
በቅዱስ ፖትርያርኩ ፣ በብፁዓን አባቶች ፣ በልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች መካከል መለያየት እንዲፈጠር ማድረግና መከፋፈል ፤

0031

እንዲሁም ማሸማቀቅ፣ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚሰበሰቡት ሀብት ኦዲት እንዳይደረግ እምቢተኝነትና ሌላ ማደናገሪያ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር ማድረግ፣  ዓላማቸውን የማይደግፉትን ሁሉ አማሳኞች ፣ ዘራፊዎችንና ሌቦች እያሉ ተቆጣጣሪ በሌለው ፌስቡክና ብሎግ ስማቸውን ማጥፋት ፤ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ የተፈቀደውን የአሥራት ክፍያ ለቡድንና ለግል ማድረግ፣
ብልሹ አሠራርና ግብረ ሙስና
ለፅንፈኞቹና አክራሪዎቹ ምቹ ሁኒታ የፈጠረላቸው በአንዳንድ ዓላማቸውና ተልዕኳቸውን በዘነጉ ክፍሎች የሚታየው ሥር የሠደደ የሙስና እና የመልካም አስተዳደር ችግር ሲሆን ይህም ማለት በስልጣንና በገንዘብ የሚመኩ ክፍሎች የማስፈራራት ተግባር በመፈጸም ፣ የቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች ለወጣቱ ትኩረት ሰጥተው አለመሥራት፣ ዘረኝነትና ቡድናዊነት መፍጠር፣ የቤተ ክርስቲያን አንጋፋ ሊቃውንት የሚደርስባቸውን አስተዳደር በደል በመደበኛ ፍርድ ቤት ዳኝነት እንዳያገኙ ማድረግ ፣ መዋቅርን መጣስ ፣ ወጥና ግልጽ የሆነ አሠራር እና ቅሬታ ሰሚ አካል አለመኖር፣ የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶችና የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት መዋቅራዊ አሠራሩን አለመከተል፤ በአስተዳደርና በፋይናንስ ዘመኑን የዋጀ የአሠራር ሥርዓት አለመዘርጋት የሚሉና ሌሎችም በርካታ ነጥቦች ይገኙባቸዋል፡፡
በአሥር የተከፈለው የቡድን ውይይት ከተጠናቀቀ በኋላ በቀረቡት የቡድን የጋራ ውይይት ነጥቦች ላይ ከመድረኩ መሪዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጥባቸዋል፡፡
ለተፈጻሚነታቸውም በመንግሥት በኩል አስፈላጊው ክትትል እንደሚደረግበት ምንስትሩ አክለው ገልጸዋል፤ በአይነቱ ልዩ የሆነው ይህ የጋራ የምክክር ጉባኤ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አስታውቀዋል፡፡
የቅዱስነታቸውን ሙሉ መግለጫና መልእክት ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤
የሰላም አምላክ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጉባኤ ተገኝተን የሰላምና መቻቻል መልእክት ለማስተላለፍ ስለፈቀደልን ምስጋና፣ አምልኮትና ክብር ለእርሱ ይሁን ፡፡
‹‹ኅሣሣ ለሰላም ወዴግና፤ ሰላምን አጥብቀህ ፈልጋት፣ ባገኘሃትም ጊዜ ተከተላት እንጂ አትለያት›› (መዝ 33፡14)ሁላችንም እንደምናውቀው የሰላም አምላክ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሲፈጥር በሕይወት፣ በነጻነትና በደስታ እንዲኖሩ ነው፤የሕይወት፣ የነጻነት፣ የደስታና የብልጽግና ዋስትና ሰጭ ደግሞ ከፈጣሪ የተገኘች ሰላም ናት፤ ሰላም ሰውን ብቻ ሳይሆን ከሰው ጋር ያሉ እንስሳት፣ ዓራዊት፣ አዕዋፍ፣ ዓሣት፣ ዕፅዋት፣ አዝርእት፤ ነፍሳት ወዘተ ሁሉ ይፈልጓታል ፡፡ከዚህም ሌላ ሰማዩም ምድሩም ሰላምን ይፈልጋል፤ ምክንያቱም ሰላም ከሌለ ሁሉም ተጎጂዎች ናቸውና፤ዛሬ የሰማዩ አየር በአየር ብክለት እየተጎዳ ሰላምን አጥቶአል እየተባለ በየጊዜው ሲነገር እንሰማለን፤ምድርም እንደ ልብስ የሚያገለግሏት ዕፅዋት እየተመነጠሩ ባዶ ወደ መሆን እየተቃረበች ስለሆነ በተፈጥሮ መዛባት ሰላምን አጥታለች እየተባለ ነው ፡፡ሰማይና ምድር

00008

በፌዴራል የሃይማኖት ተቋማት ባለመግባባት ጎዳዮች ዙሪያ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስፈን በአይነቱ የተለየ ውይይት እየተካሄደ ነው

በሃይማኖት ተቋማት ያለመግባባት ጎዳዮች መሠረታዊ የመፍትሔ አቅጣጫ ዴሞክራሲያዊነትና ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን በሚል ርዕስ የፌዴራል የሃይማኖቶች ጎዳዮች ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር በመሆን ቁጥራቸው ከ1000 በላይ ለሚደርስ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ተወካዮች ከነሐሴ 29 ቀን 2007 ዓ.ም  እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በአይነቱ ልዩ የሆነ ውይይትና ምክክር እየተካሄደ ሲሆን […]

0520

የሕንጻ ግንባታው ከመሠረቱ እስከ ጉልላቱ በአርማታ ብቻ ተሠርቶ የተጠናቀቀው የአንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ታሪካዊ አመሠራረት!!

በደቡብ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም፣ በምዕራብ የእንጦጦ ርዕሰ አድባራት ቅ/ማርያም፣በሰሜን የገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም፣ በምሥራቅ የአሜሪካ ኢንባሲ የሚአዋስኑት፣ በመልክአ ምድራዊ አቀማመጡ ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ የሚታየው የአንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በተለምዶ አጣራር ጭቁኑ ሚካኤል በተለያዩ የታሪክ ሰነዶች ተጽፎ እንደሚገኘው ክህነትን ከልዑልነት ጋር አጣምረው በመያዝ ይታወቁ በነበሩት በልዑል ራስ ከሣ ኃይሉ አማካኝነት በ1968 ዓ.ም […]

2832

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለዩ

2832

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ የኢሊባቡርና የጋንቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ  አቡነ ፊልጶስ ነሐሴ 25/2007 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ የተለዩ ሲሆን በዚሁ ዕለት  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ቤተ ክህነት እና በአበባ ሀገረ ስብከት ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎቸንና ሠራተኞች አስከሬናቸው  ካረፉበት ናሽናል ሆስፒታል ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት በክብር ታጅቦ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል  እርፏል፡፡

የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ አጭር የሕይወት ታሪክ
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የኢሉባቦርና የጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከአባታቸው ከአቶ ፈለቀ ለውጤ ከእናታቸው ከወ/ሮ አዛልነሽ ሙሉ በ1928 ዓ.ም. በወሎ ክፍለ ሀገር በላስታ ቡግና አውራጃ ሠራብጥ ካህናተ ሰማይ ከሚባል ቤተ ክርስቲያን

0498

የደብረ ታቦር በዓል በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ካቴድራል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ!!

በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን የሚከበረው የደብረ ታቦር በዓል በዘንድሮው 2007 ዓ.ም በሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በልዩ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል፡፡ በበዓሉ አከባበር ወቅት ፕንግ ድርብ (ልብሰ ያሬድ) የለበሱ የአብነት ተማሪዎች “አሀደ ለከ ፣ ወአሀደ ለሙሴ ፣ ወአሀደ ለኤልያስ፣  ንግበር ማህደረ” የሚለውን የወንጌል ቃል በዜማ ያቀረቡ ሲሆን በተመሳሳይ የደብሩ የሰንበት ት/ቤት […]

እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ መጣ

“ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን፣ ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ፣ ወደረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው÷ በፊታቸውም ተለወጠ÷ ፊቱም እንደፀሐይ በራ÷ልብሱም እንደበርሃን ነጭ ሆነ÷እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው ፣ብትወድስ በዚህ ሦስት ደስ አንዱን ላንተ፣አንዱንም ለሙሴ፣አንዱንም ለኤልያስ እንሥራአለ፡፡ እርሱም ገና ሲናገር እነሆ ብርሩህ ደመና ጋረዳቸው÷እነሆም ከደመናው በእርሱ […]

e11

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ፓትርያርክ ዘግብፅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመጎብኘት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አስታወቁ!!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በ2008 ዓ.ም የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በ2008 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ ከግብፅ ኮፕቲክ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የጉብኝት ተግባር እንደሚያከናውኑ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐምሌ 30 […]

0450

ሰበር ዜና

                                                                                                         በመ/ር ሣህሉ አድማሱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከቀረጥ ክፍያ ነጻ የሆኑ አራት ዘመናዊ አዳዲስ ሞዴል መኪኖችን ገዝቶ ያስገባ መሆኑ ተገለፀ!! የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት የሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በ2008 ዓ.ም በያዘው መሪ ዕቅድ መሠረት ከግብርና ቀረጥ ክፍያ ነፃ የሆኑ አራት ዘመናዊ አዳዲስ ሞዴል መኪኖችን ለመግዛት ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በወቅቱ  ለብፁዕ ወቅዱስ […]

1411

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአድባራትና ገዳማት ለሚገኙ ሠራተኞች ያዘጋጀው ፎርም (ክሊራንስ) በሥራ ላይ እንዲውል መመሪያ ሰጠ!!

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሥራ ላይ ለሚገኙ ገዳማትና አድባራት ሠራተኞች ያዘጋጀው ፎርም (ክሊራንስ)  ሳምፕል በሥራ ላይ እንዲውል ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱ ሁለገብ አዳራሽ ለተገኙ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ ጸሐፍያን ፣ ምክትል ሊቃነ መናብርት ፣ የሒሳብ ሠራተኞችና ተቆጣጣሪዎች መመሪያ ተላልፎአል፡፡ በተዘጋጀው የፎርም (ክሊራንስ) ማንዋል ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያና መግለጫ የሰጡት የሀገረ ስብከቱ ዋና […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን