ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያንን የሕንጻ እድሳት ጎበኙ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውን የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያንን የሕንጻ እድሳት ሥራ ጎብኝተናል፡፡ቤተ ክርስቲያኑ ከዓድዋ ታሪክ ጋር በእጅጉ የተሣሠረ ታሪክ አለው፡፡ በዚህም የተነሣ በሁለተኛው የፋሽስት ወረራ ጊዜ እንደ ጦር ወንጀለኛ ተቆጥሮ ዋጋ ከፍሏል፡፡ በእሳት እስከ መቃጠልና ጥቁር ቀለም እስከ መቀባትም ደርሷል፡፡
ቤተ ክርስቲያኑ ደረጃውን በጠበቀና ልዩ ልዩ ባለሞያዎችን ባሳተፈ መልኩ እየታደሰ መሆኑን ተመልክተዋል።
አሁን የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያን ሕንጻና ግቢ ታሪካዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ መታደሱ ደግሞ፣ ታሪኩን የተሟላ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኑ እና የአካባቢው ጥገና አሁን ከጀመርናቸው የከተማ ማዘመን ሥራዎች፣ የቱሪስት መዳረሻዎች እና የቅርስ አጠባበቅ ደረጃዎች ጋር ተጣጥሞ እንዲሠራ፣ የሚመለከታቸው ሁሉ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ አደራ መልእክት አስተላልፈዋል ፡፡
በጉብኝቱ ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር እና መልአከ ገነት ክብሩ ገብረ ጻድቅ የደብሩ አስተዳዳሪ ተገኝተዋል።
