• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

38ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሣዊ ጉባኤ ውሳኔ ሐሳብና የአቋም መግለጫ

ታሪክ እንደሚመሰክረው ዘመናዊ ት/ት ባልተስፋፋበት ዘመን እንደ ት/ት ሚኒስቴር ሆና ወጣቱን በጥበብ ሥጋዊና በጥበብ መንፈሳዊ ኮትኩታ በማሳደግ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን መሪነት ያበቃች፣ ሀገርን የሚወር፣ ሃይማኖትን የሚያጠፋ ወራሪ ኃይል በመጣ ጊዜም ታቦትን ይዛ በመዝመት ሕዝቡን በማበረታታት ዳር ድንበርን ያስከበረች፣ የሰላም ምንስቴር ባልተዋቀረቡት ዘመን እንደ ሰላም ምንስቴር ሆና የሀገርን ሰላም ያስጠበቀች የሀገር ባለውለታ የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ […]

አንጋፋው የአዲስ አበባ ሀ/ ስብከት ጽ/ቤት ዓመታዊ የሥራ ሪፖርቱን አቀረበ

በ38ኛው መደበኛ ሰባካ መንፈሳዊ ጉባኤ የ3ኛው ቀን የስብሰባ ውሎ ላይ በርካታ አህጉረ ስብከት ዓመታዊ የሥራ ሪፖረትና ዕቅዳቸውን ካቀረቡ በኃላ ተጠሪነቱ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሆነውና በረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የሚመራው አንጋፋው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትም ዓመታዊ የሥራ ሪፖርቱንና ዕቅዱን በጉባኤው ፊት አቅርቧል፡፡ ሀገረ ስብከቱ በተሰማራባቸው የተለያዩ የሥራና የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ባደረገው እንቅስቃሴ […]

‹‹የመስቀሉ ነገር ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው›› /1ኛቆሮ. 1÷18/

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ታላላቅ ብሔራውያን በዓላት መካከል አንዱ የመስቀል በዓል ነው፡፡ በተለይ ይህ በዓል በዩኒስኮ መመዝገቡ የቤተ ክርስቲያናችንን ታላቅነትና ጥንታዊነት ከመግለጹ ባሻገር በሀገር የልማት ዕድገት ላይ የሚያበረክተው ጥቅም ዘርፈ ብዙ መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ መስቀል ስንል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሲል የተቀበለውን ጸዋትወ መከራ እናስታውሳለን፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ […]

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ስለ ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ የጋራ ውይይት ተደረገ

የጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በጋራ ባዘጋጁት የምክክርና የውይይት መድረክ በሁለት ብፁዓን አባቶች የሚመራና የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች፤ የክፍላተ ከተሞች ሃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳደሪዎችና ሰባክያነ ወንጌል በተገኙበት በቀረቡ ሁለት ዳሰሳዊ ፅሁፎች መነሻነት የጋራ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን […]

ርዕሰ ዓውደ ዓመት የአዲስ ዘመን መጀመሪያ

በኢትዮጵያ ያለፈው ዓመት አልቆ የሚተካው የሚጀመርበት መስከረም አንድ ቀን ስለሆነ በቤተክርስቲያናችን ሥርዐት መሠረት ርዕሰ ዓውደ ዓመት ይባላል፡፡ ዘመን ሲያልፍ ዘመን ይተካል፡፡ ትውልድም ሲያልፍ ትውልድ ይተካል፡፡ ለኅልፈትና ለውላጤ የተፈጠረ ፍጡር ሁሉ ወቅትና ጊዜ አለው፡፡ በዚያው በተሰጠው ዘመን ሁሉም ሥራውን ያከናውናል አከናውኖም ያልፋል ያለሥራ የተፈጠረ ፍጡር የለምና፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረታትን ፈጥሮ ሲፈጽም “ወርእየ እግዚአብሔር ኵሎ ዘገብረ ከመ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳዲስ የመተግበርያ ሲስተም ሶፍት ዌሮች ሥራ ላይ ሊያውል ነው

 ይህ የቴክኖሎጂ ትግበራ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እና የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መ/ር አባ  ሞገስ ኃይለማርያም(ቆሞስ)፣ የሀገረ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሚያስተላልፋቸው መመሪያዎችና አፈጻጸማቸው ዙሪያ ውይይት አደረገ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ያሉበትን የሥራ ጫናዎች ለማቃለልና የባለጉዳዮችን እንግልት ለመቀነስ እንዲሁም ደግሞ የዕዝ ሰንሰለቱን ጠብቆ ሥራዎችን ለመከወን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መሠረት አድረጎ የተሻለውን መንገድ ሁሉ በመከተል ላይ ይገኛል፡፡ ጽ/ቤቱ ከወሰዳቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች መካከል አንዱ በሥሩ ካሉት አድባራትና ገዳማት የሚመጡ ልዩ ልዩ ባለጉዳዮችን የሚያስተናግድበት መንገድ ነው፡፡  ይህ የአሠራር መንገድ ባለጉዳዮች ከታች ጀምሮ ያሉትን የጽሕፈት […]

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ኮልፌ ክፍለ ከተማ የሚገኘውና ከሦስቱ መንፈሳዊ ኮሌጆች መካከል አንዱ የሆነው እንዲሁም በርካታ የቤተ-ክርስቲያንን ምሁራንን ያፈራውና በማፍራት ላይ የሚገኘው ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ  በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ላይ ለሦስትና ለአምስት ዓመታት አስተምሮና አሰልጥኖ ያበቃቸውን  ማለትም በሐዲሳት ትርጓሜ መጻሕፍት ትምህርት 12 ደቀመዛሙርት፤በመደበኛው ሴሚናሪ ትምህርት 31 ደቀ መዛሙርትና በማታው መርሐ ግብር ሴሚናሪ ደግሞ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በዘመናዊ የሒሳብ አያያዝ ያሰለጠናቸውን 36 ሒሳብ ሹሞችን አስመረቀ

የምርቃቱ ሥነ ሥርዓት ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እና የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፤ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መ/ር አባ  ሞገስ ኃይለማርያም(ቆሞስ)፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ሊቃነ መናብርት፣ዋና ጸሐፊዎች በተገኙበት በ14/2011ዓ.ም በደማቅ […]

በዓለ ጰራቅሊጦስ

“ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም” /ዮሐ.14÷18/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኙ ዐበይት (ታላላቅ) በዓላት መካከል አንዱ የጰራቅሊጦስ በዓል ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ ግሪክ ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት መጽንዒ በእምነት የሚያጸና፣ መንጽሒ ከኃጢአት የሚያነጻ፣ ናዛዚ ያዘኑትን የሚያረጋጋ፣ መስተፍሥሒ፣ ያዘኑትን የሚያስደስት፣ ከሣቲ ምስጢርን የሚገልጽ ማለት ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ፡- መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ የጰራቅሊጦስ በዓል ታሪክ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን