• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በርእሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተጠናቀቁ ሦስት ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር በምትገኘው ርእሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበጀተ ዓመቱ በደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት፡ በበጎ አድራጊ ኦርቶዶክሳውያንና በማኅበረ ካህናቱ የጋራ ትብብር የተጠናቀቁ ሦስት ፕሮጀክቶች በአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ተመርቀዋል፡፡ከሦስቱ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውና በደብሩ ካህናት የአንድ ወር ደመወዝ ስጦታ የታደሰው የዳግማዊ […]

“በሥራ ለተተረጎመ ቦታ በቃል ብዙ ማውራት አስፈላጊ አይደለም “…ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ

የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በርእሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበጀተ ዓመቱ የተሠሩ የልማት ሥራዎችንና የንጉሡን ቤተ መንግሥትና የቤተ ክርስቲያኑን ውስጣዊ ክፍል ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ የተደረገውን ዕድሳት በመረቁበት ወቅት ያስተላለፉት መልእክት ነው፡፡ብፁዕነታቸው በገዳሙ የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት አስተባባሪነት በደብሩ ካህናትና በበጎ አድራጊ ኦርቶዶክሳውያን የጋራ […]

“ከሰው የሚጠበቀው ማመንና መታዘዝ ነው” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ 24 በሚባለው አካባቢ በሚገኘው በምዕራፈ ሰማዕታት ቅዱስ ገብርኤልና አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ክብረ በዓሉን የተመለከተ ትምህርት አስተላልፈዋል።የሕጻን ቅዱስ ቂርቆስንና የእናቱን የቅድስት እየሉጣን የእምነት ጽናት አብራርተዋል።በሕይወታቸውና በልባቸው ውስጥ ሰማያዊውን ንጉሥ ስላነገሡ ምድራዊው ንጉሥ በወታደሮቹ […]

በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ መመሪያ ሰጭነት ተገንብቶ የተጠናቀቀው የአዳሪ ትምህርት ቤት ደቀ መዛሙርትን ተቀበለ

በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ መመሪያ ሰጭነት በጉራጌ አህጉረ ስብከት ተገንብቶ የተጠናቀቀው የአዳሪ ትምህርት ቤት ደቀ መዛሙርትን ተቀበለ።ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ለደቀመዛሙርቱ “የእንኳን ደህና መጣችሁ” መልእክት አስተላልፈውላቸዋል።ብፁዕነታቸው የትምህርት ቤቱ መገንባት ዋናው ዓላማ ካህናትን በማሰልጠን ምእመናንን በመንፈሳዊ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ እንደሆነ አውስተዋል።አያይዘውም ካህናቱ በትምህርት ቆይታቸው የሚሰጣቸውን ሥልጠናዎች በአግባቡ በመውሰድ መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ […]

የብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አራተኛ በዓለ ሲመት በድምቀት ተከብሮ ዋለ

የብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ አራተኛ በዓለ ሲመት በወልቂጤ ከተማ በደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ካቴድራል በድምቀት ተከብሮ ዋለ።ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ባስተላለፉት መልእክት በዓሉ የአንድ መንፈሳዊ አባት በዓል ሳይሆን የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓል ነው ሲሉ ገልጸዋል።የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለበርካታ ዘመናት ከግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን በሚመጡ ጳጳሳት ስትተዳደር እንደነበር አውስተዋል።ይህም ለቤተክርስቲያን በተለይ […]

“አስከፊ የኑሮ ሁኔታና ቅንነት ከጎደለው የካራን አስተሳሰብ ወጥተን የዕረፍት ምድራችን ወደ ሆነችው ከነዓን እንግባ“…ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ

የአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በርካታ አገልጋዮችና ኦርቶዶክሳዊ ምዕመናን በተገኙበት ተከብሮ ውሏል፡፡በአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጋባዥነት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ ፕሬዘዳንትና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ፊልጶስ የዕለቱን ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡በትምህርታቸውም የእምነት አርበኛ የሆነውን የአብርሃምን የጥሪ ሕይወት: ለጠራው […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰ/ት/ቤት “ራዕየ ቴዎፍሎስ” በሚል ስያሜ ሊያስገነባ ያቀደውን ሕንጻ ሥራውን አስጀመሩ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በመገኘት በሰ/ት/ቤቱ “ራዕየ ቴዎፍሎስ” በሚል ስያሜ ሊገነባ የታቀደውን ሕንጻ ሥራውን አስጀመሩ።ብፁፅነታቸው ሰንበት ትምህርት ቤት ለቤተክርስቲያን የችግኝ ጣቢያ ነው ሲሉ የሰንበት ትምህርት ቤትን አስፈላጊነት ጠቅሰዋል።የችግኝ ጣቢያ ችግኝ የሚበቅልበትና ለተለያዩ ቦታዎች ሥርጭት የሚደረግበት እንደሆነ ሁሉ ሰንበት ትምህርት ቤትም ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ ጳጳሳት፣ ለቤ/ክንና […]

” ቅድምያ ከሁሉም በላይ ፍቅር፣ ሰላምና አንድነት ላይ መሥራት ያስፈልጋል” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቅድምያ ከሁሉም በላይ ፍቅር፣ ሰላምና አንድነት ላይ መሥራት እንደሚያስፈልግ መልእክት አስተላለፉ።ብፁዕነታቸው መልእክቱን ያስተላለፉት በቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤ/ክ በመገኘት አዲስ እየተገነባ የሚገኘውን ግዙፉን ሕንጻ ቤ/ክን በጎበኙበት ነው።በግንባታ ላይ የሚገኘው ሕንጻ ቤተክርስቲያን 5200 ካሬ ላይ ያረፈ ስለመሆኑም ተገልጿል።ብፁዕነታቸው ቤተክርስቲያኑ ሊሠራ ላቀዳቸው G+2 እና G+3 ሕንጻዎችም […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የ12 አቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች እድሳት ሊያካሄድ ነው

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እድሳቱን የሚያካሂደው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ነው።የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለ ወልድ ተሰማ ለእድሳት መርሐ ግብሩ አንድ ሚሊዮን ብር መመደቡን አስታውቀዋል።ክቡር ዋና ሥራ አስኪያጁ ሀገረ ስብከቱ በአገራችን የተለያዩ ችግሮች ሲገጥሙ መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንም ተናግረዋል።የ12 አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶችን እድሳት ለማከናወን ሙሉ ዝግጅት ሲደረግ […]

“ችግኝን መትከልና መንከባከብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ነው” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ “ችግኝን መትከልና መንከባከብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ነው” ሲሉ መልእክት አስተላለፉ።ብፁዕነታቸው መልእክቱን ያስተላለፉት በጉለሌ የእፅዋት ማዕከል በመገኘት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ባካሄዱበት ነው።የችግኝ ተከላ መርሐግብሩን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ጋር በመተባበር ነው።“አብሮነትን […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን