• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳሰ ብፁዕ አቡነ መልከፄዴቅ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው በቃሉ ተራራ አቡነ ኃብተማርያም ገዳም የሥራ ጉብኝት አደረጉ

ታኅሣሥ 26 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳሰ ብፁዕ አቡነ መልከፄዴቅ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው በቃሉ ተራራ አቡነ ኃብተማርያም ገዳም የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። ብፁዕነታቸው በገዳሙ በሌሊት ተገኝተው የነግህ ጸሎተ ኪዳን አድርሰዋል።በቦታው መልአከ ሕይወት ቆሞሰ አባ ወልደ ኢየሱስ የሀገረ ስብከቱ የካህናት አሰተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ፣ የገዳሙ አሰተዳዳሪ ክቡር […]

በዓለ ጥምቀት የሀገር እና የዓለም ሕያው ቅርስ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው መንፈሳዊ የምሥጋና መርሐ ግብር በጃንሆይሜዳ (ጃንሜዳ) ተደረገ

ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፡ የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፡ የሶማሌና ምሥራቅ ሀረርጌ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳደር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለወልድ ተሰማ፡ የጠቅላይ ቤተ […]

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በልደታ ክፍለ ከተማ ሥር የሚገኘው የገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ጎበኙ

ታኅሣሥ 25 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በልደታ ክፍለ ከተማ ሥር የሚገኘው የገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ጎብኝተው ምእመናኑን ባርከዋል። በቦታው መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ነጋሽ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ፣ ሊቀ ትጉኃን ደማሙ የልደታ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት የሰው ኃይል ክፍል ኃላፊ፣ […]

አዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት በዳግማዊ ደብረ ሊባኖስ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ዓመታዊው የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የልደታቸው ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ

በዛሬው ዕለት ታኅሣሥ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ነጋሽ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ፣ የገዳሙ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን አባ ኃይለማርያም፣የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣የገዳሙ አገልጋዮችና የሰንበት ትምህርት […]

የአዲስ የአበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የብሥራት ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ

ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ/ም የጉራጌ እና የአዲስ አበባ አህገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ነጋሽ፡ የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ መ/ም ዘካርያስ ዐዲስ ፡የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አስተዳደሪ መልአከ አሚን ለይኩን አበጀ፡ የደብሩ ዋና ጸሐፊ […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት በመንበረ መንግሥት /ግቢ/ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓመታዊው የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

በዛሬው ዕለት ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት /ግቢ/ ቅዱስ ገብርኤል ገዳማት የበላይ ጠባቂ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ዋና ክፍል ኃላፊ መ/ብ ሳሙኤል ደምሴ፣የአራዳና ጉለሌ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/አሚን ቆሞስ አባ ላ/ማርያም […]

የቀበና ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅ/ገብርኤል አዲሱ መቃኞ ቤተ ክርስቲያን ተመረቀ

ታኅሣሥ 18/2013 ዓ/ም በካሳንችስ ዓድዋ ድልድይ የሚገኘው አዲሱ የተሠራ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅ/ገብርኤል መቃኞ ቤተ ክርስቲያን ተመርቆ ተባርኳል። በመርሃ ግብሩ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ዋና ክፍል ኃላፊ መ/ብ ሳሙኤል ደምሴ፥ የየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ እሰኪያጅ መጋቤ ትፍስሕት ግርማ አሰፋ፥ የየካ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ሠራተኞች፥ የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መ/ሰላም አበበ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን አካለወልድ ተሰማ ፣ ዋና ጸሐፊው መ/ር ታዴዎስ ሽፈራው እና ሌሎችም የየክፍሉ ዋና ኃላፊዎች ከአድባራት ና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ጋር ትውውቅ አደረጉ

በዛሬው ዕለት ታህሳስ 15/2013 ዓ/ም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን አካለወልድ ተሰማ ፣የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መ/ር ታዴዎስ ሽፈራው የየክፍሉ ዋና ኃላፊዎች፣የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ የስብሰባ አዳራሽ የትውውቅ መርሃ ግብሩ ተካሂዷል።በትውውቅ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ከየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጸ/ቤት ሠራተኞችና በክፍለ ከተማው ሥር ከሚገኙት የአድባራትና የገዳማት አገልጋዮች ጋር ትውውቅ አደረጉ

ዛሬ ታህሳስ 14/2013 ዓ/ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በየካ ደበረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ከየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሠራተኞች እና በክፍለ ከተማው ሥር ከሚገኙት የ46 ገዳማትና አድባራት አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፥ ምክትል ሊቃነ መናብርት፥ ጸሓፊዎች፥ ስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች እና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ጋር የትውውቅ መርሐ ግብር […]

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዕቅድ ዝግጅት እና አፈጻጸም እንዲሁም ክትትልና ግምገማን በተመለከተ ሥልጠና ተሰጠ

ዛሬ ታህሳስ 13/2013 ዓ/ም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፥ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊና የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፥ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን አካለወልድ ተሰማ ፥ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ስብሐት ሳህሉ፥ የሁለቱ አህጉረ ሰብከቶች የዋና ክፍል ኃላፊዎች እና […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን