“በእናንተ ፊት ቃል እገባለሁ”
“የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የመፈጸምና የማጽፈጸም ሓለፊነቱን የመወጣት ግዴታ ስላበት ለሰንበት ትምህርት ቤት የጸደቀውን ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ እያደረግ ይገኛል። በቀጣይም በሀገረ ስብከታችን ሥር የሚገኘውን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ለመደገፍና ለማጠናከር ይቻል ዘንድ አስፈላጊውን እገዛ ለማድረግ በእናንተ ፊት ቃል እገባለሁ”
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬ ዕለት በሰንበት ተማሪዎች እውቅና መርሐ ግብሩ ከተናገሩት የተወሰደ።
ታኅሣሥ ፮/፳፻፲፯ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ