• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

በወቅታዊ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ስለ ወቅታዊ ኹኔታ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን

በአገር ውስጥና በውጭ አገር የምትኖሩ፣ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሆይ፤

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅድመ ታሪክ ዘመን አንሥቶ ህልውናዋ፣ ታሪክዋ፣ ገናናነትዋ፣ ታላቅነትዋና ሥልጣኔዋ በዓለም ዘንድ የታወቀ ታላቅና አኩሪ ሀገር ናት፡፡ ለታላቅነትዋ ዓቢይ አስተዋፅኦ ካበረከቱት መካከል፥ በፈሪሀ እግዚአብሔር እና በአምልኮተ እግዚአብሔር የተገነባ፣ ስለ ሃይማኖቱና ስለ አንድነቱ ፍንክች ሳይል በአንድነትና በጽናት የቆመ ሕዝብ ያላት መኾኑ ነው፡፡

በዚህ የሃይማኖት ሥርዐት፣ የዜጎች የማይበጠስ አንድነትና ማኅበራዊ መስተጋብር ጸጋ፣ ሀገሪቱ ከውጭ ወራሪዎች የሚደርስባትን ማንኛውንም ጥቃት በሚገባ እየመከተች እስከ አኹን በኀያልነት ዘልቃለች፡፡

በዚህም የዓለም ኹሉ ጸሐፍትና ምሁራን፥ ብቸኛ የኾነ አንጸባራቂ ታሪኳን፣ ማንነትዋንና ነጻነትዋን በደማቅ ቀለም ጽፈውላታል፡፡በቀላሉ ተዝቆና ተተንትኖ የማያልቅ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ታሪኳ በዓለምና በአፍሪቃ ጎልቶ ሊወጣ የቻለው ሕዝቦቿ በሃይማኖት፣ በዘር፣ በቀለም፣ በመልክዐ ምድር፣ በባህልና በጥቃቅን ምክንያቶች ለሚፈጠሩ ልዩነቶች ቦታ ሳይሰጡ ዘላቂና የጋራ ጥቅማቸውን ለሚያረጋግጥ ሀገራዊ አንድነት ከማንም በፊት ቅድሚያ ሰጥተው እንደ ችቦና እንደ ነዶ አንድ ላይ በመቆማቸው እንደኾነ ታሪካችን አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡

በተለይም በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ፥ ለምሥራቅ አፍሪቃ አልፎም ለመላው አፍሪቃና ለመላው የዓለም ጥቁር ሕዝቦች ተምሳሌት የሚኾን አንጸባራቂ የልማት፣ የአንድነትና የመልካም አስተዳደር ስኬት ታረጋግጣለች ብሎ የዓለም ሕዝብ ተስፋ በጣለበት ወቅት፣ ዜጎች ለታሪካቸው፣ ለባህላቸውና ለሃይማኖታቸው የማይመጥን ሰብእና እንደዚሁም በዓለም ሕዝብ ፊት ኃፍረትና ጸጸት የሚያስከትል ተግባር እንዳይፈጽሙ በእጅጉ

ጾመ ፍልሰታ

ጾም ምንድነው?

ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ ለአንድ የተወሰነ ጊዜ መተው ወይም መከልከልና መቆጠብ  ማለት ሲሆን የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች ከእግዚአብሔር ጋር ከሚገናኙባቸው የግንኑነት መስመሮች መካከል አንዱ ነው፡፡የሰው ልጅ ግንኙነቱ የሠመረና በበረከት የተሞላ ደግሞም ለንስሐ የሚያበቃ ሕይወት ይኖረው ዘንድ በማቴ 6÷1-19 የተቀመጡለትን የግንኙነት መስመሮች በአግባቡ መተግበርና በሕይወቱ መተርጎም አለበት፡፡

እነዚህም የግንኙነት መስመሮች ስትመጸውቱ ፤ስትጸልዩ እና ስትጦሙም በማለት ከአሁን በፊት አይሁዳውያን ያደርጉት እንደነበር  ከጠቆመ በኋላ በክርስቲኖች ዘንድ ግን የድርጊት ማስተካከያና አቅጣጫ የሚያስፈልገው በመሆኑ ²እናንተ ግን² በሚል አባታዊ መመሪያ ተስተካክሎ እናገኘዋለን፡፡ ጾም ፤ጸሎትና ምጽዋት የሸፈተውን የሰውን ልብ ወደ መጸጸትና ንስሐ የሚያመጡ ብርቱ መንፈሳዊ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ጾም ያለ ጸሎትና ምጽዋት የረሃብ አድማ እንደሚመስል ሁሉ ጸሎትም ያለ ጾምና ራስን መግዛት ትርፉ    ውጤት አልባ ጩኸት መሆኑ ውስጣችን የሚቀበለው ሐቅ ነው፡፡

ጾም የሥጋ ፈቃድ የምናደርግበት፤ ሠራተኞቻችንን የምናስጨንቅበት፤የግፍ ጡጫ የማንማታበትና ለጥልና ክርክር የምንቆምበት ሳይሆን የበደል እስራት የምንፈታበት ፤የተገፉትን አርነት የምናወጣበት ፤የጭቆና ቀንበሩን የምንስብርበት ፤እንጀራን ለተራበ ቆርስን የምናበላበትና የተራቆተውን የምናለብስበት መሆን እንዳለበት እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ከነገረን በኋላ አምላካዊ መልሱንም ብርሃንህ እንደንጋት ኮከብ ይበራል፤ ጽድቅህም በፊትህ ይሔዳል በማለት ያስቀምጣል፡፡ (ኢሳ 58÷1-13)

diocese

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 14 የዋና ከፍል ኃላፊዎች ሹመት ሰጠ

የአዲሶቹ የሥራ ኃላፊዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ቀረቧል፡- መጋቤ ጥበባት ሲያምር ተ/ማርያም የአስተዳደር ዋና ክፍል ሓላፊ ሊቀ ኅሩያን ሰርፀ አበበ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ ዋና ክፍል ሓላፊ ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሓላፊ መልአከ ብርሃናት ፍስሀ ጌታነህ የቁጥጥር አገልግሎት ዋና ክፍል ሓላፊ መ/ር ዓይናለም ተጫነ የዕቅድና ልማት ዋና ክፍል ሓላፊ መ/ር ቀፀላ ጥላሁን […]

በጅጅጋ ሰለተፈጠረው ግጭት ከኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በረዥም የታሪክ ጉዞዋ፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ኹሉ በእኩልነት ስታገለግል የኖረች እናት ቤተ ክርስቲያን ናት፤ አሁንም አገልግሎቷን ከመፈጸም የተገታችበት ጊዜ የለም፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሀገር ብትኾንም፣ ሕዝቦቿ፥ በሃይማኖት፣ በጎሣና በቋንቋ ሳይለያዩ፣ ሀገርን የሚወር ነፃነትን የሚገፍ ጠላት ሲነሣ አንድነቱን አጠናክሮ ኹሉም ኢትዮጵያዊ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ የሀገሩን ነፃነት ሲያስከብር ኖሮአል፡፡ በተለይም […]

አራቱ የሃይማኖት ተቋማት የሁለቱን ሲኖዶሶች እርቀ ሰላም አደነቁ

ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ዕርቀ ሰላም መርሐ ግብር ወቅት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ገንቢ የሆነ መልእክት አስተላፈዋል የእስልምናው መሪ መልእክት የተከበረው ቅዱስ ቁርዓናችን የሰው ልጅ ክቡር ነው ይላል፤የሰው ልጅ ምንድን ነው? የሰውል ልጅ ከየት ነው የመጣ? የሰው ልጅ ለምንድን ነው የተፈጠረው? የሰው ልጅ ምን ሊሠራ ነው […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ወደ እናት አገራቸው ተመለሱ

አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትጋር ወደ ኢትዮጵያ በሰላም ገብተዋል ። ሲገቡም ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል፡፡ ከ26 ዓመታት ያላነሰ ዕድሜ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ የጥል ግንብ(ክፍፍል) በእግዚአብሔር ቸርነት፤ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በዶክተር ዐቢይ አህመድ ያላሰለሰ ጥረትና በሁለቱም ሲኖዶሳዊ ቅዱሳንና ብፁዓን አባቶች ቀና በሆነ አመለካከትና የዕርቀ […]

በአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ከሥራ የተፈናቀሉ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በሙሉ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ተወሰነ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ዶ/ር ብፁዕ አቡነ አረጋዊ እና ዋና ሥራ አስኪያጁ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ ከአድባራትና ከገዳማት አስተዳዳሪዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት ጋር በዛሬው ዕለት ከሥራ የተፈናቀሉትን ሠራተኞች አስመልክቶ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡

የውይይቱ አጀንዳ በዋነኝነት በተለያየ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው ተፈናቅለውና ታግደው ያሉትን ሠራተኞች እንዴት አድርገን መፍትሔ እንስጣቸው የሚል ነበር፡፡የሀገረ ስብከቱ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ዶ/ር ብፁዕ አቡነ አረጋዊ በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብዙ ዘመናትን ያሳለፈች፣ ብዙ ተከታይ ያላት፣ የራሷ የሆነ አስተዳደራዊ ሥርዓት የነበራትና ያላት፣ በሰላም አምባሳደርነቷ፣ በይቅርታና በመልካም ሥራዋ የምትታወቅ መሆኗን ገልጸው አሁን ግን በተለያየ ምክንያት በተፈጠረ ችግር ከውስጥ አልፎ አደባባይ ላይ በመውጣቱ ምክንያት መልካም የነበረው ስሟ በደካማ ጎን ተነሥቷል፤ ችግሩ  እንደ ችግር በፈጠርም አሁን ግን የከበረ ዝናዋን ክብሯንና ማልካም ስሟን ማስመለስ ስላለብን ለዚህም ደግሞ እናንተ የረጅም ጊዜ ልምድና ችሎታ ያላችሁ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሊቃነ መናብርት ጋር መወያየቱ እጅግ ጠቃሚ በመሆኑና ለእነዚህ አገልጋዮች መፍትሔ የሚሆን ሓሳብ እንድታግዙን ነው ሲሉ መድረኩን ከፍተዋል፡፡ በመቀጠልም ዋና ሥራ አስኪያጁ  መ/ር ይቅርባይ እንዳለ ከሥራ የተፈናቀሉት ሠራተኞ ጉዳይ አሳዛኝ መሆኑን ገልጸው ለእነዚህ አፋጣኝ ምላሽ እንዴት እንስጥ? ለወደፊት እንዲህ ያለ ችግር እንዳይደገም ምን መፍትሔ እንውሰድ በማለት የረዳት ሊቀ ጳጳሱን ሐሳብ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ በርካታ ባለጉዳዮችን ተቀብለው አስተናገዱ

ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙትን ባለጉዳዮችን በተለይም በቀጠሯቸው መሠረት የተገኙትን ባለጉዳዮች ሲያስተናግዱ ውለዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ወደ ሀገረ ስብከቱ የመጡት ባለጉዳዩች በሁለት መልኩ የሚታዩ ሲሆን በጋራ ሆነው የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ይዘው የመጡና በግል ጉዳይ የመጡ ይገኙበታል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ በመጀመሪያ በጋራ ስለ ቤተክርስቲያን ጉዳይ የመጡትን ባለጉዳዮች በቅድሚያ ያስተናገዱ ሲሆን በመቀጠልም በቀጠሮ በግል ጉዳይ የመጡትን በሚገባ አስተናግደዋል፡፡ ያለ ቀጠሮ የመጡትን ደግሞ ሐሳባውን ከተቀበሉ በኋላ ለሌላ ቀን ቀጠሮ በማስያዝ ሸኝተዋቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ይዘው ወደ ሀገረ ስብከቱ ከመጡት ባለጉዳዮች ከተሰነዘሩት ሐሳቦች መካከል የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ያለመግባባት ችግር፣ ያለመናበብ ጉዳይ ያለጨረታ የሚከራዩ የቤ/ክ ይዞታዎች፣

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ከሀገረ ስብከቱ እና ክ/ከተማ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ

ዛሬ ሐምሌ 09/2010 ዓ.ም በኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ ከብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ የመንበረ ፓትርያርክ የውጭ ጉዳይ የበላይ ሐላፊ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ከሀገረ ስብከቱና ከክፍለ ከተማ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ ካደረጉ በኋላ የሥራ አመራርም ሰጥተዋል፡፡

የዛሬ ዓመት ሐምሌ 09/2009 ዓ.ም በዓለ ሲመታቸው እንደነበረ ያወሱት ሊቀ ጳጳሱ ፣ በዘንድሮ ደግሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሆኜ ለአገልግሎት መሾሜ እግዚአብሔርን አመስግነዋለሁ በማለት በታማኝነት፣ በቅንነትና በመንፈሳዊነት ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሌሎች አሁረ ስብከት ለየት የሚያደርገው የሀገራችን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ ሀ/ስብከት እንደመሆኑ መጠን ብዙ የዲፕሎማትና ሙሁራን የሚገኙበት በመሆኑና ብዙ ውስብስብ የሆኑ አሠራር ያሉበት ሀ/ስብከት ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋገር መግለጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአሜሪካ ለሚደረገው ዕርቀ ሰላም ሶስት ሊቃነ ጳጳሳት እንደምትልክ የቤተክርስቲያኒቷ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ አስታወቁ።

በ1984 ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 4ኛው ፓትርያርክ መንበራቸውን ለቀው ከተወሰኑ አባቶች ጋር ከሃገር በመወጣታቸው በቤተ ክርስቲያኗ ለ26 ዓመታት ምዕመናን እያዘኑ በከፍተኛ የሰላም እጦት ውስጥ ማሳለፏን ቅዱስነታቸው ገልፀዋል።የጠፋውን ሰላም ወደ ነበርበት እንዲመለስ ለማድረግም ቤተ ክርስቲያኗ ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ጥረት ስታደርግ መቆየቷን ነው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የተናገሩት።

በ2010 ዓመተ ምህረት ጥቅምት ወር የቤተ ክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔን ተከትሎ በራሱ ተነሳሽነት ከካህናትና ምእመናን የተወጣጣ የሰላም ኮሚቴ ያቀረበውን የዕርቅ ጥያቄ ተቀብሏል።

በዚህም መሰረት ከሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በአባቶች መካከል የሚካሄደውን የዕርቅ ሰላም ሂደት ፍፃሜ በማግኘት በውጭ የሚገኙ አባቶች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲመለሱ ሶስት ሊቃነ ጳጳሳትን ወደ ስፍራው ያቀናሉ ነው ያሉት።

አሁን በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረውን ዕርቀ ሰላም ያለምንም መሰናከል ለውጤት ይበቃ ዘንድ ዕርቀ ሰላሙን አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶሰ ፈቃድ ከሰጠው አካል በስተቀር መግለጫ መሰጠት ጠቃሚ አለመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን