• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ትምህርተ ሃይማኖት ዘቅድስት ሥላሴ

ለክርስትና ሃይማኖት መሠረቱ ማእከሉና መደምደሚያው ምሥጢረ ሥላሴ እንደሆነ ይታወቃል ምክንያቱም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ነሥቶ ሰው ከሆነ በኋላ የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት የታወቀና የተረዳ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ ይህም በዚህ በልደት እና በጥምቀት ሰሞን በቂ ትምህርት ሊሰጥበት የሚገባ ነው፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ከቅድስት ድንግል  ማርያም ሰው ሆኖ በሥጋ  ከመወለዱ […]

pp009

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ2009 ዓ.ም የልደት በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

ቃለ በረከት  ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በእንተ በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት!! በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!! -በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ -ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ -የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ […]

1

“የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል”

ከ605 እስከ 562 ዓመተ ዓለም በባቢሎን የነገሠው ናቡከደነጾር ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፤ ንጉሥ ናቡከደነጾር መኳንንትንና ሹማምንቶችን፣ አዛዦችንና አዛውንቶችን፣ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣አውራጃ ገዢዎችንም ሁሉ ይሰበሰቡ ዘንድ ንጉሡም ናቡነከደነጾር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምንቱ አዛዦቹና አዛውንቶቹ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዢዎቹ ሁሉ […]

“ይኩንኪ በከመ ተአመንኪ” (እንዳመንሽ ይሁንልሽ)

ይህ ቃል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለከነናዊት ሴት የተናገረው ቃል ነው፡፡ ታሪኩም/በማቴዎስ ወንጌል ም. 15፡21-28/ ላይ ይገኛል፡፡ ታሪኩም እንደሚከተለው ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ፡፡ በዚያም ከነናዊት ሴት ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ ማረኝ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዟታል ብላ ጮኸች፡፡ እርሱ ግን ለጊዜው አንዳች አልመለሰላትም፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ […]

p033

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በሕንድ ኬሬላ ለስድስት ቀናት ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቅቀው ተመለሱ

                                                                                                  በመምህር ሙሴ ኃይሉ ከአምስቱ አኀት አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ ካቶሊኮስ ባስልዮስ ማርቶማ ጳውሎስ ዳግማዊ የህንድን ቤተ ክርስቲያን እንዲጎበኙ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት ጎብኝተዋል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ ኬሬላ አየር ማረፊያ ሲደርሱም […]

20090

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በ2008 ዓ.ም የበጀት ዓመት ባስመዘገበው ከፍተኛ የፐርሰንት ገቢ እድገት ልዩ ተሸላሚ መሆኑ ተገለጸ!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በ2008 ዓ.ም የበጀት ዓመት በርዕሰ ከተማው ከሚገኙት ገዳምትና አድባራት በሰበሰበው የላቀ የፐርሰንት ገቢ እድገት በ2009 ዓ.ም በተካሄደው 35ኛ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ልዩ ተሸላሚ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ሀገረ ስብከቱ በ2007 ዓ.ም ካስመዘገበው የፐርሰንት ገቢ የብር 30 ሚሊዮን ብልጫ በማሳየት ልዩ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ ሀገረ ስብከቱ በ2008 […]

“የመስቀሉ ነገር ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚብሔር ኃይል ነው” 1ኛ. ቆሮ. 1÷18

መስቀል፡- ምስጢራዊ ትርጉሙ መከራ ማለት ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል ‹‹ዘኢጾረ መስቀለ ሞትየ ኢይክል ይጸመደኒ›› (የሞቴን መስቀል የማይሸከም ይከተለኝ ዘንድ አይችልም) /ማቴ. 16÷24/ ሲል የተናገረው ቃል መስቀል መከራ መሆኑን የሚገልጽ ነው፡፡  ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ከተሰቀለ በኋላ ሕሙማን መስቀሉን እየዳሰሱ በመስቀሉ እየታሹ ይፈወሱ ነበር፡፡ በዚህ በመስቀሉ በሚደረገው ተአምራት እየተሳቡ […]

0012

የመ/ፓ/ጠ/ ቤተ ክህነት የደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ከአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ተወካዮች ጋር ለግማሽ ቀን የቆየ ውይይት አካሄደ

በ2009 ዓ.ም የሚከበረውን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ለማድረግ በማሰብ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዓርብ መስከረም 13 ቀን 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከ1000 ከማያንስሱ ከሁሉም ገዳማትና አድባራት ከመጡ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ለግማሽ ቀን የቆየ ምክክርና የውይይት መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡ በውይይቱ መርሐ ግብር የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት መጋቤ ካህናት […]

00180

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የ2009 ዓ.ም የሥራ እቅዱን ይፋ አደረገ!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይኖት የ2009 ዓ.ም ዓለም አቀፋዊ የሆነውን ሐዋርያዊ እና አስተዳደራዊ አገልግሎትን አስመልክቶ በልዩ ጽ/ቤት የተዘጋጀው ሰፊ የሥራ እቅድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የአስተዳደር ጉባኤ መሰብሰቢያ አዳራሽ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት ሐሙስ መስከረም 5 […]

1003

የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የ2009 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ አቀረቡ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰባቱ የክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤቶች የ2009 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሥራ ዕቅድን አስመልክተው የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ጎይቶኦም ያይኑ እና የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ረቡዕ ነሐሴ 4 ቀን 2009 ዓ.ም ለግማሽ ቀን የቆየ የሥራ ዕቅድ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች  […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን