• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት የዕረፍት በዓል በመርካቶ ደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ገዳም ተከብሮ ዋለ

ነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም( አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ )ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዕለቱን በተመለከተ ትምህርት አስተላልፈዋል።ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ይህንን ዓለም በመናቅና ሕይወታቸዉን ለእግዚአብሔር በመስጠት እንደኖሩ ገልጸዋል።ጻድቁ በጾም፣ በጸሎትና በምስጋና ሕይወት እንደኖሩም ጠቅሰዋል።አያይዘውም ወንጌልንም በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ለምእመናን መስበካቸውን አውስተዋል።በመድኀኒታችንና በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተለያዩ ተአምራትን ስለማድረጋቸውም […]

የቦሌ ክፍለ ከተማን ሥራ እዚሁ መጥቼ እሠራለሁ……ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ

(ነሐሴ 22 ቀን 2013 ዓ.ም )(አዲስ አበባ÷ኢትዮጵያ)የአዲስ አበባ እና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሁለንተናዊ ዕድሳት ተደርጎለት ለምርቃት የበቃውን የቦሌ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ነሐሴ 22 ቀን 2013 ዓ.ም በመረቁ ወቅት ያስተላለፉት መልእክት ነው፡፡ምቹ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር ታሳቢ አድርጎ የተጀመረው ሁለንተናዊ ዕድሳት በአጭር ጊዜ በመጠናቀቁ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነትና […]

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሠራተኞች መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ሥልጠና መስጠት ተጀመረ

(ነሐሴ 22 ቀን 2013 ዓ/ም) አዲስ አበባ: ኢትዮጵያየአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዋና ክፍል፣ የክፍልና ልዬ ልዩ ሠራተኞች በሀገረ ስብከቱ የኮምፒዩተር ማሰልጠኛ ማዕከል መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ሥልጠና መውሰድ ጀምረዋል።ሥልጠናው በብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ በሀገረ ስብከቱ አይቲና ዶክሜንቴሽን ዋና ክፍል አስተባባሪነት የተዘጋጀ ነው።ሥልጠናው የሚሰጠው ሥልጠና ለመውሰድ የተዘጋጀውን ቅጽ ለሞሉ […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ጾመ ፍልሰታ መግቢያ አስመልክተው መመሪያዎችን አስተላለፉ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ጾመ ፍልሰታ መግቢያ አስመልክተው መመሪያዎችን አስተላለፉ።ብፁዕነታቸው መመሪያዎችን ያስተላለፉት ለአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ቄሰ ገበዞች ነው።“ለሁሉም ጊዜ አለው” የሚለውን የእግዚአብሔርን ቃል መነሻ በማድረግ ከ ነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 16 ቀን ወይም አስከ 21 ቀን የምንጾምበት ጊዜ ነው ብለዋል።አያይዘውም ወደ ፈጣሪያችን አብዝተን የምንጸልይበት […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ያለፈውን የበጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትንና የመጪውን የበጀት ዓመት ዕቅድ እየገመገመ ይገኛል

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ያለፈውን የ2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትንና የመጪውን የ2014 ዓ.ም የበጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ በመገምገም ላይ ይገኛል።በአዲስ አበባና በጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ መመሪያ ሰጭነት ከሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የግምገማ መርሐ ግብሩ በመካሄድ ላይ ነው።የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ራሱን ችሎ በሊቀ ጳጳስ እንዲመራ […]

ሁለት ዓመት ከስድስት ወር የፈጀው አለመግባባት በሰላም ተፈታ

በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ሰበካ ጉባኤው መካከል ተከስቶ የነበረው አለመግባባት በሰላም ተፈታ።መርሐ ግብሩ በብፁዕ አቡነ ማርቆስ የጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌል መምሪያ የበላይ ጠባቂ ጸሎትና ቡራኬ ተከፍቷል።የችግሩ ምክንያት በሰንበት ትምህርት ቤቱና በሰበካ ጉባኤው መካከል ሁለገብ ሕንጻን በመገንባት በኩል የሃሳብ ልዩነት በመፈጠሩ እንደሆነ ተብራርቷል።በአዲስ አበባና በጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ […]

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት የፍቅር ማዕድ መርሐ ግብር ተካሄደ

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች መጪውን የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ጾመ ፍልሰታ ምክንያት በማድረግ የፍቅር ማዕድ መርሐ ግብር አካሄዱ።የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ ፍቅር ለሰው ልጆች ከእግዚአብሔር የተሰጠ ልዩ ስጦታ መሆኑን በአጋፔ ማዕድ መርሐ ግብሩ ላይ አብራርተዋል።አብሮ በጋራ የፍቅር ማዕድ መቋደስ መተሳሰብን፣ መረዳዳትን፣ መተዛዘንንና የአብሮነት ስሜትን ያሳድጋልም ብለዋል።ፍቅር […]

በጉራጌ ሀገረ ስብከት በእዣ ወረዳ የሚገኘው የመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል እና አባ ሳሙኤል ገዳም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ

በጉራጌ ሀገረ ስብከት እዥ ወረዳ በገጨ ቀበሌ የሚገኘው የመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል እና አባ ሳሙኤል ገዳም በብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ተመርቆ በዛሬው ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡በአንድ ኦርቶዶክሳዊ ባለሀብት መሬት ሰጭነት የተመሠረተው አዲሱ ገዳም የመሠረት ድንጋዩ ከተጣለ ከ6 ወራት በኋላ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት መብቃቱ በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል፡፡በአካባቢው ምእመናን እና በአንድ ባለሀብት የጋራ ትብብር በከፍተኛ ፍጥነት […]

በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የተመራው ልዑክ የጉራጌ ሀገረ ስብከትን የልማት ሥራዎች በመጎብኘት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባና በጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የተመራና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተት ልዑክ በጉራጌ ሀገረ ስብከት በአጭር ጊዜ ተሠርተው የተጠናቀቁትን እና በመጠናቀቅ ላይ ያሉትን የልማት ሥራዎችና በቴክኖሎጅ ዘርፍ እየተሠሩ የሚገኙትን የማስፋፊያ ሥራዎችመጎብኘታቸውተገልጿል፡፡ብፁዕነታቸው በሀገረስብከታቸው ከሚያደርጉትሐዋርያዊ አገልግሎት፡ አባታዊ አመራርና ቡራኬ ባሻገር በመንበረ ጵጵስናቸው ግቢ ውስጥ በርካታ የልማት ሥራዎችን ማሰራታቸውን የሀገረ ስብከቱ መረጃ ያመላክታል፡፡ሀገረ […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በአሮጌ ቄራ ሊገነባው ያቀደው ባለ 3B+ G+15 ሕንጻ ግንባታ ባርከው አስጀመሩ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በአሮጌ ቄራ ሊገነባው ያቀደው ባለ 3B + G+ 15 ሕንጻ ግንባታው በጸሎት ባርከው አስጀምረዋል።ብፁዕነታቸው ሕንጻው ለቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለውና በብዙ ምእመናን በጉጉት የሚጠበቅ መሆኑን በመጥቀስ ግንባታው እንዲፋጠን ትእዛዝ ሰጥተዋል።ሕንጻው ተጠናቅቆ ሥራውን ጀምሮ ማየት የሚናፍቅ ብዙ ነው ያሉት ብፁዕ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን