• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የአ/አ/ሀ/ስ/ዋና ስራ አስኪያጅ መልአክ ሕይወት አባ ኃይል ገብርኤል ነጋሽ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተገዢ ልንሆን ይገባል አሉ

በሀገራችን ኢትዮጵያ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ በሕዝባችን ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ከወዲሁ ካህናትና ምዕመናን በጸሎት እንዲተጉ፣ ከመንግሥት እና ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ትምህርት በተግባር ላይ እንድናውል ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መወሰኑ ይታወቃል። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መልአክ ሕይወት አባ ኃይል ገብርኤል ነጋሽ መጋቢት 22/2012 ዓ.ም ከቅዳሴ መልስ በኋላ በደብረ ፅጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ […]

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ የመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤትና የአ/አ/ሀ/ስ/ ጽ/ቤት ኮሚቴዎች ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ውይይት አደረጉ

መጋቢት 21/2012 ዓ.ም የፌደራል ፖሊስ ዋና ጀነራል እንደሻው ጣሰው እና ምክትል ጀነራል መላኩ ፈንታ በመንበረ ፓትርያርክ ቅጥር በመገኘት ስለ ወረርሽኙ ሰፊ ግንዛቤ ሰጥተዋል። በውይይቱ ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ ቤተ ክርስቲያን የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት አስፈላጊውን ውሳኔ ወስናለች የሚቀረን ነገር የተወሰነውን ወሳኔ ተግባራዊ ማድረግ ነው ብለዋል። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ […]

የኮሮና በሽታ መከላከልን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

በዓለም ላይ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የሚገኘው ተላላፊ በሽታ ለአገራችን ኢትዮጵያም ከፍተኛ ስጋት መሆኑን በመጠቆም ወረርሽኙን ለመቋቋም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ያሬድ እንዳሉት፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ባሉባት ሕዝባዊ ኃላፊነት […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምሥጋናና መልእክት

በዛሬው የነግህ የጸሎተ-ዕጣንና የማዕጠንት አገልግሎት ለተሳተፋችሁ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ካህናት በሀገረ ስብከታችን ጽ/ቤት ስም ምሥጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የአቀረብነውን የዕጣን መሥዋዕት እንዲሰምርልንና ይህንን በሽታ ከሀገራችንና ከመላው ዓለም እንዲያስወግድልን ኦርቶዶክሳውያን ሁላችን ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጀውን የጸሎትና የምህላ ጥሪ በመቀበል በየአጥቢያችን ተሳትፎ እንድናደርግ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች የሚነግሩንን ሙያዊ ምክሮች የመተግበር ግዴታ እንዳለብን መዘንጋት የለብንም፡፡ እግዚአብሔር አገራችንና መላውን ዓለም […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት መግለጫ አወጣ

መነሻውን ከሀገረ ቻይና ያደረገውና መላው ዓለምንና ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከማስጨነቁና የብዙ ወገኖቻችንን ሕይወት ከመቅጠፉም ባሻገር ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ ምክንያት እየሆነ የሚገኘውን የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ አስመልክቶ የሀገረ ስብከታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ የሚዲያ አካላት በተገኙበት ወቅታዊ መግለጫ በጽ/ቤታቸው ሰጡ፡፡ በመግለጫውም ላይ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስም ሆነ ራሳችንን ከጥቃቱ ለመከላከል በዓለም ጤና ድርጅት […]

ዓለምን ባስጨነቀው ወቅታዊ ወረርሽኝ ዙሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ አወጣ

መነሻውን ከሀገረ ቻይና ውሃን ግዛት በማድረግ በመላው ዓለም የተዛመተውና ለበርካታ ወገኖቻችን ሕልፈተ ሕይወት፤ ለብዙዎችም ያልተረጋጋ ኑሮን መግፋትና ሰላምን ማጣት እንዲሁም ደግሞ በምድራችን ላይ እየተከሰተ ላለው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ ትልቁ ምክንያት የኮረና ቫይረስ ወረሽኝ መሆኑ በሁላችን ዘንድ የታወቀ የዕለት ከዕለት ዜና ነው፡፡ ይህ በምድራችን የተከሰተው ወቅታዊ ወረርሽኝ ጾታና፤የቆዳ ቀለም፤እንዲሁም የትምህርት ደረጃና የአኗኗር ዘይቤን መሠረት አድርጎ የሚያጠቃ […]

የቦሌ ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተቀመጠ

በዕለቱ የመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች፤የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የሀገረ ስብከቱ የየዋና ክፍል ኃላፊዎች እና የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ንቡረ ዕድ አባ ዮሐንስ እንዲሁም የክፍለ ከተማው የስራ ኃላፊዎች የመንግሥት ተወካዮች ከአራቱም አቅጣጫ […]

ሰበር ዜና በ22 አካባቢ ለ2 ወጣቶች ሞት ምክንያት የሆነው ቦታ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተሰጠ

በአዲስ አበባ 22 አካባቢ በመንግሥት ታጣቂዎች ምእመናን በግፍ የተገደሉበትና በፈረሰው ቤተ ክርስቲያን ላይ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቤተ ክርስቲያን እንዲሰራበት ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ተሰጥቷል ። ይህን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ በክቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የተመራ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ በቦታው […]

አዲሱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከሀገረ ስብከቱና ከክፍላተ ከተማ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ

በትውውቅ መርሃ ግብሩ ላይ የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የክፍላተ ከተሞች ሥራ አስኪያጆችና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡ “የእንኳን ደህና መጡ መልእክትም” ለክቡር ሥራ አስኪያጁ አስተላልፈዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በተደረገው ውይይት ሀገረ ስብከቱ ያሉበትን ዘርፈ ብዙና ውስብስበ ችግሮች፣ እንዲሁም ብለሹ አሠራሮችና የወደፊት የመፍትሔ አቅጣጫዎች ይሆናሉ ተብለው የታሰቡት ለክቡር ሥራ አሥኪያጁ ተጠቁመዋል፡፡በየጊዜው ሥራ አስኪያጆችን እየተቀበለ መሸኘትን ልማዱ ያደረገው […]

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፯ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ዛሬ የካቲት 24 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች፣ የየድርጅቱ ኃላፊዎች፣ የመንፈሳዊ ኮሌጆች ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የየክፍሉ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃነ መናብርት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና  ምእመናን በተገኙበት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን