የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እጅግ ከፍተኛ ልዩ ተሸላሚ በመሆን ስጦቷ ተበረከተለት
በተያያዘም ከየምድቡ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ለወጡ አህጉረ ስብከት #የሞተር ሳይክል ሽልማት ተበርክቷላቸዋል።
ጥቅምት፰/፳፻፲፰ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ከጥቅምት ፬ እስከ፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ሲካሔድ የሰነበተው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በትላንትናው ዕለት መጠናቀቁን ተከትሎ ተመሳሳይ አቅም ያላቸው አህጉረ ስብከት በአሥራ አንድ ምድብ ተከፋፍለው እንዲወዳደሩ የተደረጉት አህጉረ ስብከት ውድድር በሸልማት ኮሚቴው የመወዳደሪያ መስፈርት መሰረት ተለክተው ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ የወጡት አህጉረ ስብከት እንዲሸለሙ ተደርጓል።በዚህም መሰረት፦
ከምድብ አንድ
1ኛ. ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት … 81 ነጥብ
2ኛ. ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት.. 71 ነጥብ
3ኛ. ሲዳማ ሀገረ ስብከት… 69 ነጥብ ሀስብከት ተሸላሚዎች ሆነዋል።
ከምድብ ሁለት
1ኛ. ወላይታ ሀገረ ስብከት… 7ዐ ነጥብ
2ኛ. ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ….. 68 ነጥብ
3ኛ. ድሬደዋ ሀገረ ስብከት….. 65 ነጥብ ተሸላሚዎች ሆነዋል።
ከምድብ ሦስት
1ኛ. ጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት …89 ነጥብ
2ኛ. አርሲ ሀገረ ስብከት….87 ነጥብ
3ኛ. ጅማ ሀገረ ስብከትና ምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ… 67 ነጥብ እኩል በማምጣት ተሸላሚዎች ሆነዋል።
ከምድብ አራት
1ኛ. ሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት……… 78 ነጥብ
2ኛ. ምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት …. 76 ነጥብ
3ኛ. ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ……. 61 ነጥብ ተሸላሚዎች ሆነዋል።
ከምድብ አምስት
1ኛ. ሸካ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ሀ/ስብከት 82 ነጥብ
2ኛ. ሰሜን ሸዋ /ሰላሌ/ ሀገረ ስብከት 81 ነጥብ
3ኛ. ዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ……….79 ነጥብ
ተሸላሚዎች ሆነዋል።
ከምድብ ስድስት
1ኛ. ጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት 78 ነጥብ
2ኛ. ከፋ ሀገረ ስብከት 77 ነጥብ
3ኛ. ኢሉ ባቦር ሀገረ ስብከት… 71 ነጥብ
ከምድብ ሰባት
1ኛ. ጉራጌ ሀገረ ስብከት…. 89 ነጥብ
2ኛ. ሶማሌ ሀገረ ስብከት…… 86 ነጥብ
3ኛ. ደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ….. 70 ነጥብ
ተሸላሚዎች ሆነዋል።
ቡድን ስምንት
1ኛ. ሐድያና ሥልጤ ሀገረ ስብከት ….. 83 ነጥብ
2ኛ. አሶሳ ሀገረ ስብከት…. 74 ነጥብ
3ኛ. ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት… 7ዐ
ነጥብ ተሸላሚዎች ሆነዋል።
ቡድን ዘጠኝ
1ኛ. ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት… 71 ነጥብ
2ኛ. ከምባታ ጠንባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት… 65ነጥብ
3ኛ. ጋምቤላ ሀገረ ስብከት ….64 ነጥብ
ተሸላሚዎች ሆነዋል።
ቡድን አሥር
1ኛ. መተከል ሀገረ ስብከት… 72 ነጥብ
2ኛ. ጎፋና ባስኬቶ ሀገረ ስብከት … 7ዐ ነጥብ
3ኛ. ራያ ሀገረ ስብከት… 68 ነጥብ
ተሸላሚዎች ሆነዋል።
የውጪ አህጉረ ስብከትን በተመለከተ ደግሞ፦
ምድብ አንድ
1. ዋሽንግተን ኦሪገን ሲያትልና አካባቢው ሀ/ስብከት
2. ስሜን ካሊፎርኒያና አካባቢው ሀ/ስብከት
3. ዋሸንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት
ምድብ ሁለት
1ኛ. ቴክሳስ እና አካባቢው ሀ/ስብከት
2ኛ. ደቡብ ካሊፎርኒያና አካባቢው ሀ/ስብከት
3ኛ, ሜኒሶታና አካባቢው ሀ/ስብከት
ምድብ ሦስት
1ኛ. ጆርጂያ እና አካባቢው ሀ/ስብከት
2ኛ. ኮሎራዶ ሀ/ስብከት
3ኛ. እንግሊዝና አካባቢው ሀ/ስብከት
ምድብ አራት
1ኛ. ምዕራብ ካናዳ እና አካባቢው ሀ/ስብከት
2ኛ. ምሥራቅ ካናዳ ሀ/ስብከት
3ኛ. የካሪቢያን ደሴቶችና ሀ/ስብከት
ምድብ አምስት
1ኛ. ሰዊድን ኖርዲክ ሀገራት ሀ/ስብከት
2ኛ. ምሥራቅ አውስትራሊያ ሀ/ስብከት
3ኛ, ጀርመንና አካባቢው ሀ/ስብከት
4ኛ, ካናዳ ኤድመንተን ሀ/ስብከት
ምድብ ስድስት
1ኛ. መካከለኛው ምሥራቅ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ሀ/ስብከት
2ኛ, ጣሊያንና አከባቢው ሀ/ስብከት
3ኛ. ሩቅ ምሥራቅ እና አከባቢው ሀ/ስብከት
ምድብ ስምንት
1ኛ. ደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ ሀ/ስብከት
2ኛ. በምሥራቅ አፍሪካ (የኬኒያ፣ አጋንዳ፣ ታንዛኒያ ሩዋንዳ ጂቡቲ ) ሀ/ስብከት
3ኛ- ሰሜን አፍሪካ እና አካባቢው
እውቅና ተሰጥቷቸዋል ።
# ከፍተኛ ልዩ ተሸላሚ በመሆን
1ኛ. ሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት
2ኛ. ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት
3ኛ. ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በልዩ መሥፈርት የተሸለሙ ሲሆን እጅግ ከፍተኛ ልዩ ተሸላሚ በመሆን ደግሞ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተሸልሟል።
ተሸላሚ አህጉረ ስብከት የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጲጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እጅ ተቀብለዋል።
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጉባኤውን መጠናቀቅ በማስመልከት ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት በርካቶች አህጉረ ስብከት በከፍተኛ ችግር ውስጥ በመሆን ላስመዘገባችሁት የሥራ እድገት እያመሰገንን ወደፊት የበለጠ ውጤት እንድታስመዘግቡ አደራ ለማለት እንወዳለን ብለዋል።
ብፁዕነታቸው አክለውም ልማትን በተመለከተ በአጥቢያና በአህጉረ ስብከት ደረጃ እየተደረገ ያለው ጥረት በእጅጉ ተስፋ ሰጪ ስለሆነ በተለይም ምግባረ ሰናይ በሆኑ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አደራ ብለዋል።
በብዙ ወጀቦች ውስጥ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅምና የሚበጅ ሥራ እንሰራለን።ሙሉ ሃይላችንን ለወንጌልና ለበጎ አድራጎት ሥራ ቅድሚያ በመስጠት እንሠራለን። በአሉባልታና በትችት ጊዜያችንን ለማጥፋትና ወርደን ከእነርሱ ጋር እሰጣገባ እንድንገባ ለሚፈልጉ ዕድሉን በመንፈግ ለቤተክርስቲያናችን ዕድገትና ልዕልና በቆራጥነት እንሠራለን ብለዋል ።
በመጨረሻም በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ተሰጥቶ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።
© የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
