• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የቦሌ ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተቀመጠ

በዕለቱ የመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች፤የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የሀገረ ስብከቱ የየዋና ክፍል ኃላፊዎች እና የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ንቡረ ዕድ አባ ዮሐንስ እንዲሁም የክፍለ ከተማው የስራ ኃላፊዎች የመንግሥት ተወካዮች ከአራቱም አቅጣጫ […]

ሰበር ዜና በ22 አካባቢ ለ2 ወጣቶች ሞት ምክንያት የሆነው ቦታ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተሰጠ

በአዲስ አበባ 22 አካባቢ በመንግሥት ታጣቂዎች ምእመናን በግፍ የተገደሉበትና በፈረሰው ቤተ ክርስቲያን ላይ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቤተ ክርስቲያን እንዲሰራበት ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ተሰጥቷል ። ይህን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ በክቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የተመራ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ በቦታው […]

አዲሱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከሀገረ ስብከቱና ከክፍላተ ከተማ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ

በትውውቅ መርሃ ግብሩ ላይ የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የክፍላተ ከተሞች ሥራ አስኪያጆችና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡ “የእንኳን ደህና መጡ መልእክትም” ለክቡር ሥራ አስኪያጁ አስተላልፈዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በተደረገው ውይይት ሀገረ ስብከቱ ያሉበትን ዘርፈ ብዙና ውስብስበ ችግሮች፣ እንዲሁም ብለሹ አሠራሮችና የወደፊት የመፍትሔ አቅጣጫዎች ይሆናሉ ተብለው የታሰቡት ለክቡር ሥራ አሥኪያጁ ተጠቁመዋል፡፡በየጊዜው ሥራ አስኪያጆችን እየተቀበለ መሸኘትን ልማዱ ያደረገው […]

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፯ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ዛሬ የካቲት 24 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች፣ የየድርጅቱ ኃላፊዎች፣ የመንፈሳዊ ኮሌጆች ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የየክፍሉ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃነ መናብርት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና  ምእመናን በተገኙበት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ […]

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመደቡት 27ኛው ተሿሚ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ በሀገረ ስበከቱ የስብሰባ አዳራሽ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት በሀገሪቱ ርእሰ መዲና አዲስ አበባ ከተመሠረተ ጀምሮ የበርካታ ሥራ አስኪያጆችን ታሪካዊ አሻራ አስተናግዶ አሁን ደግሞ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃ/ገብርኤል ነገሽን 27ኛው የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሾሟል። ላለፉት 12 ወራት ጽ/ቤቱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት ሲመሩት የነበሩት መልአከ ሕይወት አባ ሞገስ ኃ/ማርያም የካቲት 20/2012 ዓ/ም ተሰናብተው በምትካቸው ደግሞ የምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ […]

መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኀይለ ገብርኤል ነጋሽ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተመደቡ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበሩት መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኀይለ ገብርኤል ነጋሽ በቁጥር 3136/2012 በቀን 20/06/2012 ዓ.ም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት በተጻፈ ደብዳቤ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት በሆነው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በዋና ሥራ አስኪያጅነት ተመድበዋል፡፡ ለዋና […]

ጾም በክርስትና ሕይወት

በዚህ ትምህርታዊ ጹሑፍ ስለ ጾም አራት ነጥቦችን እናያለን የጾም ትርጉም ጾም ያስፈለገበት ምክንያት የጾም ጥቅሞች በምን ዓይነት መንገድ መጾም እንዳለብን፡፡ ከላይ ከ1-4 ተራ ቊጥር የተገለጹትን እንደሚከተለው በዝርዝር እናያለን፡፡ 1ኛ/ የጾም ትርጉም ጾም፡- ማለት ክርስቲያን የሆነ ሰው ሁሉ ለተወሰነ ጊዜና ሰዓት ከእህል ከውኃ ተከልክሎ መቆየት ማለት ሲሆን ከሥጋ፣ ከቅቤና፣ ከእንቁላል ደግሞ እንድንጾምባቸው የተወሰኑ የአጽዋማት ሳምንታት እስኪጠናቀቁ […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረገች

“በጎውን ማን ያሳየናል” በሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መነሻነት ወቅታዊና አንገብጋቢ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ መምህራነ ቤተክርሰቲያን፣ የዘርፉ ምሁራን ፣የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል ሰፊ ምክክርና ውይይት ተከናውኗል፡፡መርሐ ግብሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ […]

በጸጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት የተገደሉት ሁለት ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ሥርዐተ ቀብር ተፈጸመ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በቦሌ ክፍለ ከተማ ሥር በሃያ ሁለት አካባቢ ቀበሌ ሃያ አራት ልዩ ስሙ አፍሮ ጽዮን አዋሳኝ በሚባለው ባዶ ሥፍራ ዙሪያ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ተከታይ ምዕመናን ይሆን ዘንድ የአምልኮ ሥፍራ ማለትም ቤተ-ክርስቲያን ለመስራት በአካባቢው ምዕመናን ትብብር ጊዜያዊ መጠለያ ሠርተው በተቀመጡት አማንያንና ቦታው ለአረንጓዴ ልማት የተከለለ ነው በሚሉ የጸጥታ አካላት መካከል […]

በዓለ አስተርእዮ

አስተርእዮ፡– ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ አስተርእዮ ማለትም መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው፡፡ በግሪክ ቋንቋ ኤጲፋንያ ይባላል ኤጲፋንያ ማለት መገለጥ፤ መታየት ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ዘመን ዘመነ አስተርእዮ ይባላል የመገለጥ፣ የመታየት ዘመን ማለት ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው ሆኖ የተገለጠበት ዘመን ስለሆነ እና እንዲሁም በጥምቀቱ አንድነቱን ሦስትነቱን […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት