• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

t009

ቅዱስ ፓትርያርክ የአዲግራት ዩኒቨርስቲን ጎበኙ

የአዲግራት ዩኒቨርስቲ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ብፁዕ ወቅዱ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዩጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት የጉበኝታቸው አንዱ አካል የሆነውን  የአዲግራት ዩኒቨርስቲን ጥቅምት 27 ቀን 2008 ዓ.ም  ምሽት ላይ ጎበኝተዋል፡፡የዩኒቨርስቲውን አጠቃላይ ይዞታ ፣የማሪዎችን ዶርምተርና የመመገቢያ ቦታዎችን በመኪና በመዘዋወር የተመለከቱት  ቅዱስነታቸው ዩኒቨርስቲ የሚጠቀምበትን የዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል እና ማዕከሉ የሚጠውን […]

t001

የአዲግራት ደብረ መድኃኔት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተከበረ

ቅዱስ ፓትርያርኩ በደብሩ ተገኝተው አባታዊ ምክር ሲሰጡ በአዲግራት ከተማ በምሥራቃዊ ዞን ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የአዲግራት ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት በብፁዕ ወቅዱስ  ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ተባርኮ የተመረቀ ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህ ሕንፃ ከተራ ቤትነት ወደ ተቀደሰ ቤተ ክርስቲያንነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ቀኖና  መሠረት ተለውጧል፡፡ስለሆነም የአከባቢው ህዝበ ክርስቲያን በገንዘቡ […]

t006

ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር ያለን የሃይማኖት ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ ለሀገር ልማት በጋራ መሥራት እንደሚገባ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አሳሰቡ

ብፁዕ አቡነ ተሥፋ ሥላሴ የወርቅ ፅዋ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ሲያበረክቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የምሥራቅ ትግራይ ዞን ሐዋሪያዊ ጉዞን በማስመልከት የትግራይ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ተስፋ ሥላሴ፤ካህናት፣ ምዕመናንና በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሚማሩ ተማሪዎች  ከአዲግራት ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አቀባበል አድረገውላቸዋል፡፡የአዲግራት ከተማ ሕዝበ […]

t001

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የምሥራቃዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት ሐዋርያዊ ጉዞ እንደቀጠለ ነው

         ቅዱስ ፓትርያርኩ የአብርሃ ወአጽብሐ ገዳምን ጎበኙ ቅዱስ ፓትርያርኩ በገዳሙ ተገኝተው አባታዊ ምክር ሲሰጡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም በውቅሮ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውን የደብረ ነገስት አብርሃ ወአጽብሐ ገዳምን ጎብኝተዋል፡፡ገዳሙን ለመጎብኘት ከብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ከጠቅላይ ቤተ-ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች ፤ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት […]

t003

ቅዱስ ፓትርያርኩ የውቅሮ የአጽቢ ወንበርታንና የደብረ ዓላማ አሲራ መቲራ ገዳምን ጎበኙ

የደብረ ዓላማ አሲራ መቲራ ገዳም

00022

የጥቅምት 2008 ዓ.ም.የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ

ጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም.ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመደበኛ ስብሰባ፤ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ተራ ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የመክፈቻው ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከበዐሉ ዋዜማ ከጥቅምት 11 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 22 […]

00310

የደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ!!!

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ታሪካዊና ዘመናዊ ሕንጻ ቤተክርስቲያን የግንባታ ሥራው በመጠናቀቁ ቅዳሜ ጥቅምት 13 ቀን 2008 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳት ፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች […]

p004

የጥቅምት 2008 ዓ.ም.የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጀመረ

p004

በስመ አብ ወወልድ   ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
የአማልክት አምላክ፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የአጋእዝት ጌታ የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን ከተለያዩ የዓለም አህጉርና ከሀገራችን አህጉረ ስብከት አሰባስቦና አንድ ላይ አገናኝቶ በመንፈስ ቅዱስ ስለተሰጠን ሐዋርያዊ ተልእኮ ለመወያየት ስለሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን ፡፡
‹‹ምንተ ይቤ መንፈስ ቅዱስ ለአብያተ ክርስቲያናት፤ መንፈስ ቅዱስ አብያተ ክርስቲያናትን አስመልክቶ ምን አለ?›› (ራዕ. 2፡7) ፡፡በጌታችን በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተችው ክርስቶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከበዓለ ሐምሣ ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ አመራርና ጥበቃ ሥር እንዳለች ይታወቃል፡፡
ቅዱስ መንፈሰ እግዚአብሔር ዓለም በማያየውና በማያውቀው ረቂቅ ጥበቡ በሃይማኖት አማካይነት በልበ ምእመናን አድሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲመራ ይኖራል ፡፡
ከዚህም ሌላ በሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን አማካይነት ቅዱስ ቃሉንና ቅዱሳት ምሥጢራቱን ለምእመናን ያድላል ፡፡
በመሆኑም ሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን፤ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሪ የሆነው መንፈስ ቅዱስ የሚለውንና የሚናገረውን በትክክል አዳምጠውና ተረድተው ምግብናቸውን ማከናወን እንዳለባቸው ለሰባቱ ሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን ዘእስያ የተነገረው ቃለ ተግሣጽ ወምዕዳን በግልጽ ያስተምረናል ፡፡
ለተጠቀሱት የቤተ ክርስቲያን ሥዩማን የተላለፈው መልእክት በአጠቃላይ የመንፈስ ቅዱስ ቃል እንደሆነ ለማመልከት ‹‹ምንተ ይቤ መንፈስ ቅዱስ ለአብያተ ክርስቲያናት›› በሚልና ‹‹ዘቦ ዕዝን ሰሚዐ ለይስማዕ›› በሚል ኃይለ ቃል ሲዘጋ እናያለን፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
ለሰብዑ አብያተ ክርስቲያናት ዘእስያና ለአለቆቻቸው የተነገረው ሁሉ ዛሬ ያለችው ቤተ ክርስቲያንና አለቆቿን ጭምር በቀጥታ የሚመለከት እንደሆነ ጥርጥር የለውም ፡፡
ከአለቆቹ መካከል የተመሰገኑም፣ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙም፣ እንደዚሁም ጠንከር ያለ ተግሣጽ የደረሰባቸው እንዳሉ እንገነዘባለን ፡፡
ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የሥራ ኃላፊነት የምንገኝ ሥዩማንም በዚያን ጊዜ በነበረችው ፈታኝ ዓለም ውስጥ የምንገኝ እንደመሆናችን መጠን፤ በዚያን ጊዜ የነበሩ ኩነቶች ሁሉ አሁንም አይኖሩም ማለት አይቻልም ፡፡
በየትኛውም ዘመን፣ በየትኛውም ቦታ፣ ክፍተት አይፈጠርም ብሎ ሙሉ በሙሉ ኃላፊነት መውሰድ የሚችል ይገኛል ተብሎም አይጠበቅም ፡፡
ነገር ግን የከፋና የባሰ ክፍተት እንዳይፈጠር የተጠናከረ ሥራ በመሥራት መከላከል የሚችሉ በየጊዜው ሁሉ የተነሡ ታላላቅ አበው እንዳሉ እናስተውላለን ፡፡
በዚህ ዘመን የምንገኝ ኖሎትም ምንም ቢሆን ከዚህ እውነታ ውጭ መሆን አንችልም፤ መሠረታዊ ችግር ሊሆን የሚችለው ክፍተት ለምን ተፈጠረ የሚለው ሳይሆን ክፍተት መኖሩ እየታወቀ ዝም ብሎ መኖሩ ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ ይህ ዓቢይ ጉባኤ ብዙ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ በቤተ ክርስቲያናችን መሠራት የነበረባቸው፤ ሆኖም ግን እስካሁን በአጥጋቢ ሁኔታ ያልተሠራባቸው የሥራ መስኮች እንዳሉ ባይካድም ጥሩ ውጤት ያስመዘገብንባቸው ነገሮች እንዳሉም መዘንጋት የለበትም፤
በተለይም ሕዝበ ክርስቲያኑ ባለው ዓቅም ሁሉ ቤተ ክርስቲያኑን ለመደገፍና ለማልማት የሚያደርገው ቀና ትብብር ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ተስፋ ሰጪ ሆኖ ይታያል፣
አንዳንድ አህጉረ ስብከትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በሚያስደንቅ ሁኔታ የራስ አገዝ ልማት እያካሄዱ ለቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ የሚሆን ትልቅ ዓቅም እየፈጠሩ ይገኛሉ ፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችንን ሐዋርያዊ ተልእኮ ለማስፋፋት በዓለም ዙሪያ የተደረገው እንቅስቃሴ በአሁኑ ጊዜ ሁሉንም ክፍለ ዓለማት ማለትም ከምዕራብ አሜሪካ እስከ ጃፓን፣ ከአየርላንድ እስከ አውስትራሊያ ቤተ ክርስቲያናችን ክንፎቿዋን የዘረጋችበት ሁኔታ የተፈጠረ በመሆኑ ትልቅ ስኬት ተገኝቶአል ማለት እንችላለን፤ ቤተ ክርስቲያናችንም ዓለም አቀፋዊት ቤተ ክርስቲያን ወደ መሆን አድጋለች ማለት ይቻላል ፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፡፡
የቤተ ክርስቲያናችን ሥራ ሰፊና ዘርፈ ብዙ በመሆኑ አሁንም ቢሆን  ትኩረት ተሰጥቶአቸው በቅድሚያ ሊሠሩ የሚገቡ ሥራዎች እንዳሉ ማስታወሱ ተገቢ ነው፤ በመሆኑም፤

  • ቤተ ክርስቲያናችን ዘመኑን የዋጀ የአስተዳደር ጥበብ ተከትላ ሀብትዋና ንብረትዋን መጠበቅ የሚያስችሏትን አሠራሮች መቀየስ፤
  • በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ መሠረት ሊዘጋጁ የሚገቡ ልዩ ልዩ ደንቦች፣ ፖሊሲዎችና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ሥራዎች ሁሉ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖራቸው ማድረግ፤
00101

ሰበር ዜና

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሽልማት የተበረከተለትን ጄነሬተር ለአዲግራት ሀገረ ስብከት በስጦታ አስተላለፈ፡፡የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባስመዘገበው ከፍተኛ የሥራ ውጤት በ34ኛ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሽልማት የተበረከተለትን የመብራት ጄነሬተር በርካታ ገዳማት ለሚገኙበት ለአዲግራት ሀገረ ስብከት በስጦታ አስተላልፏል፡፡ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ለጉባኤው ታዳሚዎች ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ […]

00401

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባስመዘገበው ከፍተኛ የሥራ ውጤት ልዩ ተሸላሚ ሆነ!!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስተያን በተካሄደው 34ኛ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከ2006 ዓ.ም  በ2007 የበጀት ዓመት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ድርሻ ከሆነው 65% ብር  16,445,189.90  ብልጫ በማሳየቱ አጠቃላይ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በተጠናቀቀበት ወቅት ልዩ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ይህ ከፍተኛ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው ከሚያዝያ ወር 2007 እስከ ሐምሌ ወር 2007 ዓ.ም የበጀት […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን