• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ሰው በመገደሉና በዓሉ በተገቢው ባለመከበሩ መንግሥት በጥልቅ ማዘኑን ይገልጻል…የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያ በዓለም ደምቃ እንድትታይ ከሚያደርጓት በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል። በበዓለ ጥምቀቱ የታዩት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ማኅበራዊ ዕሴቶች በዓሉ የኢትዮጵያውያን ለዘመናት የዘለቀ ውብ አብሮነትንም ለዓለም ያሳየ ሆኗል። በዓሉ የኢትዮጵያውያንን መፋቀር፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ሰላም በሚገልጽ መንገድ እንዳይከበር የተለያዩ አካላት የሸረቧቸውን ሤራዎች ሕዝቡና የጸጥታ አካላት ተናብበውና ተቀናጅተው አክሽፈውታል። ኢትዮጵያ የምታስተናግዳቸው […]

በቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በጊዜያዊነት ያረፉት የወይብላ ቅድስት ማርያምና ታቦተ ሚካኤል ወደ መንበረ ክብራቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ!!!

በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በወጣቶች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት የተነሣ ወደ ኋላ ተመልሰው ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በጊዜያዊነት ያረፉት የወይብላ ቅድስት ማርያምና ታቦተ ቅዱስ ሚካኤል ወደ መንበራቸው ክብራቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ። የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የተፈጠረውን ችግር በማረጋጋትና ምእመናንንም በማጽናናት ታቦታቱን ወደ መንበረ ክብራቸው የመመለስ ጉዞውን እየመሩ ይገኛሉ። […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ሁሉም ሰው ለሰላም የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍ አሳሰቡ !!!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ሁሉም ሰው ለሰላም የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለሕዝቡ ደህንነት እንዲሰራ  ጥሪ አስተላልፈዋል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ባህር ጥምቀት ላይ በድሬዳዋ እና ጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም በ ውጭ ጉዳይ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ በብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ […]

በለቡ መብራት ኃይል አደባባይ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በለቡ መብራይት ኃይል አደባባይ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በባሕረ ጥምቀቱ እጅግ በርካታ ምእመናን ከዋዜማው ጀምሮ በስፍራው የተገኙ ሲሆን በዓሉ ሌሊት በማኅሌት ደምቆ አድሮ ንጋት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴውን ተከናውኖ በመልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ይርጋ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥተዋል። የምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት […]

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጥምቀት በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል!

በተለምዶ መሿኪያ ተብሎ በሚጠራው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት አከባቢ በሚገኘው የታቦት ማደሪያ ስፍራ ከአስራ ሰባት አድባራትና ገዳማት የወጡ ታቦታት አድረዋል። እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ምእመናን ከዋዜማው ጀምሮ በስፍራው ተገኝተው ሌሊት ማኅሌቱን፣ ንጋት ላይ ደግሞ ሥርዓተ ቅዳሴውንና ትምህርተ ወንጌል ተከታትለዋል። ከቅዳሴው መርሐግብር በኋላ በመ/ሃ ተስፋዬ ሞሲሳ በዓሉን የተመለከተ ሰፊ ትምህርት ተሰጥቷል። በዓሉ ትህትና የተፈጸመበት፣ ምሥጢረ […]

ዛሬ የነጻነታችን ቀን ነው……..ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

ዛሬ በጃን ሜዳ በድምቀት እየተከበረ ባለው የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በዓል ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የበዓሉ መሰረቱ የእዳ ደብዳቤ እንደሆነ ገልጸው ይሄንን የተመለከተ ሰፊ ትምህርት ስጥተዋል። ይህ እዳ ደብዳቤ ተቀዶ ነጻነታችን የታወጀበት የነጻነታችን ቀን ነው ሲሉ በተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ በሚል ቃለ ወንጌል መነሻ አስደግፈው በዓሉን […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይሜኖት ወልዱ የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማሕበር ጎበኙ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይሜኖት ወልዱ በሽሮ ሜዳ ቁስቋም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚገኘው የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማሕበር ጎብኝተዋል። ክቡር ዋና ሥራ አስኪያጁ ተቋሙን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢጎድል ምን ይጠቅመዋል?” ማቴ 16፥26 የሚል የእግዚአብሔር ቃል መነሻ አድርገው አስተምረዋል። የሰው ልጅ […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ!

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጥምቀት አስመልክተው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ። በዓሉን ስናከብር “የበዓሉን መንፈሳዊ ጭብጥ መልእክት” ከልብ በመረዳትና በመገንዘብ መሆን እንዳለበት ብፁዕነታቸው አሳስበዋል። ሐዋርያው የተናገረውን ” …ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን፤ ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን […]

በዓለ አስተርእዮ

አስተርእዮ፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ አስተርእዮ ማለትም መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው፡፡ በግሪክ ቋንቋ ኤጲፋንያ ይባላል ኤጲፋንያ ማለት መገለጥ፤ መታየት ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ዘመን ዘመነ አስተርእዮ ይባላል የመገለጥ፣ የመታየት ዘመን ማለት ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ሰው ሆኖ የተገለጠበት ዘመን ስለሆነ እና እንዲሁም በጥምቀቱ አንድነቱን ሦስትነቱን […]

የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ተጠናቆ ለበዓል አከባበር ሥርዓቱ ዝግጁ ሆነ

ከአንድ ወር በፊት የ2014 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን በማስመልከት በዘመናት አገልግሎት ምክንያት በእጅጉ ተጎሳቁሎ የነበረውን የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀትን ለማደስ በተደረገው እንቅስቃሴ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔና በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አሳሳቢነት የግንባታ ሥራው የተጀመረው የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ መጠናቀቁና ለጥምቀት በዓል ዝግጁ መሆኑ ታውቋል። በምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል የባህረ ጥምቀቱን ገንዳ በአዲስና […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን