• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ2008 ዓ.ም ዐቢይ ጾምን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በእንተ በዓተ ጾም ዓቢይ ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በተለያዩ ክፍላተ ዓለም የምትገኙ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ፤
ምሕረቱ የበዛ መዓቱ የራቀ ቸርና ሰው ወዳጅ የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት የጌታችን፣ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ጾም ዓቢይ በሰላም አደረሳችሁ !!
‹‹ወአንሰ መጻእኩ ከመ ይርከቡ ሕይወተ ወፈድፋደ ይርከቡ፣ እኔ የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲያገኙ መጣሁ›› (ዮሐ10፡10)
ይህ ቃል የሕይወት አስገኚና ሰጪ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ዘላቂና ዘላለማዊ ሕይወት ሊሰጥ ሰው ሆኖ ወደሰዎች እንደመጣ ሲያመለክት የተናገረው ቃለ አድኅኖ ነው ፡፡
ለፍጡራን ሁሉ ትልቁና የመጀመሪያው ጸጋ ሕይወት ነው፤ ሰውም ሆነ ሌሎች ፍጥረታት በዚህ ዓለም ሲወጡና ሲወርዱ የሚገኙት ሕይወትን ለመንከባከብ፣ ለመጠበቅና ለማስቀጠል ነው፤
ምክንያቱም ሕይወት ካለ በሕይወት መሣሪያነት ሁሉም ይገኛል፤ ሕይወት ከሌለ ግን ሁሉም የለምና ነው ፡፡
በመሆኑም ሕይወት በፍጡራን ዘንድ ተወዳዳሪና መተኪያ የሌላት ሀብት ናትና ሙሉ ጥበቃና እንክብካቤ ሊደረግላት ይገባል ፤
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንንና ነፍሳችንን በመዋሐድ ፍጹም አምላክ፣ ፍጹም ሰው ሆኖ በዓለም ላይ የተገለጠው ሕይወታችንን ለመጠበቅ፣ ለመንከባከብና ለማዳን ነው ፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ተገልጦ ይመላለስ በነበረበት ጊዜ ሕይወትን አጥተው በጉስቁልና የነበሩ የተለያዩ ሕሙማን ሕይወተ ሥጋን እንዲያገኙ አድርጎአል፤
ሕይወተ ነፍስን አጥተው የነበሩትም በሕያው ትምህርቱ ተስፋ ሕይወትን እንዲላበሱ አድርጎአል፤ ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ሙታን ሕይወታቸውን ተጎናጽፈው ከመቃብር እንዲነሡ አድርጎአል፤ በእነዚህ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት ራስ መሆኑን ከመግለጽ ጋር ለሰው ልጆች ሁሉ ሕይወትን ለመስጠት እንደመጣ በትምህርትም በተግባርም አሳይቶአል ፡፡
ከዚህ አንጻር ሕይወት በፈጣሪም ሆነ በፍጡራን ምን ያህል ታላቅ ዋጋ እንዳላት

ሥርዓተ ጸሎት በኢ.ኦ.ተ.ቤተ ክርስቲያን

                                                             ሥርዓተ ጸሎትጸሎት፡-ቃሉ ግእዝ ነው ጸለየ ለመነ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጸሎት፡- ማለት ልመና  ነው፡ጸሎት ምስጋናም ነው ‹‹ይትቀደስ ስምከ›› (ስምህ ይቀደስ) ስንል ምስጋና ነው ‹‹ሲሳየነ ዘለለእለትነ ሀበነ ዮም›› (የእለት ምግባችንን ስጠን ዛሬ) ስንል ደግሞ ልመና  ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት፡- ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14) በምን አይነት መንገድ መጸለይ እንዳለብን ከዚህ እንደሚከተለው […]

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ሦስተኛ ዓመት በዓለ ሢመት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 3ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳሳት፤ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኢፌዴሪ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀማዕምራን የማነ  ዘመንፈስቅዱስ  ፤የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያና የየድርጅቱ ኃላፊዎች ፤አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት  ልዩ  ልዩ የሥራ ኃላፊዎች፤ […]

0029

የአርሲ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል አረፉ

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር።ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባገኘነው መረጃ፥ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በትናንተናው እለት ከቀኑ 10 ሰዓት ከ30 ላይ በአሰላ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነው ያረፉት። ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በምሥራቅ ትግራይ ክለተ አውላሎ አውራጃ አውዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሕይወት ፀዓዱ […]

m0005

የአዲስ አበባ ገደማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል በማኅበረ ቅዱሳን ኢመዋቅራዊ አደረጃጀትና የሥራ ግድፈቶች ላይ ባለ 19 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጣ

ብዛቱ እስከ 2000 የሚገመተው ይህ ጉባኤ የካቲት 17 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ በመገኘት ማህበረ ቅዱሳን በመዋቅር የለሽ አሠራሩ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ  በርካታ ችግሮችን እየፈጠረ መሆኑን በማስመልከት አስፈላጊው ርምጃ ይደረግበት ዘንድ ጉባኤው በስፋት ከተወያየ በኋላ ባለ 19 ነጥብ  የአቋም  መግለጫ አውጥቷል፡፡ የስብሰባውን ቃለ ጉባኤ እና አቋም መግለጫ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡በጉባዔው መጀመሪያ የጉባዔው […]

0110

ለአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎች የካህናትና ምዕመናን አመዘጋገብን አስመልክቶ ለግማሽ ቀን የቆየ ሥልጠና ተሰጣቸው

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ በተዘጋጀ የምዕመናን አመዘጋገብና የቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት አመዘጋገብ ጥናታዊ ዝግጅት የካቲት 10 ቀን 2008 ዓ.ም ቁጥራቸው 1000 ለሚደርሱ የገዳማትና አድባራት ተወካዮች ለግማሽ ቀን የቆየ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ባደረጉት የመክፈቻ ገለፃ ይህ ሥልጠና መሠረታዊና […]

999

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቤተክርስቲያንን መንፈሳዊ አገልግሎት አስመልክቶ ከአብነት መምህራን ጋር ውይይት አካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት በመምህርነት ሥራ ተመድበው ከሚያገለግሉ የአብነት መምህራን ጋር ረዕቡ የካቲት 9 ቀን 2008 ዓ.ም ለግማሽ ቀን የቆየ የጋራ ምክክርና ውይይት አካሂደዋል፡፡ የውይይቱና ምክክሩ አጀንዳ ከፊታችን የሚጠብቀንን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ዓቢይ ጾም አስመልክቶ የስብሐተ ነግህ አገልግሎት በማይካሄድባቸው ገዳማትና አድባራት የስብሐት ነግህ አገልግሎት እንዲካሄድ፣ […]

640

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዋና ክፍል የወጣ ክፍት የሥራ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሲሠራበት የነበረውን ለማዳዊ አሠራር ወደ ዘመናዊ የአስተዳደር ሲስተም መቀየሩን ተከታትሎ አመርቂ ውጤት ከተገኘባቸው የሥራ አይነቶች መካከል የሠራተኛ ቅጥርና ዝውውር እንዲሁም የዕድገት አሰጣጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡ ሀገረ ስብከቱ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በወሰዳቸው እርምጃዎች ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ መምህራንን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን አወዳድሮ መቅጠር በመጀመሩ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብሎም ምእመናን […]

000340

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ክርስትና ካልተስፋፋባቸው ብሔር ብሔረሰቦች ካህናትን ለማፍራት እየሠራ ነው

ፎቶ ፋል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ክርስትና ያልተስፋፋባቸው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ለማስፋፋት ከየብሔረሰቡ ካህናትን ለማፍራት ተግቶ እየሠራ መሆኑ ተገለፀ፡፡የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እንደገለፁት ከጋምቤላ ክልል 18 ከደቡብ ሱዳን 3 ደቀመዛሙርትን መልምሎ ከትውልድ አካባቢያቸው ድረስ ሄዶ በማምጣት በአዲስ አበባ ከተማ በሰዓሊተ ምሕረት ቅድስተ ማርያም የአብነት ት/ቤት በአደራነት አስገብቶ […]

00230

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለአህጉረ-ስብከትና ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማት እገዛ እያደረገ ነው

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ በከፊል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ራሱ ካለበት ዘርፈ ብዙ ሥራዎች በተጨማሪ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ዕድገት ለሚያፋጥኑ እንዲሁም ወቅታዊ ችግር ላለባቸው አህጉረ ስብከትና የልማት ተቋማት ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ባለፉት 6 ወራት ብር 8,000,000.00 (ስምንት ሚሊየን ብር) የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል፡፡ ድጋፍ ከተደረገላቸው ውስጥ በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለሚመራው […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን