• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የእግዚአብሔር ቤት ከሰው ቤት በላይ ንፁህ መሆን አለበት……. ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

በጉራጌ ሀገረ ስብከት በሶዶ ወረዳ ቤተ ክህነት የዶባ ጥሙጋ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አዲስ በተሰራው ቤተክርሴቲያን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዳሴ ቤቱ የጉራጌ ሀገረ እና አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ተክብሮ ውሏል። ለበዓሉ የጉራጌ ሀገረ ስብከት የሥራ ሀላፊዎች እና የክብር እንግዶች በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል። በዚህ ዕለት ትውልድ እና ሀገርን በሀይማኖት አንጾ ስለመገንባት ብፁዕነታቸው […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በወይብላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ላይ በተፈጸመው ግፍ ልጆቻቸውን ላጡት ቤተሰቦች ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ!

በማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ላይ የተፈጸመው ግፍ መላውን ሕዝበ ክርስቲያን ያሳዘነ እና ያስቆጣ እጅግ አስነዋሪ ተግባር መሆኑ የሚታወስ ነው። ያ ሁሉ ሰቆቃ እና ግፍ አልፎ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት በሰላም ተከብሮ ውሏል። ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በደብሩ ከዋዜማው ጀምሮ በመገኘት ማኅሌቱን፣ሥርዓተ ቅዳሴውንና አጠቃላይ […]

“ከሰማዕታት እውነተኛ ምስክርነትን ልንማር ያስፈልጋል” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

ዓመታዊው የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ  ክብረ በዓል በጉራጌ ሀገረ ስብከት በአትርፎ ደብረ ወርቅ  ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል  በድምቀት ታስቦ ውሏል። ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በበዓሉ ላይ ተገኝተው “ከሰማዕታት እውነተኛ ምስክርነትን ልንማር ያስፈልጋል” ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። እውነተኛ ምስክርነት የሰማዕታት የዕለት ተዕለት ተግባር እንደሆነም ጠቅሰዋል። የሰው ልጆች በሙሉ የፈጠራቸውን እና ከዘለዓለም […]

የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማኅበር በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማኅበር በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ የሚፈጅ የአልባሳት፥ የምግብና የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ በአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት ጽ/ቤት የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ተወካዮች እና የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማኅበር አባላት በተገኙበት በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ርክክብ ተደርጓል። ብፁዕ አቡነ […]

ዜና ሕይወቱ ወዕረፍቱ ለብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሊቀ ጳጳስ ዘኢሉባቡር (ከ1960 እስከ 2014 ዓ.ም.)

ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ከአባታቸው ከአቶ ወልደ አምላክ ሁንዴና ከእናታቸው ወ/ሮ በላይነሽ በዲየ በቀድሞ ሸዋ ክፍለ ሀገር፤ በፍቼ ዞን በሙከጡሪ ወረዳ በበቾ ፋኒሊ ቀበሌ ልዩ ስሙ ደሴ በሚባል ቦታ በ1960 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም የጀመሩት ብፁዕነታቸው፤ በገዳሙ ከሚገኘው አንጋፋው የመምህር ገብረ ማርያም ንባብ ቤት መሠረታዊ የግእዝ ንባብ፣ በደብረ ጽጌ ገዳም ከመምህር ልዑል […]

” እግዚአብሔር የስስትን መንፈስ ከልባችን አስወገደልን” … ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

የሰሜንና የደቡብ ወሎ እንዲሁም የከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ባካሄደው መንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር ነው። ብፁዕነታቸው በጦርነቱ ወቅት ለአምስት ወራት ገደማ በአህጉረ ስብከታቸው ከምእመናን እና ከሕዝቡ ጋር ስላሳለፉት ሁኔታዎች አስመልክተው ማብራሪያ ለጉባኤው ሰጥተዋል። በዚያ በችግር ወቅት ምእመኑ እና ሕዝቡ አንዱ ለሌላው […]

“የወንጌል አገልግሎትን በማስቀደም ዘመኑን የዋጀ ሥራ ልንሠራ ይገባል” …ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት የበጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን አድንቀዋል። ክፍለ ከተማው ያከናወናቸውን ሥራዎች እና የገጠሙትን ተግዳሮት በመጽሔት አሳትሞ ለአድባራቱና ለገዳማቱ ለንባብ ማብቃቱም ለቀጣይ ሥራዎች ትልቅ መነሣሣትን የሚፈጥር ነው ብለዋል። ብፁዕነታቸው የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነብርሃን በበጀት ዓመቱ […]

የቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት በሥሩ ካሉት አድባራትና ገዳማት ጋር በመሆን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን እያካሄደ ይገኛል!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት በሥሩ ካሉት አድባራትና ገዳማት ጋር በመሆን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን አካሄደ። ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ የሰሜንና የደቡብ ወሎ እንዲሁም የከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ጉባኤውን በጸሎት ከፍተዋል። ጉባኤው የተካሄደው በቦሌ […]

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት እንደሚያወግዝ አስታወቀ!!!

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር የተፈጸመውን ሕገወጥ ድርጊት በመቃወም መግለጫ አወጥቷል። ጉባኤው በመግለጫው ሃይማኖቶች የትህትና፣ የሰላምና የአንድነት፣ የፍቅርና መከባበር መሠረቶች ናቸው ብሏል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የሰላም መሠረት ሆና ዘልቃለች ያለው የጉባኤው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን አጥብቀን እንቃወማለን ነው ያለው። ጥር […]

“እየተፈጠረብን ያለውን ችግር ለመፍታት ቅዱስ ሲኖዶስ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል” …ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው እየተፈጠረብን ያለውን ችግር ለመፍታት ቅዱስ ሲኖዶስ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል” ሲሉ  አስታወቁ። ብፁዕነታቸው በቦታው ተገኝተው ሕዝበ ክርስቲያኑን  ያፅናኑ እና ቡራኬ የሰጡ ሲሆን እየተፈጠሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እስከ ሕይወት መስዋዕትነት እያስከፈለ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል። የተፈጠረውን ችግር ለቅዱስ ሲኖዶስ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን