በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሯል

በበዓሉ ላይ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ መጋቤ ሠናያት የቻለው ለማ የአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ አሚን ለይኩን አበጀ የደብሩ አስተዳዳሪ ፣የሀገረ ስብከቱና የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ተወካዮች፣ የሰበካ ጉባኤና የሕንጻ ኮሚቴ አባላት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የደብሩ ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና መዘምራን በርከታ ምእመናንና ምእመናት ተገኝተዋል።
በበዓሉ ላይ በሊቃውንትና በደቦሩ ሰንበት መዘምራን ያሬዳዊ ዝማሬ ቀርቧል።
በቀጠልም ትምህርተ ወንጌል በሊቀ ሊቃውንት ሥሙር ዓላምረው ተሰጥቷል።
በደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ለይኩን አበጀ ለክቡር ሥራ አስኪያጁ የእንኳን ደህና መጡና ለበዓሉ ታዳሚዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
አያይዘውም በመታነጽ ላይ ስለሚገኘው የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን አሁን ያለበትን ሁንታ የገለጹ ሲሆን በሁሉም በተቻለው አቅም ሁሉ በሐሳቡ በገንዘቡና በጉልበቱ እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።
መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አባታዊ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትና መመሪያ አስተላልፈዋል።
የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጥንታውያት ከሚባሉ ገዳማትና አድባራት መካከል አንዱ ነው።