• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ ቤት በአሮጌ ቄራ ባለ 3B + G+15 ሕንጻ ሊገነባ መሆኑን ተገለጸ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በአሮጌ ቄራ ባለ 3B + G+15 ሕንጻ ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል የሕንጻው ግንባታ ዲዛይን ሂደት በኢንጅነር ታምሩ ጥላሁን ለብፁዓን አባቶች ገለጻ ተደርጓል ሕንጻው ለሀገረ ስብከቱ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለውና ከ70 በላይ ፓርክ ያለው መሆኑን ተገልጿል። በገለጻው የተገኙት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና […]

“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያዋ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኗ” ተገለጸ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያዋ የትምህርት ሚኒስተር ናት” ሲሉ ገለጹ። ብፁዕነታቸው ይህንን የተናገሩት በቀን 13/9/2013 ዓ.ም በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት ተሠርተው የተጠናቀቁትን G+1 እና G+4 ሕንጻዎችን በጸሎት በመረቁበት ዕለት ነው። G+1 ሕንጻው ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሲሆን G+4 የሆነው ሕንጻ ደግሞ ዛሬ ከመመረቁ ቀደም […]

“ጻድቅ መሆን የክርስቲያን ሁሉ ግዴታ ነው” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

“ጻድቅ መሆን የክርስቲያን ሁሉ ግዴታ ነው” ሲሉ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ገለጹ። ብፁዕነታቸው ይህንን ያሉት በቀን 12/09/2013 ዓ.ም በደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ገዳም ተገኝተው የጻድቁን የአቡነ ተክለሃይማኖትን የፍልሰተ ዐፅሙን ክብረ በዓል ባከበሩበት ነው። ጻድቅ ማለት እውነተኛ ማለት ነው፤ እውነት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሕርይ ነው፤ እርሱ እውነት ስለሆነ ርኩሰትንና ውሸትን ይጸየፋል […]

መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፉ መስቀል አደባባይን አሰመልከተው በተናገሩት ቃል ሀገረ ስብከቱ መግለጫ እንደሚሰጥ ገለጸ

ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የአስተዳደር ጉባኤ መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፉ የመስቀል አደባባይ ጉዳይን አስመልክቶ “በቤተክርስቲያን ስም ይቅርታ እንጠይቃለን” ብለው በሰጡት ንግግር ዙሪያ ተወያየ። የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ የሆኑት መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፉ በጉባኤ ፊት ቀርበው ጥያቄም ተጠይቀዋል፡፡ ከተጠየቁት ጥያቄዎች መካከል፦ በቤተክርስቲያኒቱ ስም […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዘመኑን በዋጀ መልኩ በአዲስ መልክ ለማደራጀት የወጣ ውስጠ ደንብ ረቂቅ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት

ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ ያለው መዋቅራዊና አደረጃጀት የሚያጠና 13 አባላት ያሉት ኮሚቴ ያቀረበው ውሰጠ ደንብ ረቂቅ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በአጥኚው ኮሚቴ የቀረበው ውስጠ ደንቡ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ እየተመራ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለ ወልድ ተሰማና የየዋና ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተርጎበታል። ውስጠ ደንቡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዘመኑን […]

“ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች የኅብረት ቤት ናት” በማለት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ገለጹ

ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች የኅብረት ቤት መሆኗን የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በመልእክታቸው ገለጹ። ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች የኅብረት ቤት ናት፤ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት አንድ የሆኑ ሁሉ የሚጠመቁባት፣ የክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን የሚቀበሉባት በመጨረሻም በሰላም የሚያርፉባት ናት በማለት አብራርተዋል። ብፁዕነታቸው ይህንን መልእክት ያስተላለፉት ግንቦት 7 ቀን 2013 ዓ/ም በየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ስር በሚገኘው […]

“ከአሁን በኋላ ከውጪ ሆናችሁ ሳይሆን ከውስጥ ሆናችሁ አስቀድሱ” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ “ከአሁን በኋላ ከውጪ ሆናችሁ ሳይሆን ከውስጥ ሆናችሁ አስቀድሱ” በማለት መልእክት አስተላለፉ። ብፁዕነታቸው መልእክቱን ያስተላለፉት በቀን 6/09/2013 ዓ.ም አዲስ ተገንብቶ የተጠናቀቀውን የኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን በጸሎት ከባረኩ በኋላ ነው። ግዙፍ የሆነው ይህ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በጸሎት ስለተባረከ ከአሁን በኋላ በውጪ ቆማችሁ አታስቀድሱ፣ እንደመቃኞው […]

መሠረታዊ የኮምፒውተር ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች

የተለያዩ መሠረታዊ የኮምፒውተር ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች አሉ፡፡ከእነዚህ ውስጥ ሁሉም ሰው የጥቃት ዒላማ ውስጥ መሆኑን መረዳትና ለዚህ ሁልጊዜም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ነው፡፡ለሶፍትዌሮች ወቅታዊና የዘመኑ ሶፍትዌሮችን መጫንም የኮምፒውተሮችን ደህንነት መጠበቂያ መሠረታዊ መንገድ መሆኑ ይነገራል፡፡በተጨማሪም ቀጥተኛ የደህንነት ዝመና በየጊዜው የሚያቀርቡ እንደ ክሮም ወይም ፋየር ፎክስ ያሉ የድረ-ገጽ ማፈላለጊያዎችን መጠቀም ፣እንደ ፍላሽ፣ ሀርድ ዲስክ እና የመሳሰሉ ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎችን ሲጠቀሙ […]

በዚህ ዘመን ለመብል የሚሞት ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ የሚሞት አባት/ጳጳስ ያስፈልጋል ተባለ

የ2013 ዓ/ም የጌታችን ትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የእንኳን አደረሶት ዝግጅት በሀገረ ስብከቱ በድምቀት ተከብሮ ውሏል። በዝግጅቱ የተገኙት በሰሜን አመሪካ የካልፎርንያ አከባቢ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ትምህርት ሰጥተዋል። ጌታችን “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? ብሎ ጴጥሮስን ሲጠይቀው “አዎን ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” ሲለው “ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ በጎቼን አሰማራ” የሚል ትልቅ ሐላፊነት አሸከሞታል […]

በቦሌ ደ/ገ/ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ዕረፍት በድምቀት ተከበረ

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በቦሌ ደ/ገ/ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጊዮርግስ በዓለ ዕረፍት በድምቀት ተከብሯል። የ2013 የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ዕረፍቱ ሚያዚያ 23 በሕማማት ውስጥ የዋለ በመሆኑ ክብረ በዓሉ ተሻግሮ ዛሬ ሚያዚያ 27/2013 ዓ/ም ተከብሮ ውሏል። በዕለቱ በመጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ኒቆዲሞስ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራ የመጽሐፍ መምህር ትምህርት […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን