• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት የዕድሳት ሥራ የሳይት ርክክብ ተካሄደ!!!

በዘመናዊ መልኩ ታድሶ ለአገልግሎት ምቹ የማድረግ ሥራ የተጀመረው የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት ዝርዝር ጥናቶችን እንዲያጠና በተሰየመው ኮሚቴ አማካኝነት የቅድመ ግንባታ ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል። የጥናት ኮሚቴው የጥምቀት በዓልን መቃረብ ተከትሎ የግንባታ ሥራው በአስቸኳይ እንዲጀመር ማድረግ እንዲቻልና ለግንባታ ሥራው መፋጠን ይረዳ ዘንድ የግብዣ ጨረታ እንዲወጣ የሚቻልበትን ሁኔታን ማመቻቸት እንደሚገባ መክሯል። የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሊቀ […]

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በአሸባሪው ህውሓት የደረሰበትን ሁለንተናዊ ጉዳት የሚያጠና ቡድን አቋቁሞ ሥራ መጀመሩን ገለጸ !!!

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች በአሸባሪው የህውሓት ቡድን በካህናት እና በምእመናን ሕይወት የደረሰውን ጭፍጨፋ፣ እንዲሁም በገዳማትና አድባራቱ የደረሰውን ቁሳዊ ጉዳትና ውድመት የሚያጠና የልኡካን ቡድን አቋቁሞ የጥናት ሥራ መጀመሩን ከጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በተሰጠው የሥራ መመሪያ መሠረት የልኡካን ቡድኑ በጦርነቱ የደረሰውን የጉዳት መጠንና ውድመት ለይቶ ከማጥናት ባሻገር […]

በጉራጌ ሀገረ ስብከት ጽ.ቤት ሲካሄድ የቆየው 17ኛው የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ጉባኤ ባለ14 ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ !!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ዜና ማርቆስ ዘምሁር መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራች ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ርእሰ መንበርነት ከህዳር 24-25 ቀን 2014 ዓ.ምሲካሄድ የቆየው 17ኛው የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቋል። የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የስብሰባ አዳራሽ […]

የጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በቆጠር ገድራ መካነ ቅዱሳን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ተከብሮ ዋለ!

የጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በጉራጌ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኘው ቆጠር ገድራ መካነ ቅዱሳን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና አቡነ ሀብተማርያም አንድነት ገዳም አዳሪ መንፈሳዊ ት/ቤት ተከብሮ ውሏል። ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ክብረ በዓሉን የተመለከተ ትምህርት ሰጥተዋል። ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ከራሳቸው ፍላጎት ይልቅ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸምና በመከተል መልካም ፍሬ […]

“ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር ንዋየ ቅድሣት ሀገር ናት !!!” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በተገኙበት በደብረ ምጥማቅ ሠአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል የእመቤታችን ንግሥ ተከብሮ ውሏል። በአውደ ምህረቱ የካቴድራሉ መምህራን “ሙሴኒ ርዕያ ሀገር ቅድስት የሚለውን እና አባ አቡነ አባ መምህርነ አባ መልከጴዴቅ” የሚለውን ለብፁዕነታቸው በሽብሻቦ አቀርበዋል። የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችም ታቦተ ሕጉ […]

ደቡብ ክልል የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመረቀ!

በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ መመሪያ ሰጭነት በጉራጌ አህጉረ ስብከት ተገንብቶ የተጠናቀቀው መንፈሳዊ ኮሌጅ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በጸሎት ተባርኳል።ኮሌጁም “ዜና ማርቆስ ዘምሁር መንፈሳዊ ኮሌጅ” ተብሎ ተሰይሟል። መንፈሳዊ ኮሌጆች ትውልዱን በመንፈሳዊ ሕይወት ለማነጽ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ጠቅሰዋል።አያይዘውም ደቀመዛሙርትን በማሰልጠን ምእመናንን በመንፈሳዊ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ብዙ መንፈሳዊ ኮሌጆች ለቤተክርስቲያኒቱ እንደሚያስፈልጉም […]

የ 2014 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በተመለከተ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ውይይት ተካሄደ

ነሐሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም( አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ )መጪውን የ 2014 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በተመለከተ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ውይይት ተካሄደ።በመስቀል አደባባይ የሚከበረውን የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓል የሚያዘጋጀው የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን በጥሩ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ ቀሲስ በቀለ ተሰማ ለብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት […]

የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት የዕረፍት በዓል በመርካቶ ደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ገዳም ተከብሮ ዋለ

ነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም( አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ )ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዕለቱን በተመለከተ ትምህርት አስተላልፈዋል።ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ይህንን ዓለም በመናቅና ሕይወታቸዉን ለእግዚአብሔር በመስጠት እንደኖሩ ገልጸዋል።ጻድቁ በጾም፣ በጸሎትና በምስጋና ሕይወት እንደኖሩም ጠቅሰዋል።አያይዘውም ወንጌልንም በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ለምእመናን መስበካቸውን አውስተዋል።በመድኀኒታችንና በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተለያዩ ተአምራትን ስለማድረጋቸውም […]

የቦሌ ክፍለ ከተማን ሥራ እዚሁ መጥቼ እሠራለሁ……ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ

(ነሐሴ 22 ቀን 2013 ዓ.ም )(አዲስ አበባ÷ኢትዮጵያ)የአዲስ አበባ እና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሁለንተናዊ ዕድሳት ተደርጎለት ለምርቃት የበቃውን የቦሌ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ነሐሴ 22 ቀን 2013 ዓ.ም በመረቁ ወቅት ያስተላለፉት መልእክት ነው፡፡ምቹ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር ታሳቢ አድርጎ የተጀመረው ሁለንተናዊ ዕድሳት በአጭር ጊዜ በመጠናቀቁ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነትና […]

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሠራተኞች መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ሥልጠና መስጠት ተጀመረ

(ነሐሴ 22 ቀን 2013 ዓ/ም) አዲስ አበባ: ኢትዮጵያየአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዋና ክፍል፣ የክፍልና ልዬ ልዩ ሠራተኞች በሀገረ ስብከቱ የኮምፒዩተር ማሰልጠኛ ማዕከል መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ሥልጠና መውሰድ ጀምረዋል።ሥልጠናው በብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ በሀገረ ስብከቱ አይቲና ዶክሜንቴሽን ዋና ክፍል አስተባባሪነት የተዘጋጀ ነው።ሥልጠናው የሚሰጠው ሥልጠና ለመውሰድ የተዘጋጀውን ቅጽ ለሞሉ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን