• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ጾመ ፍልሰታ መግቢያ አስመልክተው መመሪያዎችን አስተላለፉ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ጾመ ፍልሰታ መግቢያ አስመልክተው መመሪያዎችን አስተላለፉ።ብፁዕነታቸው መመሪያዎችን ያስተላለፉት ለአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ቄሰ ገበዞች ነው።“ለሁሉም ጊዜ አለው” የሚለውን የእግዚአብሔርን ቃል መነሻ በማድረግ ከ ነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 16 ቀን ወይም አስከ 21 ቀን የምንጾምበት ጊዜ ነው ብለዋል።አያይዘውም ወደ ፈጣሪያችን አብዝተን የምንጸልይበት […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ያለፈውን የበጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትንና የመጪውን የበጀት ዓመት ዕቅድ እየገመገመ ይገኛል

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ያለፈውን የ2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትንና የመጪውን የ2014 ዓ.ም የበጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ በመገምገም ላይ ይገኛል።በአዲስ አበባና በጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ መመሪያ ሰጭነት ከሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የግምገማ መርሐ ግብሩ በመካሄድ ላይ ነው።የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ራሱን ችሎ በሊቀ ጳጳስ እንዲመራ […]

ሁለት ዓመት ከስድስት ወር የፈጀው አለመግባባት በሰላም ተፈታ

በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ሰበካ ጉባኤው መካከል ተከስቶ የነበረው አለመግባባት በሰላም ተፈታ።መርሐ ግብሩ በብፁዕ አቡነ ማርቆስ የጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌል መምሪያ የበላይ ጠባቂ ጸሎትና ቡራኬ ተከፍቷል።የችግሩ ምክንያት በሰንበት ትምህርት ቤቱና በሰበካ ጉባኤው መካከል ሁለገብ ሕንጻን በመገንባት በኩል የሃሳብ ልዩነት በመፈጠሩ እንደሆነ ተብራርቷል።በአዲስ አበባና በጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ […]

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት የፍቅር ማዕድ መርሐ ግብር ተካሄደ

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች መጪውን የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ጾመ ፍልሰታ ምክንያት በማድረግ የፍቅር ማዕድ መርሐ ግብር አካሄዱ።የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ ፍቅር ለሰው ልጆች ከእግዚአብሔር የተሰጠ ልዩ ስጦታ መሆኑን በአጋፔ ማዕድ መርሐ ግብሩ ላይ አብራርተዋል።አብሮ በጋራ የፍቅር ማዕድ መቋደስ መተሳሰብን፣ መረዳዳትን፣ መተዛዘንንና የአብሮነት ስሜትን ያሳድጋልም ብለዋል።ፍቅር […]

በጉራጌ ሀገረ ስብከት በእዣ ወረዳ የሚገኘው የመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል እና አባ ሳሙኤል ገዳም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ

በጉራጌ ሀገረ ስብከት እዥ ወረዳ በገጨ ቀበሌ የሚገኘው የመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል እና አባ ሳሙኤል ገዳም በብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ተመርቆ በዛሬው ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡በአንድ ኦርቶዶክሳዊ ባለሀብት መሬት ሰጭነት የተመሠረተው አዲሱ ገዳም የመሠረት ድንጋዩ ከተጣለ ከ6 ወራት በኋላ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት መብቃቱ በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል፡፡በአካባቢው ምእመናን እና በአንድ ባለሀብት የጋራ ትብብር በከፍተኛ ፍጥነት […]

በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የተመራው ልዑክ የጉራጌ ሀገረ ስብከትን የልማት ሥራዎች በመጎብኘት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባና በጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የተመራና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተት ልዑክ በጉራጌ ሀገረ ስብከት በአጭር ጊዜ ተሠርተው የተጠናቀቁትን እና በመጠናቀቅ ላይ ያሉትን የልማት ሥራዎችና በቴክኖሎጅ ዘርፍ እየተሠሩ የሚገኙትን የማስፋፊያ ሥራዎችመጎብኘታቸውተገልጿል፡፡ብፁዕነታቸው በሀገረስብከታቸው ከሚያደርጉትሐዋርያዊ አገልግሎት፡ አባታዊ አመራርና ቡራኬ ባሻገር በመንበረ ጵጵስናቸው ግቢ ውስጥ በርካታ የልማት ሥራዎችን ማሰራታቸውን የሀገረ ስብከቱ መረጃ ያመላክታል፡፡ሀገረ […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በአሮጌ ቄራ ሊገነባው ያቀደው ባለ 3B+ G+15 ሕንጻ ግንባታ ባርከው አስጀመሩ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በአሮጌ ቄራ ሊገነባው ያቀደው ባለ 3B + G+ 15 ሕንጻ ግንባታው በጸሎት ባርከው አስጀምረዋል።ብፁዕነታቸው ሕንጻው ለቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለውና በብዙ ምእመናን በጉጉት የሚጠበቅ መሆኑን በመጥቀስ ግንባታው እንዲፋጠን ትእዛዝ ሰጥተዋል።ሕንጻው ተጠናቅቆ ሥራውን ጀምሮ ማየት የሚናፍቅ ብዙ ነው ያሉት ብፁዕ […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በርእሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተጠናቀቁ ሦስት ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር በምትገኘው ርእሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበጀተ ዓመቱ በደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት፡ በበጎ አድራጊ ኦርቶዶክሳውያንና በማኅበረ ካህናቱ የጋራ ትብብር የተጠናቀቁ ሦስት ፕሮጀክቶች በአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ተመርቀዋል፡፡ከሦስቱ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውና በደብሩ ካህናት የአንድ ወር ደመወዝ ስጦታ የታደሰው የዳግማዊ […]

“በሥራ ለተተረጎመ ቦታ በቃል ብዙ ማውራት አስፈላጊ አይደለም “…ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ

የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በርእሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበጀተ ዓመቱ የተሠሩ የልማት ሥራዎችንና የንጉሡን ቤተ መንግሥትና የቤተ ክርስቲያኑን ውስጣዊ ክፍል ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ የተደረገውን ዕድሳት በመረቁበት ወቅት ያስተላለፉት መልእክት ነው፡፡ብፁዕነታቸው በገዳሙ የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት አስተባባሪነት በደብሩ ካህናትና በበጎ አድራጊ ኦርቶዶክሳውያን የጋራ […]

“ከሰው የሚጠበቀው ማመንና መታዘዝ ነው” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ 24 በሚባለው አካባቢ በሚገኘው በምዕራፈ ሰማዕታት ቅዱስ ገብርኤልና አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ክብረ በዓሉን የተመለከተ ትምህርት አስተላልፈዋል።የሕጻን ቅዱስ ቂርቆስንና የእናቱን የቅድስት እየሉጣን የእምነት ጽናት አብራርተዋል።በሕይወታቸውና በልባቸው ውስጥ ሰማያዊውን ንጉሥ ስላነገሡ ምድራዊው ንጉሥ በወታደሮቹ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን