• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

አራቱ የሃይማኖት ተቋማት የሁለቱን ሲኖዶሶች እርቀ ሰላም አደነቁ

ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ዕርቀ ሰላም መርሐ ግብር ወቅት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ገንቢ የሆነ መልእክት አስተላፈዋል የእስልምናው መሪ መልእክት የተከበረው ቅዱስ ቁርዓናችን የሰው ልጅ ክቡር ነው ይላል፤የሰው ልጅ ምንድን ነው? የሰውል ልጅ ከየት ነው የመጣ? የሰው ልጅ ለምንድን ነው የተፈጠረው? የሰው ልጅ ምን ሊሠራ ነው […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ወደ እናት አገራቸው ተመለሱ

አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትጋር ወደ ኢትዮጵያ በሰላም ገብተዋል ። ሲገቡም ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል፡፡ ከ26 ዓመታት ያላነሰ ዕድሜ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ የጥል ግንብ(ክፍፍል) በእግዚአብሔር ቸርነት፤ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በዶክተር ዐቢይ አህመድ ያላሰለሰ ጥረትና በሁለቱም ሲኖዶሳዊ ቅዱሳንና ብፁዓን አባቶች ቀና በሆነ አመለካከትና የዕርቀ […]

በአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ከሥራ የተፈናቀሉ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በሙሉ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ተወሰነ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ዶ/ር ብፁዕ አቡነ አረጋዊ እና ዋና ሥራ አስኪያጁ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ ከአድባራትና ከገዳማት አስተዳዳሪዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት ጋር በዛሬው ዕለት ከሥራ የተፈናቀሉትን ሠራተኞች አስመልክቶ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡

የውይይቱ አጀንዳ በዋነኝነት በተለያየ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው ተፈናቅለውና ታግደው ያሉትን ሠራተኞች እንዴት አድርገን መፍትሔ እንስጣቸው የሚል ነበር፡፡የሀገረ ስብከቱ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ዶ/ር ብፁዕ አቡነ አረጋዊ በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብዙ ዘመናትን ያሳለፈች፣ ብዙ ተከታይ ያላት፣ የራሷ የሆነ አስተዳደራዊ ሥርዓት የነበራትና ያላት፣ በሰላም አምባሳደርነቷ፣ በይቅርታና በመልካም ሥራዋ የምትታወቅ መሆኗን ገልጸው አሁን ግን በተለያየ ምክንያት በተፈጠረ ችግር ከውስጥ አልፎ አደባባይ ላይ በመውጣቱ ምክንያት መልካም የነበረው ስሟ በደካማ ጎን ተነሥቷል፤ ችግሩ  እንደ ችግር በፈጠርም አሁን ግን የከበረ ዝናዋን ክብሯንና ማልካም ስሟን ማስመለስ ስላለብን ለዚህም ደግሞ እናንተ የረጅም ጊዜ ልምድና ችሎታ ያላችሁ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሊቃነ መናብርት ጋር መወያየቱ እጅግ ጠቃሚ በመሆኑና ለእነዚህ አገልጋዮች መፍትሔ የሚሆን ሓሳብ እንድታግዙን ነው ሲሉ መድረኩን ከፍተዋል፡፡ በመቀጠልም ዋና ሥራ አስኪያጁ  መ/ር ይቅርባይ እንዳለ ከሥራ የተፈናቀሉት ሠራተኞ ጉዳይ አሳዛኝ መሆኑን ገልጸው ለእነዚህ አፋጣኝ ምላሽ እንዴት እንስጥ? ለወደፊት እንዲህ ያለ ችግር እንዳይደገም ምን መፍትሔ እንውሰድ በማለት የረዳት ሊቀ ጳጳሱን ሐሳብ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ በርካታ ባለጉዳዮችን ተቀብለው አስተናገዱ

ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙትን ባለጉዳዮችን በተለይም በቀጠሯቸው መሠረት የተገኙትን ባለጉዳዮች ሲያስተናግዱ ውለዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ወደ ሀገረ ስብከቱ የመጡት ባለጉዳዩች በሁለት መልኩ የሚታዩ ሲሆን በጋራ ሆነው የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ይዘው የመጡና በግል ጉዳይ የመጡ ይገኙበታል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ በመጀመሪያ በጋራ ስለ ቤተክርስቲያን ጉዳይ የመጡትን ባለጉዳዮች በቅድሚያ ያስተናገዱ ሲሆን በመቀጠልም በቀጠሮ በግል ጉዳይ የመጡትን በሚገባ አስተናግደዋል፡፡ ያለ ቀጠሮ የመጡትን ደግሞ ሐሳባውን ከተቀበሉ በኋላ ለሌላ ቀን ቀጠሮ በማስያዝ ሸኝተዋቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ይዘው ወደ ሀገረ ስብከቱ ከመጡት ባለጉዳዮች ከተሰነዘሩት ሐሳቦች መካከል የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ያለመግባባት ችግር፣ ያለመናበብ ጉዳይ ያለጨረታ የሚከራዩ የቤ/ክ ይዞታዎች፣

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ከሀገረ ስብከቱ እና ክ/ከተማ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ

ዛሬ ሐምሌ 09/2010 ዓ.ም በኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ ከብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ የመንበረ ፓትርያርክ የውጭ ጉዳይ የበላይ ሐላፊ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ከሀገረ ስብከቱና ከክፍለ ከተማ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ ካደረጉ በኋላ የሥራ አመራርም ሰጥተዋል፡፡

የዛሬ ዓመት ሐምሌ 09/2009 ዓ.ም በዓለ ሲመታቸው እንደነበረ ያወሱት ሊቀ ጳጳሱ ፣ በዘንድሮ ደግሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሆኜ ለአገልግሎት መሾሜ እግዚአብሔርን አመስግነዋለሁ በማለት በታማኝነት፣ በቅንነትና በመንፈሳዊነት ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሌሎች አሁረ ስብከት ለየት የሚያደርገው የሀገራችን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ ሀ/ስብከት እንደመሆኑ መጠን ብዙ የዲፕሎማትና ሙሁራን የሚገኙበት በመሆኑና ብዙ ውስብስብ የሆኑ አሠራር ያሉበት ሀ/ስብከት ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋገር መግለጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአሜሪካ ለሚደረገው ዕርቀ ሰላም ሶስት ሊቃነ ጳጳሳት እንደምትልክ የቤተክርስቲያኒቷ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ አስታወቁ።

በ1984 ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 4ኛው ፓትርያርክ መንበራቸውን ለቀው ከተወሰኑ አባቶች ጋር ከሃገር በመወጣታቸው በቤተ ክርስቲያኗ ለ26 ዓመታት ምዕመናን እያዘኑ በከፍተኛ የሰላም እጦት ውስጥ ማሳለፏን ቅዱስነታቸው ገልፀዋል።የጠፋውን ሰላም ወደ ነበርበት እንዲመለስ ለማድረግም ቤተ ክርስቲያኗ ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ጥረት ስታደርግ መቆየቷን ነው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የተናገሩት።

በ2010 ዓመተ ምህረት ጥቅምት ወር የቤተ ክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔን ተከትሎ በራሱ ተነሳሽነት ከካህናትና ምእመናን የተወጣጣ የሰላም ኮሚቴ ያቀረበውን የዕርቅ ጥያቄ ተቀብሏል።

በዚህም መሰረት ከሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በአባቶች መካከል የሚካሄደውን የዕርቅ ሰላም ሂደት ፍፃሜ በማግኘት በውጭ የሚገኙ አባቶች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲመለሱ ሶስት ሊቃነ ጳጳሳትን ወደ ስፍራው ያቀናሉ ነው ያሉት።

አሁን በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረውን ዕርቀ ሰላም ያለምንም መሰናከል ለውጤት ይበቃ ዘንድ ዕርቀ ሰላሙን አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶሰ ፈቃድ ከሰጠው አካል በስተቀር መግለጫ መሰጠት ጠቃሚ አለመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ

ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት ጳጳስ ሆነው በመመደባቸው ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ለብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ የመንበረ ፓትርያርክ ውጭ ጉዳይ የበላይ ሓላፊ ባአድራሻቸው በተጻፈላቸው የሹመት ደብዳቤ እንደተገለጸው ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሠረት ብፁዕነታቸው ከሐምሌ ወርህ 2010ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወርህ 2011 ዓ/ም ድረስ ሀገረ ስብከቱን በጊዜአዊነት ረዳት ጳጳስ ሆነው ይመራሉ፡፡ በአቀባበል ሥርዓቱ ወቅት የእንኳን ደስ አለን መልእክት ያስተላለፉት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ይቅርባይ እንዳለ እንዳብራሩት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በሚመለከት ጉዳይ አጣሪዎች ተመድበው እስከ አሁን እያጣሩ ነው ያሉት፤በሀገረ ስበከቱ ጉዳይ ቤተ ክርስቲያንዋ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሥር ከመውደቋም በላይ በተለያዩ ስብሰባዎች ስሟ በክፉ ሲነሣ ስለነበር ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህን ተገንዝበው መመሪያ ሰጥተውበት እኛን ዋና ሥራአስኪያጅና ምክትል ሥራአስኪያጅ አድርገው ልከውናል፡፡መዋቅሩ ተሟልቶ ሥራ እንድንጀምር ረዳት ጳጳስ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ ዘመናዊ የአስተዳደር

ለመምህር ይቅርባይ እንዳለ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወልደ ሐና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

በቅዱስ ፓትርያርኩ መልካም ፈቃድ ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ/ም በዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመደቡትን መ/ር ይቅርባይ እንዳለንና ምክትላቸውን መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወልደ ሐናን በሀገረ ስብከቱ የስብሰባ አዳራሽ የአቀባበል መርሐ ግብር ተደረገላቸው፡፡

ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ  ዲዮስቆሮስና ሌሎችም ሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች፤ የክፍላተ ከተማ ሥራ አስኪያጆችና የየክፍሉ ሐላፊዎች፤ እንዲሁም የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳደሪዎችና ጸሐፊዎች በተገኙበት በተደረገው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ብፁዕ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስ የሹመት ደብዳቤውን በንባብ ካሰሙ በኋላ ² ልጁ የእኛው ጽ/ቤት የሥራ ባልደረባና አስተዋይ ልጅ ነው ፤በዛሬ ቀን ደግሞ ሙሽራ ስለሆነ እኛ የእርሱ አጃቢ ሚዜዎች ሆነን በዚህ ተገኝተናል  በማለት የመክፈቻ ንግግራቸውን ጀምረው በአሁኑ ጊዜ መሆን ሰለሚገባው አሠራር ሲገልጹም በአለንበት በዚህ ወቅት ቤተ-ክርስቲያናችን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፤ በሩን ለባለጉዳዮች ክፍት አድርጉ ነገር ግን የጊዜውን ሁኔታ ለራሱ ለጊዜ እንተውለት ጊዜ ራሱ በጊዜው ይናገራል በሚል ተጨማሪ በሳል ሐሳብም

መምህር ይቅርባይ እንዳለ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወ/ሐና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተመደቡ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ሓላፊ ሆነው ሲሠሩ የቆዩት ሰባኬ ወንጌል መምህር ይቅርባይ እንዳለ በቁጥር 113-28/2010 በቀን 20/10/2010 ዓ.ም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት በተጻፈ ደብዳቤ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት በሆነው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በዋና ሥራ አስኪያጅነት ተመድበዋል፡፡
ለዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ይቅር ባይ እንዳለ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የተጻፈላቸው የሹመት ደብዳቤ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሲሆን መልካም አስተዳደርን በማስፈን፣ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፣ ካህናትንና ማኅበረ ምዕመናንን፣ በፍቅርና በአንድነት በመምራት፣ ሰንበት ት/ቤቶችን በማጠናከርና በማደራጀት፣ የሀገረ ስብከቱን የልማት ሥራ በማጠናከርና የቃለ ዓዋዲውን መመሪያ መመሪያ በማስፈጸም የተሰጣቸውን ከባድ ሓላፊነት በትጋትና በብቃት

0012

አ/አ/ሀ/ስብከት“የሕጋዊነት መርሕ”በሚል ርእስ ለገዳማትና አድባራት የሥራ መሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ጥናታዊ ውይይት አካሄደ

ሀገረ ስብከቱ ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ.ም ከገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሒሳብ ሹሞች ጋር የሕጋዊነት መርሕ በሚል ርእስ ለግማሽ ቀን የቆየ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጥናታዊ ውይይት አድርጓል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ጎይቶኦም ያይኑ በውይይቱ መክፈቻ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት በአሁኑ ጊዜ ሀገረ ስብከቱ ሆስፒታል ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ሆስፒታል በየቀኑ በሽተኞች ይታዩበታል እና ነው፡፡ ባለ ጉዳዮቹ ሥራ አስኪያጁን ማግኘት አልቻልንም በማለት ያማርራሉ፡፡ በየደረጃው ያሉ የሥራ ሐላፊዎች ባለጉዳዮችን በአግባቡ ማስተናገድ አለባቸው፡፡ ጉዳዩንም በወቅቱ መፈጸም አለባቸው በማለት አብራርተዋል፡፡  
የመወያያ ጥናቱን ያቀረቡት የሀገረ ስብከቱ የሕግ ክፍል ሐላፊ መምህር ባሕሩ ተፈራ ባቀረቡት የመወያያ ጥናታዊ

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት