• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ዓመታዊው የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ

ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፈ፣ የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ መ/አሚን አባ ላዕከ ማርያም፣ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሲራክ እንዲሁም የደብሩ ማኅበረ […]

4.1

በዓለ አስተርእዮ

አስተርእዮ፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ አስተርእዮ ማለትም መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው፡፡በግሪክ ቋንቋ ኤጲፋንያ ይባላል ኤጲፋንያ ማለት መገለጥ፤ መታየት ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ዘመን ዘመነ አስተርእዮ ይባላል የመገለጥ፣ የመታየት ዘመን ማለት ነው፡፡ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ሰው ሆኖ የተገለጠበት ዘመን ስለሆነ እና እንዲሁም በጥምቀቱ አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠበት ዘመን […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለወልድ ተሰማ በመካኒሳ ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካቴድራል በመገኘት የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴንና የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

በዛሬው ዕለት ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለወልድ ተሰማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በመካኒሳ ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካቴድራል በመገኘት የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴንና የተጠናቀቁ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።በጉብኝት መርሃግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊና የአቃቂ […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አሁናዊ ፈተና እና ችግር መነሻ ምክንያቱ የስብከት ወንጌል አገልግሎት መዳከም መሆኑ ተገለጸ

ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለወልድ ተሰማ፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከት ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ ዋና ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ እና የሀገረ ስብከቱ ዋና ፀሐፊ መ/ር ታዲዎስ ሽፈራው እንዲሁም የሰባቱም ክፍላተ ከተማ የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች እና የሁሉም አድባራትና ገዳማት የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለborn again mental disorder rehabilitation center ድጋፍ አደረገ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ምግባረ ሰናይ ዋና ክፍል አስተባባሪነት የተሰበሰቡ የትምህርት፣ የልብስና የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶችን ለborn again mental disorder rehabilitation center የበጎ አድራጎት ድርጅት አስረክቧል፡፡ድጋፉ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን አካለወልድ ተሰማ ለድርጅቱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ልዑል ብረሃነ አስረክበዋልborn again mental disorder rehabilitation center ሕጋዊ የበጎ አድራጎት […]

የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ዓመታዊ ክብረ በዓል፣ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ

ጥር 04 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የምዕራብ አውስትራልያ ሊቀ ጳጳስ፣ መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፈ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ ፣ መ/አሚን ቆሞስ አባ ላ/ማርያም የአራዳ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መ/አሚን ቆሞስ አባ […]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለአዲስ አባባ ከተማ አስተዳድር የገና ስጦታ አበረከተ

በአዲስ አበባ የሃይማኖቶች ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢ እና የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፅዕ አቡነ መልኬ ጼዴቅ የተመራ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቅዋማት ጉባኤ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ ከንቲባ እና ከፍተኛ የሥራ አመራሮች እንኳን አደረሳቹ በማለት በከተማዋ ለተሰሩ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ሥራዎች በርቱ በማለት የገና ስጦታ ማበርከታቸውንና የከተማ አስተዳደሩ […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤ/ክ ዓመታዊው የቅዱስ አማኑኤል ክብረ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

በዛሬው ዕለት ታኅሣሥ 28 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፈ፣ የአዲስ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ሃይማኖት ጸጋዬ ገ/ዮሐንስ፣ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ መ/ገነት ቀሲስ በቀለ ዘውዴ፣ የካቴድራሉ ጸሐፊ መ/ሥርዓት እጓለ፣ የካቴድራሉ ካህናትና ዲያቆናት፣የካቴድራሉ […]

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

ብፁዕነታቸው “በእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው” እንደገለጹት የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ስናከብር ” ሕጻን ተወልደ ለነ ወልድ ተውህበ ለነ” (ት.ኢሳ 9፥6) ሕጻን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና የሚለውን መለኮታዊ ቃል በውስጣችን በማሰብ ማክበር እንደሚገባን መልእክት አስተላልፈዋል።ክብረ በዓላትን ስናከብር በአንዳንዶች ዘንድ እንደሚታው ሥጋዊ ነገሮች ላይ ብቻ ትኩረት ከማድረግ ተቆጥበን፤ይልቁንም ከምንም በላይ መንፈሳዊ መልእክቱና ይዘቱ ላይ ትኩረት ልናደርግ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገና በዓልን አስመልክቶ ለስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ አደረገ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ምግባረ ሰናይ አስተባባሪነት የተሰበሰበ የምግብ፣የልብስ፣ የጤናና የትምህርት ቁሳቁሶችን ለስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት አስረክቧል፡፡ድጋፉ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳሰ ለስለ አናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ፕሮግራም ኃላፊ ሙሉ ጌታ በቀለ አስረክበዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አንድ ቀን ድርጅቱን እንደሚጎበኙ ገልጸዋል፡፡ስለአናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ከፍተኛ የአእምሮ የአካል ጉዳት ያለባቸውና […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን