• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የ2012 ዓ/ም ዓመታዊ የፐርሰንት አሰባሰብን አስመልከቶ ውይይት ተካሄደ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብሰባ አዳራሽ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ፤ የሀገረ ስብከቱ የየዋና ክፍል ኃላፊዎች፤የሁሉም ክፍላተ ከተሞች ሥራ አስኪያጆችና ሠራተኞች እንዲሁም የአድባራትና ገዳማቱ አስተዳዳሪዎች፤ ሊቃነ መናብርትና ሒሳብ ሹሞች በተገኙበት ዓመታዊ የፐርሰንት ገቢ ካላጠናቀቁ አድባራትና ገዳማት ጋር ውይይት ሰኔ 4/2012 ዓ/ም ተደርጓል፡፡ወቅታዊውን የኮረና ወረርሽኝ ለመከላከል ሲባል የውይይት መርሐ ግብሩ […]

ጾመ-ሐዋርያት

“ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምሕላ ጾምን ለዩ ምሕላንም አውጁ“ (ኢዮ 1÷14)ጾም የሚለው ቃል “ጾመ“ ተወ ፤ታቀበ፤ ታረመ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ጥቅል ትርጉሙም ጥሉላትን መባልዕትን ፈጽሞ መተው መከልከልና መወሰን ወይም ደግሞ ሰውነትን ከሚያምረውና ከሚያስጎመጀው መብልና መጠጥ እንዲሁም ከክፉ ነገር ሁሉ ራስን መጠበቅ መቆጣጠርና መግዛት ማለት ነው፡፡ ጾም የመላ ሰውነታችንን መታዘዝ የሚጠይቅ መንፈሳዊ ተግባር እንጅ በተወሰኑ […]

በአዲስ መልክ የተሠራው የጉራራ ኪዳነ ምሕረት ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ተመረቀ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት የሚገኘው የጉራራ ምስራቀ ፀሀይ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ግንቦት 29/2012ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ ተፈጽሞ ተመርቋል። በምረቃው ሥነስርዓት ላይ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከተ ሊቀ ጳጳሰ ብፀዕ አቡነ እንጦስ ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መልአከ ህይወት አባ ኃይል ገብርኤል ነጋሽ ፣ የደብሩ […]

የ2012 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ መርሐ ግብር ተካሄደ

ግንቦት 28/2012 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ፤ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስከያጅ እና የሐይማኖት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ተካሂዷል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ብፁዕ […]

በዓለ ጰራቅሊጦስ

“ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም” /ዮሐ.14÷18/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኙ ዐበይት (ታላላቅ) በዓላት መካከል አንዱ የጰራቅሊጦስ በዓል ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ ግሪክ ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት መጽንዒ በእምነት የሚያጸና፣ መንጽሒ ከኃጢአት የሚያነጻ፣ ናዛዚ ያዘኑትን የሚያረጋጋ፣ መስተፍሥሒ፣ ያዘኑትን የሚያስደስት፣ ከሣቲ ምስጢርን የሚገልጽ ማለት ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ፡- መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ የጰራቅሊጦስ በዓል ታሪክ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ […]

በቦሌ ቡልቡላ ፈለገ ዮርዳኖስ ቅዱስ ሚካኤል እና አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ችግኝ ተከላና የእርዳታ መርሐ ግብር ተካሄደ

❖ ገዳሙን የአንድነት ገዳም ለማድረግ ታቅዷል፤❖ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳሙ የማጠናከር ድጋፍ ያደርጋል ። የቡልቡላ ፈለገ ዮርዳኖስ ቅዱስ ሚካኤል እና አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ብዙ ዋሻዎች ያሉት ፈዋሻ ጸበል የፈለቀበት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለ ልዩና ድንቅ መንፈሳዊ ቦታ ነው። ግንቦት 19/09/2012 ዓ.ም በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ […]

የተስፋ ልዑክ ዐቢይ ኮሚቴ ሪፓርትን በተመለከተ የሀገረ ስብከቱ ምላሽ

ዓለም አቀፋዊ የኮሮና ወረርሽኝን ተከትሎ ስርጭቱን ለመቀነስና ለመግታት ከዚህ ቀደም ምእመናን በቤታቸው በጸሎት እንዲተጉ በቋሚ ሲኖዶስ የተወሰነውን ውሳኔ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቀን 5/9/2012 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ በድጋሚ ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ መክሮ እና አፈጻጸሙን ገምግሞ ወረርሽኙን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ በባለሙያዎች የሚሰጠውን ጥንቃቄ በማድረግ ምእመናን በአምልኮተ እግዚአብሔር እንዲሳተፉ ወስኗል፡፡ቋሚ ሲኖዶስ የወረርሽኙን ሥጋት ተከትሎ ምእመናንን ለመታደግ በሚል […]

የአ/አ/ሀ/ስ/ ዋና ስራ አስኪያጅ መ/ሕ/ አባ ኃይል ገብርኤል ነጋሽ በተለምዶ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመሠራት ላይ ያለው የቦሌ ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ገብርኤል ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ጎበኙ

ይህ ቦታ ከወራት በፊት የሁለት ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞች ሕይወት የጠፋበትና የበርካታ ክርስቲያኖችም አካል የጎደለበት እንዲሁም የብዙ ምእመናን ልብ የተሰበረበት ቦታ የነበረ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤተ ክርስቲያኒቱ እና የምእመናኑ ጥያቄ ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ በፈቀደው መሠረታ ሁለቱ ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞች ሕይወት በጠፋበት ቦታ የቅድስት አርሴማና የቅዱስ ገብርኤልህንፃ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰራ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ርዕሰ […]

በቤቴል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በሰላም ለመፍታት ከስምምነት ላይ ተደረሰ

ቤቴል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በኮልፌ ቀራኒዮ ክርለ ከተማ የሚገኝ ሲሆን በሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት ሠራተኞች ከአከባቢው ምዕመናን ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ የአስተዳደር ሠራተኞች ቢሮ ለ3ቀናት ያህል ታሽጎ መቆየቱ ይታወቃል። በዚሁ መነሻነት ዛሬ ሚያዝያ 21/2012 ዓ.ም መልአከ ሕይወት አባ ኀይለ ገብርኤል ነጋሽ (ቆሞስ)የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ በደብሩ በመገኝት ከካህናትና ከምዕመናን ተወካዮች […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃይለገብርኤል ነጋሽ(ቆሞስ) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጡ

“አምጣነ ብነ ዕለተ ንግበር ሠናየ ለኵሉ ወፈድፋደሰ ለሰብአ ሃይማኖት” “እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተሰዎች መልካም እናድርግ፡፡” ገላ.6፡10 መልካም ማድረግ ከበጎ አስተሳሰብ፣ ከመልካም ስብእና ይመነጫል፡፡ በዚህ ዘመን ዓለማችን በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ምከንያት በተረበሸችበት ወቅት፤ በበሽታው ምክንያት ለተጎዱ፣ ቀን ለጎደለባቸው፣ ወገኖች ሁሉ የበኩላችንን ድጋፍ ማድረግ ለሰው ልጆች ሁሉ የተገባ ግብረ ገባዊ (ሞራላዊ) […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት