• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ሐዋርያዊ ጉዞና የሱማሌ ጅግጅጋ አብያተ ክርስቲያናት ፈተናዎች

  የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው በቅዱስ ሲኖዶስ የተሾሙት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ህዳር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ከጅግጅጋ ከተማ 170 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው በደጋ ሀቡር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ብፁዕነታቸው የእሳት ቃጠሎ የደረሰበትን የደጋ ሀቡር ቅዱስ ጊዮርጊስን ፅላት በተዘጋጀው መቃረቢያ ባርከው ያስገቡ ስለሆነ በማግሥቱ ህዳር 8 ቀን 2011 ዓ.ም የቅዳሴ ቤቱ በዓል በላቀ ድምቀት ተከብሯል፡፡
በዚሁ ደብር የቅዱስ ሚካኤል ፅላት በተደራቢነት ገብቶ ህዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም በዓሉ ተከብሯል፡፡
በጅግጅጋ መልእልተ አድባራት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ በርካታ ምዕማንንና ካህናት በተገኙበት ለብፁዕነታቸው እጅግ የደመቀ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
በማግሥቱ ሰኞ ህዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም ከጅግጅጋ ከተማ በ70 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የውጫሌ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ጎብኝተዋል፡፡
ማክሰኞ ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም በጅግጅጋ ከተማ ዙሪያ የሚገኙትንና በፀረ ሰላም ኃይሎች የእሳት ቃጠሎ የደረሰባቸውን የአቡነ ተክለሃይማኖትን፣ የቅድስት አርሴማን፣ የቅዱስ ጊዮርጊስንና የቅድስት ኪዳነ ምሕረትን አብያተ ክርስቲያናት ብፁዕነታቸው እየተዘዋወሩ …

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ ሰባቱ ክፍለ ከተሞች ሪፖርት አቀረቡ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ፤ ምክትል ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወ/ሐና እና የሀገረ ስብከቱ ዋና ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት በክፍለ ከተማ ሠራተኞች በአዲስ ቅጥር፣ ሽግሽግ፣ ዙሪያ የተደረገው ጥናት ሪፖርት ቀርቧል፡፡ የ7ቱ ክፍለ ከተማ ሠራተኞች በእነርሱ ሥር ያሉትን ገዳማትና አድባራት ላይ ባደረጉት ፍተሻ የተወሰኑት አዲስ ቅጥርን ፣ ሽግሽግን እንደፈፀሙ ገልፀዋል፡፡ እነዚህም አብዛኛው በኢ-ሕጋዊ መልክ እንደተፈፀመ ነው የተረጋገጠው፡፡ በተለይ ደግሞ በአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት በሚደረግ ቅጥር በጣም ውስብስብና ሥርዓት አልባ እየሆነ የሚሄደበት ሂደት ስላለ በደንብ ታይቶ  ጠንከር ያለ አሠራር እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል፡፡ በአንዳንድ አብያተ  ክርስቲያናት ያሉት ሠራተኞች ብንናገራቸውም የሚሰጡን መልስ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በአንዳንድ አጥቢያ ላይ በተመሣሣይ ሥራ ላይ ሁለትና ከሁለት በላ የሆኑ ሰዎች መቀመጣቸው ሌላ ችግር መሆኑም…

የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ስብከተ ወንጌልን እንቅስቃሴን አስመልክቶ ውይይት አደረገ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ በቀን 29/02/2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡

በውይይቱ ላይ የሀገረ ስብከቱና፣ የክፍለ ከተማው ሠራተኞች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ የውይይቱ አጀንዳዎች ሁለት ሲሆኑ የመጀመሪያው ጥናታዊ ጽሑፍ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስብከተ ወንጌልን በመተለከተ ነው፡፡ በመጀመሪያው ክፍል በክፍለ ከተማው አዘጋጅነት መጋቤ ሐዲስ ሮዳስን በመጋበዝ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን የብራና መጻሕፍት ይዞታቸውና ያካተታቸው ምሥጢራትና በባሕር ማዶ ስለሚገኙት መጻሕፍት በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ ጥናታዊው ጽሑፉ በውስጡ ብዙ ነገሮችን ያካተተ…

መ/ር ይቅርባይ እንዳለ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስከያጅ በ37ኛው አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ላይ ያቀረቡት ዓመታዊ የሥራ ሪፖርት

ሙሉ ቪዲዮውን ከስር ይመልከቱ

ቅዱስ ሲኖዶስ በዴርሱልጣን ገዳም በተፈፀመው ሕገ-ወጥ ድርጊት መግለጫ ሰጠ

በስመአብወወልድወመንፈስቅዱስአሐዱአምላክአሜን! የኢትዮጵያውያን ይዞታ በሆነው በዴርሱልጣን ገዳም የቅዱስ ሚካኤል ቤተመቅደስ እድሳት ላይ የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባላት ያሳዩትን ሕገወጥ ተቃውሞ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፤ ሁላችሁም እንደምታውቁት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኢየሩሳሌም ካሏት ጥንታውያንና ታሪካውያን ቅዱሳት መካናት ውስጥ አንዱና ዋናው በዴርሱልጣን የሚገኘው የመድኀኔዓለም፣ የአርባዕቱ እንስሳ እና የቅዱስ ሚካኤል ገዳማት ናቸው፡፡ ከታሪክ እንደምንረዳው […]

የጥቅምት 2011 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የመክፈቻው ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የተለመደውን […]

የጥቅምት 2011 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጀመረ

 ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ባለችው ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን፣ ሃይማኖታዊ አገልግሎታችንን እየባረከ ዘወትር የማይለይ እግዚአብሔር አምላካችን፣ አሁንም ለበለጠ ሐዋርያዊ ሥራ እንድንመካከር በስሙ ስለ ሰበሰበን ስሙ የተመሰገነ ይኹን፡፡

በቤተ ክርስቲያናችንም ኾነ በዓለም አቀፍ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ እንደሚታወቀው፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ መሠረቱ ክርስቶሳዊ አስተምህሮ፣ ሐዋርያዊ ትውፊትና ቀኖና ቅዱሳን አበው ነው፡፡

ክርስቶስ መድኃኒታችን፣ “በስሜ በምትሰበሰቡበት እኔ በመካከላችሁ እኖራለሁ፤” ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶአል፤ ይህን ተከትሎም የመጀመሪያው ሲኖዶሳዊ ጉባኤ፣ በቅዱሳን ሐዋርያትና በቀሲሳን ኅብረት በቅድስት ሀገር በኢየሩሳሌም ማእከላዊነት፣ በቅዱስ ያዕቆብ እኁሁ ለእግዚእነ ርእሰ መንበርነት፣ በዘመነ ሐዋርያት እንደተካሔደ፣ “ወአንገለጉ ሐዋርያት ወቀሲሳን ከመ ይርአዩ ዘይገብሩ በእንተዝ ነገር፤ ሐዋርያትና ቀሳውስትም ስለዚህ ነገር ለመመካከር ተሰባሰቡ” ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ ተመዝግቦአል፡፡ የተወሰነው ውሳኔም፣ መንፈስ ቅዱስ ያለበት መኾኑን ለማመልከት፣ “እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናል” ተብሎ ተገልጾአል፡፡ (የሐዋ ሥራ 15፥6-29)ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን ያጋጠሙ ፈተናዎችን ለማየት፣ ላለፈው እርማትና ማስተካከያ ለመስጠት፣ ለሚቀጥለው የሥራ አቅጣጫን ለማስቀመጥ፣ ተላውያነ ሐዋርያት በየጊዜው ሲኖዶሳዊ ጉባኤ ያካሒዱ እንደነበር ኹላችንም የምናውቀው ነው፤ በተለይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓለ ቅዱስ መስቀል በተከበረ በኻያ አምስተኛ ቀን ጥቅምት ዐሥራ ኹለት እና የትንሣኤ በዓል በዋለ በኻያ አምስተኛው ቀን በርክበ ካህናት፣ በድምሩ በዓመት ኹለት ጊዜ እንዲካሔድ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መደንገጉ በፍትሕ መንፈሳዊ ተጽፎ…

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 37ኛው የሰበካ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ተጀመረ

ጥቅምት 5 ቀን 2011 ዓ.ም ጉባኤው የተጀመረ ሲሆን ስብሰባው በጸሎት ወንጌል ተከፍቷል፡፡
“ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ እግዚአብሔር፣ምክር ሰናይት ለኲሉ ዘይገብራ ውስብሓትሁኒ ይነብር ለዓለም” የሚለው የዳዊት መዝሙር ልብሰ ተከክህኖ በለበሱ ዲያቆናት በዜማ ቀርቧል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ቀዳማዊ ፣ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በጉባኤው ላይ የተገኙ ሲሆን በመርሐ ግብሩ መሠረት
በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 18 ቁጥር 18 ላይ የተፃፈው “በስሜ አንድም ሁለት ሆናችሁ ብትሰበሰቡ እኔ በመካከላችሁ እገኛለሁ” የሚለው ቃል በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በንባብ ተነቧል፡፡
በመቀጠልም ሰላም ለክሙ ኦ ማኅበራኒሁ ለክርስቶስ እለተገባዕክሙ ውስተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት፣ ቀሳውስት ወዲያቆናት ወማኅበረ ምዕመናን የሚል ያሬዲዊ ወረብ በማህደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ተዘምሯል፡፡
ከዚህ በኋላ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የጠቅላይ ቤተክህነተ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ በክልል ትግራይ የደቡባዊ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጠቅላላ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ብፁዕነታቸው በታላቁ ጉባኤ ባቀረቡት ሪፖርት “ዮም በዛቲ ዕለት አስተጋብአነ በመንፈስ ቅዱስ ከመንንግር ሠናይቶ ወከመንዘከር አበዊነ እንዘ ናረትዕ አእጋሪነ ውስተ ፍኖተ ሰላም” በሚል የመጽሐፍ ቃል ንግግራቸውን በመጀመር ባቀረቡት ሰፊ እና ጥልቅ ሪፖርት በዘንድሮው 37ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ልዩ የሚያደርገው ከሃያ ሰባት ዓመታት በኋላ በውጭ ሀገር የነበሩ ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደሀገራቸው ተመልሰው የቅድስት ቤተክርስቲያን አንድነትና የቅዱስ ሲኖዶስ ውሕደት በተፈጸመበት ማግስት የሚካሄድ …

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሰባክያን ጋር ውይይት አደረገ

የሀገረ ስብከቱ የሥራ መሪዎች ከገዳማትና አድባራት አስተዳዳረዎችና ሰባክያነ ወንጌል ጋር “የስብከተ ወንጌልና የሚድያ አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን ያለው ሚና” በሚል ርእስ መስከረም 14 ቀን 2011 ዓ/ም በሀገረ ስብከቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለግማሽ ቀን የቆየ የምክክርና የውይይት መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡ በመርሐ ግብሩ ሂደት ላይ ሰፋ ያለ ትምህርታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልእክት ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የውጭ ግንኙነት የበላይ ሓላፊና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ጳጳስ ስለስብከተ ወንጌል ምንነት ሲገልጹ የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ የሕይወታችን አካል ፣ያገልግሎታችን መሠረት ነው፡፡ ለሁለት ሺህ ዓመታት ወንጌል የተዘራባት ፣በተዘራው መልኩ ውጤቱን በፍሬው መገምገም የቻልንበት ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡

ስብከተ ወንጌል በቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ማንነት ትልቅ ሚና አለው፡፡ስብከተ ወንጌል ለቤተ ክርስቲያን ዕድገትና ጥንካሬ ፣ለምዕመናን ሕይወት መሠረት መሆኑን ፣ስብከተ ወንጌል ትእዛዘ እግዚአብሔር መሆኑን ፣ይህም በመሆኑ ለስብከተ ወንጌል ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ፣የእግዚአብሔር ቃል ያልገራውና ያልተቆጣጠረው ህሊና ለእግዚአብሔርም ለሰውም የማይመች መሆኑን በመግለጽ ብፁዕነታቸው ጥናታዊ በሆነ አቀራረብ ሰፋ የለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ይቅር ባይ እንዳለ አክለው እንደገለጹት የስብከተ ወንጌል ጉዳይ ከቀን ወደቀን አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ፣ቢፅ ሓሳውያን አስተሳሰብን የሚያራምዱ ኃይሎች በቤተ ክረርስቲያን መሰግሰጋቸውን ፣የቅዱሳኑን ስም የመጥራት ፍላጎት የማያሳዩ መሆናቸውን፣…

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ2011 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወአሐዱ ዓመተ ምሕረት በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን