• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ችግሮች ለመፍታትና ሁለንተናዊ ዕድገቱን ለማፋጠን ያለመደነቃቀፍ መስመራችንን ጠብቀን በጋራ እንሮጣለን………ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ/ም የጉራጌ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ: የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎች እና ሠራተኞች:የሰባቱም ክፍላተ ከተሞች ሥራ አስኪያጆችና የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ የስብሰባ አዳራሽ በስብከተ ወንጌል በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የሥራ መመሪያ ተሰጠ፣ አጭር ውይይትም ተካሄደ ። የሥራ መመሪያውንና የውይይት መርሐ ግብሩን […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስከያጅ መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ ከሥራ ኃላፊት ታገዱ!!!

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዉሳኔ ውጭ በግል ማገድ እንደማይቻል ገልጸው ቀደም ሲል ከልዩ ጽ/ቤት ለተጻፈው ደብዳቤ መልስ ሰጡ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ለተመደቡት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ጥቅምት 2013 ዓ/ም ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ ሊቀ ጳጳስ አድርጎ በመደበው መሠረት ጥቅምት 21/2013 ዓ/ም የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እና በርካታ ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገረ ስብከቱ […]

ቅዱስ ሲኖዶስ ታላቁን የሕዳሴ ግድብ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

ቅዱስ ሲኖዶስ ጥቅምት16 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በነበረው ጉባኤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በታላቁ የሓዳሴው ግድብ ዙሪያ በሰጡት ግጭት ቀስቃሽ ንግግር ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡ መግለጫው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የቀረበ ሲሆን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሥራው ተጀምሮ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ደረጃ ላይ […]

የቤተ-ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን ስብከተ ወንጌልን ማጠናከር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ተገለጸ

ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ክቡር አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ፣ የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ ዋና ክፍል ኃላፊው መ/ር ባህሩ ተፈራ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰባቱም ክፍላተ ከተሞች የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎችና የአድባራትና ገዳማቱ የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ የስብሰባ አዳራሽ በስብከተ ወንጌል ዙሪያ ውይይት […]

የጥቅምቱ የ2013 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ምልአተ ጉባኤ የመክፈቻው ስነ ሥርዓት በጸሎት ተከፈተ

የ2013 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ምልዓተ ጉባኤ ጥቅምት 11 ከቀኑ 10:00 ሰዓት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ክቡር ቆሞስ አባ ኃይለገብርኤል ነጋሽ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የጠቅላይ […]

39ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ

ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው አጠቃላይ መንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ በዛሬው እለት ጥቅምት 05/2013 ዓ.ም ተጠናቋል ፡፡ ከሰዓት በኋላ በነበረው መርሃግብር የአውስትራሊያ፣የጣሊያንና አከባቢዋ፣ የሊባኖስና የተባባሩት ኢምሬቶች አህጉረ ስብከቶች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከሪፖርታቸውም እንደተደመጠው የኮሮና ቫይረስ ለመንፈሳዊ አገልግሎታቸው ከባድ እንቅፋት መሆኑን ገልጸው ነገር ግን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም ስብከተ ወንጌልን እንዳስፋፉ፣በብሔርና በሃይማኖት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ምእመናን የተለያዩ እርዳታዎችን […]

አንጋፋው የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ጽ/ቤት በ39ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ሰበካ መደበኛ ጉባኤ ላይ ሪፖርቱንና እቅዱን አቀረበ

ተጠሪነቱ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሆነው ታላቁና አንጋፋው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በዛሬው እለት በቀን 05/2013ዓ.ም ሪፖርቱንና እቅዱን አቅርቧል፡፡ሪፖርቱን ያቀረቡት ክቡር ዋና ሥራ አስኪያጁ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ ሲሆኑ ንግግራቸውንም “አቤቱ አንድነታችንን በሰላም ባርክ ጠብቅ፣ከዓለም ይልቅ የወደዱህን ቅዱሳን ካህናትህን፣ምዕመናንንህን […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በመንፈሳዊ ፣ ማኅበራዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች እጅግ የተሳካ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለጸ !!!

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ድንጋጌ መሠረት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በ2012 ዓመተ ምህረት በመንፈሳዊ ፣ ማኅበራዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች ላይ እጅግ የተሳካ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ። የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ህይወት አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ በ39ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ አለምአቀፍ ጉባኤ የሀገረ ስብከቱን የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን