• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

006

“ሕያዉን ከሙታን ጋር ለምን ትፈልጉታላችሁ? በዚህ የለም ተነሥቷል” /ሉቃ. ፳፬፡፭/

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን እንደሚነሣ ቅዱሳን ነቢያት አስቀድመው ትንቢት ተናግረዋል፡፡ ከትንቢቶቹም አንዱ “ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፡፡ ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፡፡ ወቀተለ ጸሮ በድኅሬሁ” /የተኛ ሰው ከእንቅልፍ እንደሚነቃ እግዚአብሔር ከሙታን ተነሣ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ በኋላው በተተከለ መስቀል ጠላቱን ድል አደረገ/ /መዝ. 77፡65/       ስለ ጌታችን ትንሣኤ አራቱም ወንጌላውያን ጽፈዋል፡፡ ይህም /ማቴ. […]

002

በዓለ ሆሣዕና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆሣዕና በዓል ነው፡፡ ስለዚህ በዓል አስቀድሞ ትንቢት ተነግሯል፤ ከትንቢቶቹም አንዱ እንደሚከተለው ተጠቅሷል፡፡ “አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ በአህያና በአህያይቱ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል” /ትን. ዘካ. 9፡9/ ከዚህም ጋር ስለበዓለ ሆሣዕና አራቱም […]

‹‹ጥንተ ስቅለት››

የዓለም መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በቀራንዮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሕይወቱን ለዓለም ቤዛ፣ አድርጎ የሰጠው መጋቢት ፳፯ ቀን ፴፫ ዓ.ም እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ቀን ስለክርስቶስ ሕማም፣ ስለመከራ መስቀሉና ስለሞቱ የተነገሩት ትንቢቶችና ምሳሌዎች ሁሉ የተፈጸሙበት፤ ሰማያዊ አምላክ ስለሰው ልጆች ፍቅር ሲል ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ሞትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ […]

መልካም ባልንጀራ

ምስጢር የሚያወያዩትን አብሮ የሚሠሩትንና ጧት ማታ የሚገናኙትን እንዲሁም አብሮ አደግየሆነውን ሰው ባልንጀራዬ ነው ብሎ መናገር የተለመደ ነው፡፡ ዛሬ ለኔ ነገ ላንተ እየተባባሉ አብረው ከሚውሉት፣ ከሚያመሹት ጓደኞቻቸው ሌላ ባልንጀራ ያለ የማይመስላቸውም ብዙዎች ናቸው፡፡ በመሠረቱ አብሮ መብላትና መጠጣት ወይም በአንድ ላይ ተምሮ ማደግና አብሮ መኖር ይልቁንም ትንሽ ትልቁን ክፉና ደጉን ምስጢር መካፈል ባልንጀራ ሊያሰኝ ቢችልም ይህ ብቻ […]

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ፮ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፬ኛ ፓትርያርክ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ ከ34 በላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የእስልምና ዋና ሐላፊ ሸክ አህመድ፣ የቤተክህነት ሠራቶኞች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በርከት ያሉ ምእመናንና እንግዶች በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ […]

ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የዓብይ ጾም መግባትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

በቤተክርስቲያንችን ቀኖናዊ ሥርዓተ እምነት መሠረት በጾምና በጸሎት ከምንዘክራቸውና ፈቃደ ሥጋችንን ለፈቃደ ነፍሳችን ከምናስገዛበቸው አጽዋማት መካከል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾሞ በአርዓያነት ያሳየን ጾመ ኢየሱስ ወይም ዓብይ ጾም አንዱ ነው፡፡ በዚሁ የገዳመ ቆሮንቶስ ጾም ወቅት የሰውን ልብ በእጅጉ የሚገዳደሩና ለውድቀትም የሚዳርጉ የኃጢአትና የበደል ምክንያቶች ሁሉ በክርስቶስ ባሕሪያዊ ገንዘብ በሆነው በኃይሉ ችሎት ከመንገዳቸው ወጥተዋል የሰይጣንም ሽንፈት ተረጋግጧል፡፡ […]

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የክፍል ኃላፊዎች የስድስት ወር ሪፖርት አዳመጠ

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራአስኪያጅ ቆሞስ አባ ሞገስ ኃ/ማርያም ፣ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወ/ሐና፣ የየክፍሉ ኃላፊዎች፣ የሀ/ስብከቱና የሰባቱ ክፍለ ከተሞች ሠራተኞች በተገኙበት በሀ/ስብከቱ የስብሰባ አዳራሽ የሁሉም ክፍል ኃላፊዎች የስድስት ወር ሪፖርት ቀርቧል። በሪፖርቱ ብዙ አመርቂ የሚባሉ ሥራዎች እንዳሉ ሆነው በአንጻሩ ደግሞ ብዙ ሊሠሩ የሚገባቸው ሳይሠሩ እንደቀሩና ለወደፊቱ ትኩረት ተሰጥቶባቸው በአግባቡና በጊዜው […]

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ስብከተ ወንጌልን አስመልክቶ በሥሩ ከሚገኙት ከገዳማትና አድባራት ስብከተ ወንጌል ሐላፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት አደረገ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስብከተ ወንጌልን አስመልክቶ  በስሩ ከሚገኙት የገዳማትና አድባራት የስብከተ ወንጌል ሐላፊዎች ጋር ሰፊ የሆነ ውይይት ያደረገ ሲሆን በስብሰባው ላይ የአንድነት ጉባኤ፣ የስብከተወንጌል ኮሚቴ  የሚጠበቅበትን ሥራ ለምን አልሠራም፣ ሥልጠናን እንዴት እንስጥ የሚሉት ታላላቅና ወቅታዊ የሆኑ አጀንዳዎች ተነስተዋል፡፡ አጀንዳዎቹ ለታዳሚዎቹ በክፍለ ከተማው የስብከተ ወንጌል ሐላፊ በመጋቤ ሐዲስ ዘለዓለም […]

አዲሶቹ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የሥራ ሐላፊዎች ከገዳማቱና አድባራቱ ሐላፊዎች ጋር ትውውቅ አደረጉ

በአዲስ መልኩ የተመደቡት የጽሕፈት ቤቱ የሥራ ሐላፊዎች ከአንድ ሳምንት በፊት በሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ሐላፊዎችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም በክፍላተ ከተሞች ሠራተኞች አቀባበል የተደረገላቸው ቢሆንም በቀን 11/2011 ዓ/ም ደግሞ ቅዱስ ፓትርያሪኩና ሌሎችም በርካታ ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ከአድባራቱና ገዳማቱ አስተዳደሪዎችና ጸሐፊዎች ጋር በሀገረ ስብከቱ የስብሰባ አዳራሽ የትውውቅ መርሐ ግብር ተደርጓል፡፡ በዚሁ የትውውቅ መርሐ ግብር ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት […]

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተመደቡት ብጹእ አቡነ መልከጼዴቅ እና በዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመደቡት መ/ር አባ ሞገስ ኃይለ ማርያም በሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ሐላፊዎችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም የክፍላተ ከተሞች ሥራ አስኪያጆችና ሠራተኞች በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ የስብሰባ አዳራሽ ዛሬ የካቲት 2011ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ በሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን