የሰባክያነ ወንጌል ኅብረት ጥሪ

ለታላቅ የምሥራች ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ
“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።”
፩ኛ ቆሮንቶስ ፱፥፳፫
የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ትልቁ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአ/አ ሀገረ ስብከት የሰባክያነ ወንጌል ኅብረትን በማስመልከት የምስጋናና የዕውቅና መርሐግብር ላይ መላው ኦርቶዶክሳውያን ተገኝታችሁ የደስታ ቀናችንን በጋራ እናክብር በማለት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በዕለቱም፡-
= የሰባክያነ ወንጌል ኅብረት የምስጋናና
የዕውቅና መርሐግብር ያከናውናል፡፡
= በመርሐግብሩም ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀ/ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ ብፁዕ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕርዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአ/አ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎችና እና የአ/አ ሀገረ ስብከት የየክፍሉ ኃላፊዎች፤ ጥሪ የተደረገላቸው የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች፤ ሰባክያነ ወንጌል፤ ልዩ ልዩ ተቋማት፤ ይገኙበታል።
እርስዎም በመርሐ ግብሩ እንዲገኙ የከበረ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት
በስብከተ ወንጌል ዋና ክፍል
የሰባክያነ ወንጌል ኅብረት።

Source:-አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ