ተቀጸል ጽጌ በዓል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጬጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት ተከብሯል

መስከረም ፲/፳፻፲፰ ዓ/ም
በየዓመቱ መስከረም ፲ ቀን በጥንት ጊዜ ወርኃ ክረምቱ አለፈ የጽጌ ዘመን መጣ ይህን ያደረገ እግዚአብሕር ይመስገን ሲሉ ተቀጸል ጽጌን መስከረም ፳፭ ቀን በታላቅ የምስጋና ማዕድ በቤተ ክርስቲያንንና ነገሥታቱ አብያተ መንግሥት ይከበር ነበር።
በኋላ አጼ ዳዊት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ግማደ መስቀል ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ መስከረም ፲ ቀን በመግባቱ ምክንያት መስቀል ከሁሉም ነገር በላይ ነውና የተቀጸል ጽጌ በዓል በወደ ዚሁ ቀን በመሳብ አንድ ላይ ማክበሩ እንደቀጠለ ሊቃውንት ይናገራሉ።
የተቀጸል ጽጌ በዓል ከ፲፱፻፹፯ ዓ/ም ወዲህ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፭ኛው የቤተ ክርስቲያናችን ፓትርያርክ አማካኝነት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እስካሁን በተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብራት እየተከበረ እዚህ ደርሷል።
በዚህ ዓመት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዲዮስቆሮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና የሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ፣ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአድባራትና ገደማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል ።