• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አሸባሪው ህወሓት በወልዲያ በርካታ ንፁሐንን በመግደልና ንብረት በመዝረፍ ከፍተኛ በደል መፈፀሙን አስታወቁ !!!

የሰሜንና የደቡብ ወሎ እንዲሁም የከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አሸባሪው ህወሓት በወልዲያ በርካታ ንፁሐንን መግደሉንና በንብረት ላይ ዘረፋ እና ውድመት መፈፀሙን አስታወቁ። ብፁዕነታቸው አሸባሪው ቡድን በወልዲያ ከተማ በቆየባቸው ጊዜያት የከተማው ነዋሪ እህል ፣ መድኃኒት እና አስፈላጊ ነገሮችን ሳያገኝ መቆየቱን ገልፀዋል። በተጨማሪም ከግለሰብ ኪስ ጀምሮ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን መዝረፋቸውን እና ማውደማቸውን  […]

የሰሜን አሜሪካ ማኀበረ ካህናት ለቤተክርስቲያንና ለሀገር ዘረፈ ብዙ አገልግሎት እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ!!!

በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት የሚያገለግሉ ካህናት “የሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት ” በሚል ኅብረት መሥርተው ሀገራቸውና ቤተክርስቲያናቸውን በሁለንተናዊ መልኩ እያገለገሉ ይገኛሉ። ማኅበሩ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ለተጎዱ ካህናትን ምዕመናን ዕርዳታ ለማድረግ ያሰባሰበውን ገንዘብ በአግባቡ ለተጎጂዎች በማሰራጨት የፕሮጀክቱን መዝጊያ ሥነ ሥርዓት እንዲሁም ወቅታዊው የሀገራችንንና የቤተ ክርስቲያንን ሁኔታ አስመልክቶ የተዘጋጀውን መርሐ ግብር  […]

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ለሦስት ቀናት ሲያካሂድ የሰነበተው ጸሎተ ፍትሐትና ምሕላ ተጠናቀቀ!!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሽዋ ሀገረ ስብከት በኅልውና ዘመቻ ለሀገርና ለወገን በመዋደቅ ለተሰው የጸጥታ አባላትና በጦርነቱ የተነሣ ሕይወታቸውን ላጡ ምእመናን በደብረ ብርሃን ከተማ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ አደባባይ ከታኅሣሥ 5 -7 ለሦስት ቀናት ሲያካሂድ የሰነበተው ጸሎተ ፍትሐትና ጸሎተ ምሕላ ተጠናቅቋል:: ለሦስት ቀናት የተካሄደውን ጸሎተ ፍትሐትና ምሕላ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ […]

የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሆስፒታል ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች የሚውል 400 ሽህ ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ !!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የባህር ዳር ሀገረ ስብከት በባህር ዳር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች የሚውል 400 ሽህ ብር የሚገመት ድጋፍ አድርጓል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃምንጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች በሆስፒታሉ በመገኘት ታካሚ የፀጥታ አካላትን ጎብኝተዋል፣ የህክምና መስጫ ግብአቶችንና አልባሳትንም ለሆስፒታሉ አስረክበዋል። በድጋፍ ርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ብፁዕነታቸው […]

በምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ገብርኤል፣ ቅ/አርሴማ ወአቡነ አዳም ቤተ ክርስቲያን የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

በምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ገብርኤል፣ ቅ/አርሴማ ወአቡነ አዳም ቤተ ክርስቲያን የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ቅዳሴ ቤቷ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና እጅግ በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ውሏል። በበዓሉ በሊቃውንት “ሃሌ ሉያ ቤተ ክርስቲያን፡ መስቀለ ክርስቶስ መሠረታ…፣ በደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንም “እንተ ተሐንጸት በእደ ካህናት፡ ወተቀደሰት ቤተ ክርስቲያን በአፈ ጳጳሳት” የሚል ያሬዳዊ ዝማሬ ተዘምሯል። በዕለቱ መ/መንክራት ግርማ ወንድሙ ትምህርት […]

ርስዒ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ: ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ

በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን ዓመታዊ ክብረ በዓል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ውሏል። በበዓሉ ዕለቱን በተመለከተ ያሬዳዊ ዝማሬ፣ መንፈሳዊ ትምህርትና ወቅቱን በተመለከተ አባታዊ ምክር በብፁዓን አባቶችና በሊቃውንት ቀርቧል። በሊቃውንት “ይቤላ ሰሎሞን ለማርያም ርግብየ ሠናይት…፤ በገዳሙ የሰንበት ትምህርት ቤት […]

“ልጆቻችሁን ወደ ቤተ ክርስቲያን አምጧቸው” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዓመታዊ ክብረ በዓልና የጻድቁ የአቡነ ዜና ማርቆስ የዕረፍት በዓል በጉራጌ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኘው በምሁር ኢየሱስ ገዳም በጋራ ተከብሮ ዋለ። ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በበዓሉ ላይ ለተገኙት ምእመናን ትምህርት አስተላልፈዋል። ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሶስት ዓመት ሲሆናት […]

የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት የዕድሳት ሥራ የሳይት ርክክብ ተካሄደ!!!

በዘመናዊ መልኩ ታድሶ ለአገልግሎት ምቹ የማድረግ ሥራ የተጀመረው የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት ዝርዝር ጥናቶችን እንዲያጠና በተሰየመው ኮሚቴ አማካኝነት የቅድመ ግንባታ ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል። የጥናት ኮሚቴው የጥምቀት በዓልን መቃረብ ተከትሎ የግንባታ ሥራው በአስቸኳይ እንዲጀመር ማድረግ እንዲቻልና ለግንባታ ሥራው መፋጠን ይረዳ ዘንድ የግብዣ ጨረታ እንዲወጣ የሚቻልበትን ሁኔታን ማመቻቸት እንደሚገባ መክሯል። የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሊቀ […]

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በአሸባሪው ህውሓት የደረሰበትን ሁለንተናዊ ጉዳት የሚያጠና ቡድን አቋቁሞ ሥራ መጀመሩን ገለጸ !!!

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች በአሸባሪው የህውሓት ቡድን በካህናት እና በምእመናን ሕይወት የደረሰውን ጭፍጨፋ፣ እንዲሁም በገዳማትና አድባራቱ የደረሰውን ቁሳዊ ጉዳትና ውድመት የሚያጠና የልኡካን ቡድን አቋቁሞ የጥናት ሥራ መጀመሩን ከጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በተሰጠው የሥራ መመሪያ መሠረት የልኡካን ቡድኑ በጦርነቱ የደረሰውን የጉዳት መጠንና ውድመት ለይቶ ከማጥናት ባሻገር […]

በጉራጌ ሀገረ ስብከት ጽ.ቤት ሲካሄድ የቆየው 17ኛው የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ጉባኤ ባለ14 ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ !!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ዜና ማርቆስ ዘምሁር መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራች ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ርእሰ መንበርነት ከህዳር 24-25 ቀን 2014 ዓ.ምሲካሄድ የቆየው 17ኛው የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቋል። የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የስብሰባ አዳራሽ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት