• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ የኢትዮጵያና የሩሲያን ግንኙት ለማጠናከር እንደምትሰራ ገለፀች

በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገለፀች። ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለኃይማኖት በሩሲያ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው ተመልሰዋል። ፓትርያርኩ በጉብኝታቸው ከመላው ሩሲያ ቅዱስ ፓትርያርክ ክሪል ጋር ተወያይተዋል። በዚህ ወቅትም ቅዱስ ክሪል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአባቶችና በእናቶች ጥንካሬ ተጠብቃ […]

“በገድል የተፈተነ ሰማዕት”

“መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት በተናገረው ቃል መሠረት በሃይማኖት ምክንያት መከራ እየተቀበለና ስለክርስቶስ እየመሰከረ በግፍ የተገደለ ሰው ሰማዕት ተብሎ ይጠራል፡፡ ቃሉ ከግእዝ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ሰማዕት ማለት ምስክር ማለት ነው፡፡ ይህ የቅድስናና የክብር ስም የሚገኘውም እንዲሁ በከንቱ ሳይሆን ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ከብዙ ተጋድሎና ፈተና በኋላ ነው፡፡ (የሐ. ሥራ 1÷8፤ 22÷26)

የሚድያ አገልግሎትን እናጠናክር!!

በዘመኑ የአነጋገር ዘይቤ ሚድያ እየተባለ የሚጠራው የመረጃ ልውውጥ አገልግሎት በዓለማችን ዙሪያ የንግዱም፣ የማኅበራዊውም፣   የፖለቲካውም፣ የመንፈሳዊ ዓለሙም የሚጠቀምበትና የሚገለገልበት ቢሆንም እንኳን የዚህ ቴክኖሎጂ የመጀመሪያዋ መሥራች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነች የታሪክ መዛግብት ይስማማሉ፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ ሚድያ በሁለት ዐበይት ነጥቦች ሊመደብ ይችላል፡፡ አንደኛው በሥነ ጽሑፍ የሚገለጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በስዕልና በድምፅ የሚገለጥ ነው፡፡ ሥነ ጽሑፍ ሥነ ጽሑፍ በተለያዩ […]

c001

21ኛው ክፍለ ዘመን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቤተ ክርስቲያን የሚዲያ አጠቃቀም

እንደየ ዘመኑ አጠራርና አተገባበር ይለያይ እንጂ የሚዲያ አጠቃቀም ለቤተ ክርስቲያን አዲስ ነው ለማለት ባያስደፍርም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት አንፃር ሲታይ ሚዲያው ምን ያህል እንገለገልበታለን የሚለው ጉዳይ ግን አነጋጋሪ ነው፡፡ቤተ ክርስቲያኒቱ ቀደም ሲል በፕሪንትሚዲያ(ጋዜጣና መጽሔት…) በኋላም በተወሰነመልኩ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ(ሬድዮ) ትጠቀም እንደነበር የታሪክ መዛገብት ያስረዳሉ፡፡ይሁን እንጂ አሁን ባለንበት ክፍለ ዘመን ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ /ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ(ማኅበራዊ ድረ-ገፅ፤ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) በተደራሽነቱ፤በዓለም አቀፍ ስርጭቱ፤በዋጋ ቅናሽነቱ እና ዓለምን ወደ አንድ መንደር በማምጣት በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል::

በዓለ ሆሣዕና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ታላለቅ በዓላት አንዱ የሆሣዕና በዓል ነው፡፡ ስለዚህ በዓል አስቀድሞ ትንቢት ተነግሯል፤ ከትንቢቶቹም አንዱ እንደሚከተለው ተጠቅሷል፡፡ “አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ በአህያና በአህያይቱ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል” (ትን. ዘካ. 9÷9)

“ዳግም ምጽአት”

ዳግም ምጽአት የሚለው ምንባበ ቃል በብዙዎች ዘንድ ግልጥና የሚታወቅ መስሎ ቢታይም ቋንቋው ግእዝ እንደመሆኑ መጠን ወደ አማርኛ መተርጎምና መብራራት ስለአለበት ወደ ሐተታውና ጥልቀት ወዳለው ምሥጢሩ ከመግባታችን በፊት ትልቁም ትንሹም የተማረውና ያልተማረውም ሁሉም በግልጥ እንዲረዳው የምሥጢሩ ቋጠሮና ውል ያለውም በዚሁ በርእሱ ላይ ስለሆነ ርእሱን ወደ አማርኛ መተርጎም አስፈላጊና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ በዚህም መሠረት “ዳግም ምጽአት” ማለት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ወደዚህ ዓለም መምጣት ማለት ነው፡፡

0152

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አምስተኛ ዓመት በዓለ ሢመት በታላቅ ድምቀት ተከበረ!!

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ5ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ጎይቶኦም ያይኑ፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና የሥራ ኃላፊዎች ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሰንበት ት/ቤ ወጣቶች በተገኙበት ቅዳሜ የካቲት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡

810

የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ባለ 16 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መ/ር ጎይቶኦም ያይኑ፤የሀገረ ስብከቱና የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች  እንዲሁም የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት፣በቅዱስነታቸው ጸሎት የተከፈተው መርሐ ግብር በቤተክርስቲያናችን ብሎም በሐገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በመመካከር ሥራችንን እንፈትሽ፤አንድነታችንን እናጠናክር፤ቤተክርስቲያንችንን እንጠብቅና መብታችንን እናስከብር በሚል […]

pp009

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ2010 ዓ.ም ጾመ አርባአን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!! በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ወምእመናት በሙሉ፣ መሐሪና ይቅር ባይ የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥር ዓመተ ምሕረት የጾመ ኢየሱስ ሱባዔ በሰላም አደረሳችሁ!! ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ ጾምን ለዩ ምህላንም አውጁ፣ (ኢዩ 2፤15) ሁሉን ያስገኘ ፣ ሁሉንም […]

4402

የአንጋፋው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሁለገብ ሕንፃ ተመረቀ

ኮሌጁ ያስገነባው እጅግ ዘመናዊ ሁለገብ ሕንፃ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ መምህር ጎይትኦም ያይኑ እና የዋና ክፍል ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የኮሌጁ ማኅበረ ሰብ በተገኙበት ጥር 26/2010ዓ.ም በታላቅ ምንፈሳዊ ሥነ ሥርዓትና እጅግ ባማረ ሁኔታ በቅዱስነታቸው ፀሎተ ቡራኬ ተመርቋል፡፡

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት